Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 19, 2016

ከዐማራ ሐኪሞች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ

ከሞትና ሥቃይ ያልታደጋት እርግዝናን አጥብቃ የገታች የአማራው እናት፣
የኢትዮጵያ ማእከላዊ ስታትስቲካል ኤጀንሲ የ2016 DHS ቁልፍ አመልካቾች በአማራ ሐኪሞች ዕይታ፤
እድሜአቸው ከ 15- 49 ዓመት የሆኑ የአማራ ሴቶች 47 በመቶ የሚሆኑት የእርግዝና መከላከያን በመጠቀም ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በኢትዮጵያ ከፍተኛው ነው። ይህም ካጠቃላይ ካገሪቱ መጠን 9 በመቶ ከፍ ያለ ነው። የመጀመሪያ ልጇቸውን ከወለዱ የአማራ እናቶች ዉሥጥ 45 ፐርሰንት የሚሄኑት ብቻ የመንጋጋ ቆልፍ ክትባት አግኝተዋል። ከሀገሪቱ ትንሹና በ8ኛ ደረጃ ላይ ሲሆን የጨቅላ ህፃናት ሞት እንዲያሻቅብ ያደርገዋል። ላለፋት 5 ዓመታት 27 ፐርሰንት ብቻ ናቸው በጤና ማእከል የወለዱት። ከሀገሪቱ 6ኛ ደረጃ ላይ ነው። በምጥና ድህረ ወሊድ ጊዜዋ በሰለጠነ ባለሞያ የመታየት እድሏም በንፅፅር አነስተኛ ነው።
ውልደትን መግታት የህዝብን ቁጥር፣ ሞትና ብዙ ስነተዋልዷዊ ችግሮችን ይቀንሳል። ወሊድን አጥብቆ መከላከል የሴቶችን የትምህርትና ኢኮኖሚ መዳበር ይገልፃል። በራስ መወሠንን ያረጋገጠችበት ባለ ፀጋ መሆንን ማሳያ ነው። ይህን ማንም እናት ብትታደል የሁሉም ደስታ ይሆን ነበር። የአማራዋ እናት ግን አብዝታ ያልተማረች ደሀ እናት ነች። የአማራዋ እናት ግን አብዝታ የምትሞትና ህፃኗን ምታጣ ደሀ እናት ነች። ቤተሰብን መመጠን ግን እየተካነችበት ነው ይለናል የኢትዮጵያ DHS 2016። እርስ በርሳቸው የሚጋጩና ተጔዳኝ ያልሆኑ የአማራን ህዝብ ህልዉና በድጋሜ የሚጎዱና አደገኛ የጤና ፖሊሲ ውጤቶች መሆናቸውን የአማራ ሀኪሞች ያምናሉ።
የአሜሪካው ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን (US Food and Drug Administration) ለህዝቦቹ አንድን መቆጣጠሪያ ተፈፃሚ ለማረግ ካስር ዓመት በላይ ጥናትና ምርምር ማካሄድ አለበት።
ከ2012-2016 ባሉት ጊዜያት ውስጥ ‘ዲፖፕሮቬራ’ እና ‘ኖርፕላንት’ የተባሉት በብዛት በአማራ ውስጥ ተሠጥተዋል። ‘በስኬል አፕ’ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ በሰለጠኑ ኤክስቴሽን ባለሞያወች በብዛት ለመስጠት ታቅዷል። ስለ ጎንዮሽ ጉዳታቸው አማራ ላይ የተጠና ጥናት ባይኖርም የተወሠኑ የሴቶች ስነ ተዋልዶ ተቆርቌሪዎች ይከለክላሉ።
ፖለቲካዊ ተፅእኖ አንድ ማኅበረሰ እርግዝናን አጥብቆ እንዲከላከል ሊያደርግ ይችላል። አስገዳች ህግ በማስፈፀምና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ጥቂቶች ናቸው።
የአንድ ሀገር የሀብት ክምችት መጎልበት አንዲት ሴት በህይወት ዘመኑዋ የምትወልዳቸዉን ልዦች መጠን እንድትቀንስ ያረጋል። ለልዦች ወጭ ለመቀነስ መቆጣጠርያ ለመጠቀም ትገደዳለች።
በተቃራኒው ደግሞ ድሃና ያልተማረች እናት ግን ልጇን በሞትና ስቃይ ልታጣ ትችላለች። የተወለደ የማደግ እድሉ ትንሽ መሆኑን ታቃለች። ንፁህ ዉሃና በቂ ምግብ ስለሌለ። በቂ ክትባት ስለማይታደለው በሽታ ይገለዋል። በቂ ሀኪም ከሌለ ሳይታከም ይሞታል። ልጅ የሀብት ምንጭና ቤተሰብ ጧሪ መሆኑን ትረዳለች። ይህ አይነቱ ማህበረሰብ መቆጣጠሪያን ቅድሚያ አይሰጥም። በብዙ ጥናቶች የተረጋገጠ እውነታ ነው። ችግሮች ሲፈቱለትና ሴት በት/ት ስትታነፅ ባለመውለድና ልጅ በመቀነስ ጊዜ እንዲኖራት ትፈልጋለች። ዘመናዊ መሆን የመጨረሻው ደረጃ ሲሆን የእናትና ህፃን ሞት ይቀንሳል።እንደ ሀይማኖቷ ሁኔታ እርግዝናን አጥብቃ ትከላከላለች። የልጅ መጠኗን ትቀንሳለች።
