Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 17, 2016

የአውሮጳ ህብረት አባል በሆኑት ክብርት አና ጎመስ ላይ ህወሃት የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመረ


የአውሮጳ ህብረት አባል በሆኑት ክብርት አና ጎመስ ላይ ህወሃት የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመረ



በምርጫ 97 ወቅት የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን በመምራት ኢትዮጵያ ቆይተው ከተመለሱ ወዲህ የህወሃት አገዛዝ በዘጎቹ ላይ የሚፈጽማቸውን የሰባአዊ መብት ጥሰቶች እየተከታተሉ በማጋለጥ የታወቁትን የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ አባል ክብርት አና ጎመዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሰሙት ድምጽ እንዲያቆሙ ለመጠየቅ የህወሃት አገዛዝ በቅጥረኝነት ያሰማራቸው አባላቱና ደጋፊዎቹ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል

የህወሃት የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ጋር በቅርበት እንደሚሠራ የሚታወቀው አይጋ ፎረም የተባለው ድረ ገጽ ላይ አባላትና ደጋፊዎች እንዲፈርሙት ተለጥፎ ያለው የተቃውሞ ፊርማ ደብዳቤ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ክብርት አና ጎመስ ባለፈው ወር መጀመሪያ ሳምንት ላይ ብራስልስ በሚገኘው የአውሮጳ ፓርላማ ጽቤት ስብሰባ ላይ ተሳትፈው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በህወሃት ደህንነቶች ተይዘው እስር ቤት የተወረወሩት ዶክተር መረራ ጉድናን ለማስፈታት ህብረቱ ጠንካራ አቋም በኢትዮጵያ ላይ እንዲወስድ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጀተዋል ። ክብርት አና ጎመስ የአውሮጳ ህበረት በህወሃት መራሹ አገዛዝ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከማዘጋጀታቸው በተጨማሪ ለህብረቱ የውጪ ግንኙነት ሃላፊ ለሆኑት ለማዳም ፌደሪካ ሞርጋሪኒ ባለፈው ሳምንት በጻፉት ደብዳቤ ላ፤ ዶ/ር መረራ ጉዲና የታሠሩት በርሳቸው መሪነት የአውሮጳ ህበረት በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚፈጸመው የሰባዊ መብት ጥሰት ለመስማትና አገራችን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ወዴት እንደሚያመራ ለመገምገም አዘጋጅቶት በነበረው ስብሰባ ላይ መሳተፍቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ ነው ማለታቸው ህወሃትን ክፉኛ አስቆጥቶታል። ክብርት አና ጎመስ ባልደረባቸው ለሆኑት ኢጣሊያዊቷ የህብረቱ የውጪ ግንኙነት ሃላፊ በጻፉት ደብዳቤ ዶ/ር መረራ ጉዲና በህወሃት አገዛዝ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀውና ህብረቱ አዘጋጅቶት በነበረው በዚያ ስብሰባ ላይ ከተገኙት ሌላው እንግዳ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ጎን ለጎ ተቀምጦ መታየታቸው ብቻ እንደወንጀለኛ እንዳስቆጠራቸው ይህም ኢትዮጵያ ወስጥ የዜጎች ነጻነትና ሃሳብን የመግለጽ መብት ምን ያህል የከፋ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመልካች ነው ብለው መግለጻቸው ህወሃትንና ደጋፊዎቹን እጅግ ያናደደና የተቃውሞ ፊርማ እስከማሰባሰብ ያደረሰ እንደሆነ በተቃውሞ ደብደቤው ላይ ተገልጾአ።

በዚህም የተነሳ ክብርት አና ጎመስ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ እጃቸውን ከማስገባት እንዲቆጠቡ ለመጠየቅ በህወሃት መሪነት የተጀመረው ፊሪማ የማሰባሰብ ዘመቻ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚገኝባቸው አገሮች በሙሉ ውስጥ ለውስጥ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ሆኖም በርካታ ትኩረት ለማግኘት ያልቻለና በራሱ በህወሃት አባላትና ደጋፊዎች ዘንድ ሳይቀር እንደ ትልቅ ተስፋ መቁረጥ እርምጃ እንደታየ ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰ ከደረሰ መረጃ ለማወቅ ተችሎአል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በብድርና በተለያየ መንገድ ከአለም አቀፍ ህብረተሰብ የሚያገኘውን ገንዘብ ለገጽታ ግንባታ አገልግሎት በማዋል በጣም ውድ ገንዘብ በመክፈል ትላልቅ የሎቢ ተቋሞችን ቀጥሮ ሲያሰራ እንደኖረ ይታወቃል። ካለፈው እንድ መት ወዲህ በመላው አገሪቱ በተለይም በኦሮሚያ፤ በኮንሶና በአማራ ክልሎች ተቃውሞን ለማፈን ሲል እየተወሰደ ባለው የሃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጽሃን ዜጎች በግፍ መጨፍጨፋቸውና በሺዎች የሚቆጠሩት በጅምላ መታሠራቸው የአገዛዙን ፍጹም አምባገነንነትና አውሬነት ባህሪ ለአለም ህዝብ ያጋለጠ በመሆኑ ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ የሎቢ ተቋሞች ሊያስተባብሉትና ሊሸፋፍኑለት ከሚችሉት በላይ እንደሆነባቸው በአሜሪካና በአውሮጳ ለህወሃት ተቀጥረው ከሚሠሩ እነዚሁ የሎቢ ድርጅቶች አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials