ዶ/ር መረራ በድብቅ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ወያኔ የኦሮሚያ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ሊቀ መንበር ዶ/ር መረራ ጉዲናን በድብቅ ፍርድ ቤት ማቅረቡን የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ በዛሬው ዜናው እንደሚከተለው ዘገበ።
የወያኔ የፀጥታ ኃይሎች ዶ/ር መረራ ጉዲናን ትናንት ህዳር 22, 2009 ጊዎርጊስ ፌደራል ፍርድ ቤት ያቀረቡት ቢሮዎች ከተዘጉና ሌሎች ሰራተኞች ከወጡ በኋላ መሆኑ ታዉቋል። ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 20 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል።
የዶ/ር መረራ ጉዲና ቤተሰቦች ዛሬ ጧት ቁርስ የወሰዱላቸዉ ቢሆንም የወያኔ የፀጥታ ኃይሎች ምግቡን አንቀበልም በማለታቸዉ ምግቡን ይዘዉ ለመመለስ ተገደዋል። ዶ/ር መረራ ጉዲና የስኳር በሽታ እንዳለባቸዉ የገለጹት የዶክተሩ ቤተሰቦች የወያኔ የፀጥታ ኃይሎች ምግብ አንቀበልም ማለታቸዉ ዶ/ር መረራ ወይ ታሟል ወይም በፀጥታ ኃይሎች ተሰዉሯል በማለት ትልቅ ስጋት ፈጥሮባቸዋል።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ከመታሰራቸዉ በፊትና ከታሰሩም በኋላ የመኖሪያ ቤታቸዉ በ33 የፀጥታ ኃይሎች መኪና ተከቦ እንደነበር የዐይን እማኞች አረጋግጠዋል።
ዶ/ር መረራ ጉዲና በአሳተሙት መጽሐፍ ሺያጭ ያገኙት ገቢና ሌሎች ንብረቶች በወያኔ የፀጥታ ኃይሎች መዘረፉን ታማኝ ምንጮች አረጋግጠዋል።
በአምቦ ከተማ የሚገኙ ት/ቤቶችም ቀደም ብለዉ ተዘግተዋል። እንዲዘጉም የተደረገበትም ምክንያት የዶክተሩ ትውልድ አካባቢ በመሆኑ ተቃውሞ ይነሳል በሚል ስጋት እንደሆነ ይገመታል።![](https://scontent-frt3-1.xx.fbcdn.net/v/t34.0-12/15356984_683232081842125_1211691950_n.jpg?oh=7801b31ea42a43eff8e428a5911670b6&oe=58487B40)
![](https://scontent-frt3-1.xx.fbcdn.net/v/t34.0-12/15356984_683232081842125_1211691950_n.jpg?oh=7801b31ea42a43eff8e428a5911670b6&oe=58487B40)
No comments:
Post a Comment