የኢትዮጵያ ጤና ፖሊሲ ግን ከዚህ ህግና እውነታ አልፎ ድብቅ አላማው ገሀድ እየሆነ ነው። በጤና ፖሊሲ ስም የአማራውን ህልውና ማውደም። በቅኝ ግዛት ዘመን ያገለግል የነበረ ባዮፖለቲካ ነው። በጤና ጥበቃ ሚንስቴር በአንድ ዳይሬክቶሬት የሚመራው የእናቶችና ህፃናት ጤና ፕሮግራም፣ ስድስት ተዛማጅ ኬዝ ቲሞችን በውስጡ በማቀፍ የሚሊዮን አማሮችን ህይወት እየቀጠፈ ስለመሆኑ የEDHS 2016 ሪፓርት በቂ ይመስላል። ውጤቶች በአፃንኦት ሲታዩ ከአድሎአዊነት አልፈው የህልውና ጉዳይ ይሆናሉ። መድሀኒት ኤጀንሲ /PFSA ፣ PLMU ፣ጥራትና ቁጥጥር /FMHACA ፣ የኤች አይ ቪ ና አባላዘር/ HIV-AIDS & STI ፣በሽታ መከላከል/Disease Prevention and Control እና የክትባት ፕሮግራም/EPHI የሚባሉ ሲሆኑ ለዚህ ተጠያቂ ናቸው። ላንድ ጎል የቆሙ በመምሰል የአማራን ህዝብ ቁጥር የሚገታ ስልት የቀመሩ ናቸው።
ይህን እውነታ የሚያረጋግጡት ብዙ መረጃዎች አሉ፤
1ኛ. በአማራ ላይ ወሊድ ቁጥጥርን በሥፋትና በፍጥነት እንዲደርስ እየተደረግ ነው። እውቀትና ልምድ በሌላቸው አዲስ ‘የጤና ኢክስቴንሽን ሰራተኞች’ በገጠሩ አማራ ይሰጣል። በዚህ ምክንያት 47 በመቶ የሚሆኑት የአማራ ሴቶች እርግዝናን እንዲከላከሉ ሆኖአል። ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በኢትዮጵያ ከፍተኛው ነው። በተገላቢጦሽ የመጀመሪያ ልጇቸውን ከወለዱ የአማራ እናቶች ዉሥጥ 45 ፐርሰንት ብቻ ናቸው የመንጋጋ ቆልፍ ክትባት ያገኙት። የጨቅላ ህፃናት ሞት በዚህ ምክንያት ያሻቀበ ነው። የተሻለ የክትባት ሽፋን የያዙት አዲስ አበባ 82፣ ድሬዳዋ 72 ፣ሀረር 70፣ ትግራይ 62፣ጋምቤላ 55፣ቤኒሻንጉል 53፣ደቡብ 51 እና ኦሮምያ 47 በመቶ ናቸው።
ላለፋት 5 አመታት 27 ፐርሰንት ብቻ የአማራ እናቶች ልጆቻቸውን በጤና ማእከል ሲወልዱ የአዲስ አበባ 97 ፣ ትግራይ 57 ፣ ድሬዳዋ 56፣ ሐረር 50 ፣ ና ጋምቤላ 45 በመቶ በቅደም ተከተል ናቸው።
የአማራ እናት በምጥ እና በድህረ ጊዜዋ በሰለጠነ ባለሞያ የመታየት እድሏም በንፅፅር አነስተኛ ነው። በዚህ ወሳኝና አደገኛ ጊዜ የእናትና ልጅ ሞት ከፍ እንዲል ያረገዋል።
ትኩረቱ ወሊድ ቅነሳ ላይ ነው። አሁንም አዲስ ሞያተኞችን በማሰልጠን ወደ አማራ ልኴል። ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉትን፡ ኢምፕላኖን (Implanon) ና ሉፕ(IUD) የተባሉትን የበለጠ ለመተግበር ከአዲስ አበባ ሰልጥነው ወደ ክልሉ ገብተዋል።
እውነታው እንደ ሼርማና ራዘር ፎርድ የተባሉ ተመራማራወች ከሆነ የዉልደት መጠንን ለመቀነስ 80 በመቶ የሚሆኑ ሴቴች የሚማሩበትን ሁኔታ መመቻቸት ግድ ነው ይላሉ። በ10 በመቶ ትምህርትን ማሳደግ ከተቻለ፣ መቀንስ የሚቻለው የልጅ መጠን ካንድ ያነሰ ነው (0.5 ብቻ )። የአማራ እናት የተደረገላትን የት/ት እድገት በምናብ ማሰብ ይበቃል።
2ኛ. ሌላውና አሳሳቢው በአማራ የተመድቡ ሀኪሞች ስራቸውን ትተው ለመሄድ የሚገደዱበት ዘዴ መንደፋቸው ነው። ስራን ከአማራ የመልቀቅ ወይም ትቶ የመሄድ እድላቸው ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ጋር ሲነፃፀር በሁለት እጥፍ የጨመረ ነው።
ብዙ ጥቅማጥቅሞችን መከልከል አንዱ ምክንያት ነው፤ አማራው በኢትዮጵያ በንፅፅር ትንሽ ሀኪሞች ያሉበት እንዲሆን በመደረጉ ለከባድ ሞትና ስቃይ ተዳርጔል። ለ118,805 አማሮች አንድ ሀኪም ብቻ በመሆኑ።
ይህን ሀቅ በመረዳት የአማራን እናትና ህልዉና መታደግ የሁሉም ኃላፊነት ነው፤
© የአማራ ሐኪሞች ማኅበር
አዲስ አበባ
ታህሥስ 8 ቀን 2009 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment

wanted officials