Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 26, 2016

የአርበኛ ጎቤ መልኬ ጦር የወያኔን ጦር ዳግም ቀጣ – የወያኔ ጦር በ6 መኪና ተጭኖ ከሁመራ ወደ መተማ አቅጣጫ እያመራ ነው




(ዘ-ሐበሻ) በአርበኛ ጎቤ መልኬ የሚመራው ጦር በትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ መቀጠሉ ተሰማ::
ከትናንት በስቲያ በሕወሓት ወታደሮች ተከቦ የነበረው የአርበኛ ጎቤ ጦር በሕወሓት ወታደሮች ላይ የበላይነቱን ወስዶ ከከባበው ከወጣ በኋላ ትናንትናም የሕወሓት ጦር ኃይሉን አጠናክሮ ወደ የጎቤን የሕዝብ ጦር ሊያጠቃ ሞክሮ በድጋሚ ሽንፈትን ተከናንቦ ተመልሷል::

በዛሬው ዕለትም እንዲሁ የሕወሓት ጦር በጎቤ ኃይል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቢሞክርም እንደገና መቀጣቱን እና የጎቤም ጦር በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የተሰራጨው መረጃ አመልክቷል::

በሌላ በኩል አክቲቭስት ሙሉነህ ዮሐንስ “በዛሬው እለት ከሁመራ የተነሱ በ6 መኪና የሞሉ የወያኔ ወታደር ወደመተማ አቅጣጫ እያመሩ ነው። ስናር ላይ መድረሳቸው ታውቋልና በመተማ ቋራና አካባቢው ዝግጅት እንዲደረግ መልእክት ይተላለፍ” ሲል ጥሪውን አቅርቧል::

አክቲቭስቱ ጨምሮም “ጎንደር ላይ በየአቅጣጫው የተወጠረው ወያኔ ያለ እረፍት የወታደር እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። የመኸር ስራውን በጥድፊያ የተያያዘውን ገበሬ እጅግ የፈራው ወያኔ የተደገሰለትን ለማደናቀፍ ሲል አስቀድሞ በየቦታው ጦርነት እያስነሳ ይገኛል። ወያኔ የፈራውን እንደማያመልጠው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት በሙሉ ልብ ይናገራሉ።” ሲል ያለውን መረጃ ለሕዝብ አካፍሏል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials