Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, November 30, 2016

“መነኵሴ ነበርኩ” ባዩ ፓስተር ናትናኤል ታዬ: በቅሠጣ ተግባር በቁጥጥር ሥር ዋለ! በማጭበርበር ወንጀል የክሥ አቤቱታ ቀርቦበታል

“መነኵሴ ነበርኩ” ባዩ ፓስተር ናትናኤል ታዬ: በቅሠጣ ተግባር በቁጥጥር ሥር ዋለ! በማጭበርበር ወንጀል የክሥ አቤቱታ ቀርቦበታል


  • ግቢ ጉባኤያት በኩል፣ በማኅበረ ቅዱሳን መዋቅር ሰርጎ የመግባት ዓቅዱ ተጋልጧል፤
  • በአብነት ት/ቤቶች ርዳታ ስም፣ ‘ጳጳሳትንና ቴዎሎጂያንን የመቅረፅ’ ውጥኑን ገልጿል፤
  • ገዳማዊነትን በማጥላላት፣ ምንኵስናን በፈቃዱ ትቶ ወደ መናፍቃን የከዳ ኮብላይ ነው!
  • ለቅሠጣ ተግባሩ፣ የቤተ ክህነቱን አስተዳደራዊ ክፍተት እንደሚጠቀም ግልጽ አድርጓል፤
  • እንደ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶዎች፣ ‘ቸርች’ አቋቁሞ ተልእኳቸውን እያስፈጸመ ይገኛል፤
*                     *                     *
pastor-natnael-taye-arrested

ሐራ ዘተዋሕዶ

ሥርዓተ ምንኵስናንና ገዳማዊ ሕይወትን በመሠቀቅና በማጥላላት፣ ምንኵስናውን በገዛ ፈቃዱ ትቶ ወደ መናፍቃን አዳራሽ ከኮበለለ በኋላ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያንን ተልእኮ ለማስፈጸም የተሠማራው ፓስተር ናትናኤል ታዬ፤በአንድ የቤተ ክርስቲያናችን ዐጸደ ሕፃናት ውስጥ በቅሠጣ ተግባር ላይ ሳለ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ፡፡
የቀድሞው ‘አባ’ ነኝ ባይ የዛሬው ‘መጋቢ’ ናትናኤል ታዬ፤ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ከቀትር በኋላ፣ በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ብርሃን ማዕከል በሚያስተዳድረው የአቡነ ጎርጎርዮስ ዐጸደ ሕፃናት ቅጽር ውስጥ፣ የግእዝ ትምህርት በመከታተል ላይ የነበሩ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን ሲቀሥጥ ተይዞ በከተማው ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጧል፡፡
ቀሣጢው ፓስተር ናትናኤል ታዬ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ታስሮ ጥያቄ እየተደረገለት ሲኾን፤ የማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ብርሃን ብርሃን ማዕከል ጽ/ቤትም ትላንት ሰኞ ለወንጀል ምርመራ ክፍሉ የክሥ አቤቱታእንዳቀረበበት ተጠቅሷል፡፡
ያለፈቃድ ወደ ዐጸደ ሕፃናቱ ግቢ ገብቶ ሕገ ወጥ የምስል ቀረፃ በማካሔድ ግቢ በመድፈር፤ የሃይማኖቱ ተከታይ ሳይኾን እንደኾነ በማስመሰል ቤተ ክርስቲያኒቱን በማጥላላት፤ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሳይላክ እንደተላከ በማስመሰል የሐሰት ውክልናን መጠቀም የሚሉ የወንጀል አድራጎቶች በአቤቱታው መካተታቸው ተመልክቷል፡፡
ግለሰቡ በተጠቀሰው ዕለትና ሰዓት፣ ማዕከሉ ከሚያስተባብረው የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ጋር የተገናኘው የዐጸደ ሕፃናቱን ክፍሎችና ዙሪያውን በቪዲዮ ካሜራ ሲቀርፅና ፎቶ ሲያነሣ ከቆየ በኋላ ነው፡፡ በሰዓቱ የግእዝ ትምህርት በመማር ላይ የነበሩት የኮሌጅና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹ፣ ስለ ማንነቱ የሚያውቁት ነገር ካለመኖሩም በላይ፣ ወደ ግቢው ለመግባትና ቀረፃውን ለማካሔድ የሚያስችል አንዳችም ዕውቅና እና ፈቃድ አልነበረውም፡፡
ይህም ኾኖ ናትናኤል ታዬ ራሱን ለተማሪዎቹ ያስተዋወቀው፣ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ እንደተላከ አድርጎ ሲኾን፤ የአብነት ትምህርት ቤቶችን የመርዳት ፍላጎት እንዳለውም ገልጾላቸዋል፡፡ “አኹን አብነት ተማሪዎችን መርዳትና ማጠናከር የሚያስፈልግበት ወቅት ነው፤” ያለው ናቲ፣ ከዚኹ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ውጭ ሳይቀር መጓዙንም ነግሯቸዋል፤ ዓላማውንም ሲያስረዳ፡- “በደንብ ቀርፀን እናወጣችኋለን፤ ከእናንተ ጳጳስ፣ የቴዎሎጂ ተማሪ[ቴዎሎጅያንን] ማውጣት እንፈልጋለን፤ ለዚያ ነው የመጣኹት፤”በማለት ነው ያብራራላቸው፡፡
ከዚኹ ጋር በተገናኘ መረጃ እንደሚያስፈልገው የተናገረው ናትናኤል፣ “ቤተ ክህነት ላይ ሔጄ ብጠይቃቸው የመልካም አስተዳደር ችግር ስላለባቸው መረጃውን በአግባቡ አይሰጡኝም፤ በቀጥታ መረጃውን ማግኘት የምንችለው ከናንተ ነው፤”በማለት የመምጣቱን ምክንያት አስቀምጧል፡፡ በዚኹም ሳያበቃ፣ “ቤተ ክርስቲያኒቱ ወድቃለች፤ በአኹኑ ሰዓት እጅግ ብዙ ችግር ነው ያለባት፤” የሚሉ የማጥላላት ንግግሮች ማከሉ ተጠቅሷል፡፡
pastor-natnael-taye-arrested

ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ተልኬ ነው የመጣኹት እያለና በተጠቀማቸው የማጥላላት ንግግሮች የተጠራጠሩት ተማሪዎቹም፣ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ የተጻፈለት ደብዳቤ እንዳለ ሲጠይቁት፣ “አይ፣ ደብዳቤ አልያዝኩም” ይላቸዋል፡፡ ደብዳቤ ካልያዘ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ እንዲያሳይ ጫን አድርገው ይጠይቁታል፡፡ የቀሣጢው ማንነትም ለተማሪዎቹ የታወቀው ይህን ጊዜ ነበር – “እስቲ የተጻፈልህን ደብዳቤ ሲባል፣ አይ፥ ደብዳቤ አልያዝኩም አለ፤ መታወቂያኽን ሲባል መታወቂያውን ሲያወጣ፣ ስም፡- አቶ ናትናኤል ታዬ፤ ሥራ፡- ፓስተር ይላል፡፡ ወዲያው ፖሊስ ተጠራና ጉዳዩን ካወቀ በኋላ በቁጥጥር ሥር ውሎ ወዲያው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፤” ብለዋል ስለ ኹኔታው የተናገሩ የዓይን እማኞች፡፡
ናትናኤል በፖሊስ ከተያዘ በኋላ ስለሚከተለው እምነት ሲጠየቅ፣ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ እንደኾነና ከአኹን በፊት ግን‘ኦርቶዶክስ እንደነበረ’ ነው ምላሽ የሰጠው – “ኦርቶዶክስ ነበርኩ፤ አኹን ፕሮቴስታንት ኾኛለኁ፤ አኹን ሃይማኖቴ ፕሮቴስንታንት ነው::” ናትናኤል ታዩን ቀሣጢ የሚያሰኘውና የሚያደርገው፤ በራሱ አንደበት እንደነገረን፥ በእምነቱ ፕሮቴስታንት ኾኖ ሳለ ከቤተ ክህነቱ እንደተላከ በማስመሰል በርዳታ ስም ሰርጎ ገብቶ የመናፍቃኑን የጥፋት ተልእኮ ለማሳካት መንቀሳቀሱና በግሉም ለመጠቀም ማሰቡ ነው፡፡
pastor-natnael-taye-arrested04ግለሰቡ በአንድ ወቅት፣ ‘ትሪኒቲ’ ለተሰኘ ፕሮቴስታንታዊ መጽሔት በሰጠው ቃለ መጠየቅ፤ “ዐማኑኤል ኅብረት”የተሰኘና ሜክሲኮ አካባቢ የሚገኝ ፕሮቴስታንታዊ ማኅበር አባል መኾኑን እንዲኹም፤ ክራይስት ኢንተርናሽናል ