በአማራ ክልል በተለይም በጎንደር እና በጎጃም እየተደረገ ያለው ሕዝባዊ አመጽ በተቀጣጠለበት በዚህ ወቅት የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት የክልሉን ጸጥታና አስተዳደራዊ ዘርፍ ዋና ኃላፊን ከስልጣን አንስቶ አባረራቸው::
እንደ ምንጮች ገለጻ ከሆነ ለሕወሓት መንግስት ታማኝ ናቸው ተብለው በተደጋጋሚ ይነገርላቸው የነበሩት አቶ ደሴ ዓለሜ በአማራ ክልል ከተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ ስልጣናቸውን አጥተዋል::
በአሁኑ ወቅት ካለምንም ሥራ ቤት ቁጭ ብለው የሚገኙት አቶ ደሴ ዓለሜ በቁም እስር ላይ እንደሆኑም ምንጮቻችን ዘግበዋል::
የሕወሓት መንግስት የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በተደጋጋሚ ከልጣናቸው ለማንሳት ሞክሮ የነበረ ቢሆን ሕዝብ ይነሳብኛል በሚል ሃሳቡን ሲቀያይር ቆይቷል:: በተለይም አቶ ገዱን የአርበኞች ግንቦት 7 ተላላኪ ነው እያሉ የሕወሓት ሚዲያዎች በአደባባይ እስከመተቸት የደረሱበት ሁኔታ ተስተውሏል::

No comments:
Post a Comment