Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, December 18, 2016

አይሪሽ ኢትዮጵያዊትዋ የፊልም (ሲኔማ) ተዋናይ ሩት ነጋ
ጋሻው ገብሬ አባይ ሚዲያ (Vogue)መጽሄት እንደዘገበው።

ሩት ነጋ በቅርቡ ዝናን እየትጎናጸፍች የምትግኝ የሆሊውድ ተዋናይ ናት። ጄፍ ኒኮልስ የተባለው የፊልም ድሬክተር ያቀረበው ለቪንግ (Loving) የተባለው ይሲኔማ ዝናን አትርፎላታል:: እንደ ቮግ መትሄት(Vogue) አባባል የዘመናችን ኮክብ አሰኝቷታል። ለቪንግ (Loving) ሲኔማ የሚተርክው በቀድሞ የገጠጠ ዘረኝነት በነገሰባት አማሪካ ነጭና ጥቁር በሆኑ ተዋደው ትዳር በመሰረቱ ሁለት ዜጎች ላይ በቆዳ ቀላማችሁ ምክንያት ጋብቻቸሁ ህጋዊ ሊሆን አይችልም።ነጭና ጥቁር ሰዎች የመሰረቱት ጋብቻ በህግ ዘንድ ቦታ የለውም ተብሎ በአሜሪካ ተደንገጎ ሲኖር ኖሮ በነዚሁ ሁለት ሰዎች ለህጋዊ መብታቸው መክራክራቸውን መርታታቸውንም የሚያሳይ ነው። ለሲኔማው ትረካ ህይውታቸው መሰረቱ የሆነው ሚልድሬና ሪቻርድ ይባሉ የነበሩ ይቨርጂኒያ ነዋሪዎች ናቸው።ሩት ነጋ ጆኤል እግጋርቶን ጋር በመሆን ፊልሙን ሰርታለች።
ሩት ነጋ ከኢትዮጵያዊ አባትዋና የአይር ላንድ ዜጋ ክሆነችው እናትዋ ትወለዳለች።አባትዋ ዶክተር ነጋ የጥቁር አንበሳ ሃኪም የነበረ ሲሆን እናትዋ በዚሁ ሃኪም ቤት ነርስ ነበረች።ሩት ነጋ “የክልስነት ፖለቲካ ድርሽ እንዲልብኝ አልፋልግም።” ትላለች።አባትዋ ነጋ ያረፈው 1988 ሲሆን ያደገችው አየር ላንድ ነው።ከሰፊ ቤተ ሰብ ዘረኝነት ሳይሰማኝ አድጌ እንግሊዝ አገር ግን የዘረኝነት ሰለባ ሆንኩ ትላለች።የአማሪካ ጥቁር ምሁራን መጥጽሀፎቻቸውንና አስትሳሰቦቻቸውን መረመርኩ ትላልች። ቶኒ ንሞሪሰንን፤ማያ አንጄሎን እና ጃምስ ባልድዊንን ትጠቅሳላእች።አሜሪካ ባላድግም የህይወታቸውን ታሪክ ልምዳቸውን እጋራለሁ፤እንደሰው ያሳላፉትን ልብ እላልሁ ትላለች።
“አይሪሽ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል ጥንቅቅ ብዬ ነው። ለምን ስሜቴ ኢትዮጵያዊ ነው። መልኬ ኢትዮጵያዊ ነው።በኢትዮጵያ ግን 81 ቋንቋዎች ሲኖሩ አንዱንም ቋንቋ አልናገርም” ትላለች።አባትዋን ማጣትዋ የሚያንገበግባት ሩት ነጋ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials