Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 12, 2016

አምባገነኑ ያሜህ “አላህ ብቻ ከስልጣኔ ያነሳኛል” እያሉ ነው



አምባገነኑ ያሜህ “አላህ ብቻ ከስልጣኔ ያነሳኛል” እያሉ ነው
=============Image may contain: 4 people, people standing
ጋምቢያን ለሶስት አስርት ዓመታት የገዙት ያህያ ያሜህ ‹‹አላህ ብቻ››ከስልጣን ሊያነሳቸው እንደሚችል በመግለጽ ለምን የዘንድሮውን የምርጫ ውጤት ለመቀበል ከወሰኑ በኋላ ሐሳባቸውን እንደቀየሩ ተናግረዋል፡፡
ዲሴምበር 1 በተደረገው ምርጫ የፕሬዘዳንቱ ዋነኛ ተፎካካሪ የነበሩት አዳማ ባሮው ያሜህን መርታታቸውም የአገሪቱ ምርጫ ቦርድ ቢያሳውቅም በመጀመሪያ ሽንፈታቸውን በጸጋ እንደሚቀበሉት ተናግረው የነበሩት ያሜህ ድምጽ ተጭበርብሯል በማለት የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውጤቱን በመቀልበስ አዲስ ምርጫ እንዲደርግ ይወስን ዘንድ ጠይቀዋል፡፡
‹‹በዚህ ዓለም ላይ የሚገኝ የትኛውም ኃይል እኔን አያስፈራኝም››በማለት በአገራቸው ቴሌቭዥን ለህዝቡ ንግግራቸውን ያስደመጡት ያሜህ ‹‹ፍትህ መረጋገጧን ማወቅ እፈልጋለሁ እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ ነገር ግን ፈሪ አይደለሁም››ብለዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት፣አፍሪካ ህብረትና የምዕራብ አፍሪካ አገራት ህብረት ያሜህ ሽንፈታቸውን በመቀበል ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
በ1994 መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣን የያዙት ያሜህ የምዕራብ አፍሪካ አገራት መሪዎች ላቀረቡላቸው የስልጣን ይልቀቁ ጥያቄ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ እናንተ ለእኔ የመንገር መብት የላችሁም ብለዋቸዋል፡፡
ያሜህ በቀጣዩ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ስልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ ይጠበቁ የነበረ ቢሆንም ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው የአገሪቱ ፍርድ ቤት ያቀረቡትን ቅሬታ ለማዳመጥ ለጃንዋሪ 10 ቀጠሮ ይዟል፡፡
ያሜህ ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ በአገሪቱ አራት ፕሬዘዳንታዊ ምርጫዎችን በማድረግ ተፎካካሪዎቻቸውን ሲያሸንፉ ቢቆዩም ምርጫዎቹ ነጻና ፍትሐዊ እንዳልነበሩ ይነገራል፡፡
በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ጋምቢያዊያን ህይወታቸውን ለማዳን አደገኛ የባህር ላይ ጉዞ በማድረግ ጭምር ወደአውሮፓ አገራት በመሸጋገር የፖለቲካ ጥገኝነት ሲጠይቁ መቆየታቸውም ይታወቃል፡፡
* ፎቶው ያሜህ ድምጽ ለመስጠት ከባለቤታቸው ዘይነብ ጋር ሲያመሩ የተነሱት ነው

No comments:

Post a Comment

wanted officials