Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 19, 2016

በርካታ የዜና ስህተት እንደሰራ የወያኔው ቲቪ አመነ





በርካታ የዜና ስህተት እንደሰራ የወያኔው ቲቪ አመነ

ማስተካከያ!
እንደሚታወቀው በዚህ ሰሞን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመዋቅር ማሻሻያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት ሲያጠና የቆየውን የመዋቅር ማሻሻያ ጥናት ይፋ ያደረገ ሲሆን በከተማው አመራር እና የዘርፉ ባለሙያዎች የ2 ቀን ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በዚህ ውይይት ላይ በጥናቱ ሊካተቱ የሚገባቸው ሊስተካከሉ የሚገባቸው ወይም እንዳሉ ቢቀጥሉ የተባሉ ሃሳቦች በስፋት ተነስተው ቤቱም አስተያየት ሰጥቶባቸው በቀጣይ እየታየ እንደሚሄድ ከመድረክ ማረጋገጫም አግኝቷል፡፡
ይህንን ጥናታዊ ፅሁፍ አስመልክቶ በቦታው ተገኝቶ የነበረው ኢቢሲ ታህሳስ 9፣ 2009 የተላለፈው ዜና ግን ስህተቶች ያሉበት እና አንባቢያንን የሚያዛቡ በመሆኑ በመሆኑ ለአንባቢዎቻችን ማስተካከያ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡
ማስተካከያ ሚያስፈልገው ነጥብ


1ኛ በዜናው ላይ መሪ እቅድ ተብሎ የቀረበው ሃሳብ ሲሆን ውይይት የተካሄደበት “መሪ እቅድ’’ሳይሆን ገና በሂደት ላይ ያለ ረቂቅ ጥናት ነው።
2ኛ በዜናው ላይ ያለቀለት ሰንድ ተደርጎ የቀረበው ሃሳብ ሲሆን ሰነዱ በፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ተዘጋጅቶ ቀረበ እንጂ የከተማው አስተዳደር እንዳለቀለት ሰነድ አልተረከበውም፡፡ በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የአደረጃጀት መዋቅር ፍኖተ ካርታ አጠናቀቀ የሚለው የተሳሳተ አገላለፅ ነው!

3ኛ ሌላው ሃሳብ ክ/ከተሞች ከተማ ይሆናሉ የተባለው ዜና ሲሆን ለውይይት በቀረበው ሰነድ ላይ በአንድ ቦታ እንኳን ክፍለ ከተሞች የከተማ አደረጃጀት ይኖራቸዋል የሚል የውሳኔ ሃሳብ የለም!

4ኛ ቢሮዎች ወደ ኮርፖሬሽኖ ይቀየራሉ የሚለው ዜናው ፡- በጥናቱ ቢሮዎች ከስመው አደረጃጀቱ በኮርፖሬሽን ይሆናል አይልም። የተባለው በጥናቱ መሰረት ሁለት መንግስታዊ አካላት ይኖራሉ እነሱም ፖለቲካል ኤክስኩቲቭና የአስተዳደር ኤክስኩቲቭ ናቸው። በፖለቲካ ኤክስኩቲቭ ተዋረድ ቢሮዎች ይኖራሉ በአስተዳደር አክስኩቲቭ ክንፍ ደግሞ እንደየባህሪያቸው ኮርፖሬሽን፣ባለስልጣን፣ ኤጄንሲ ይኖራሉ ይላል ረቂቅ ጥናቱ።

5ኛ ከሁሉም በላይ ግን ጥናቱ በቀጣይ ብዙ ውይይቶችና ማሻሻያዎች የሚደረግበት እንጂ እንዳለቀለትና በቅርብ ተግባራዊ የሚደረግ አይነት አድርጎ የቀረበውም ሂደት የተሳሳተና የታሳሳተ አቀራረብ መሆኑን ለተመልካቾቻችን ግልፅ እንዲሆን እንወዳለን!
የዚህ ፍኖተ ካርታ ረቂቅ ወደፊት እየታየ ውይይት እየተደረገበት የሚዳብር መነሻ ሰነድ መሆኑ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡
EBC

No comments:

Post a Comment

wanted officials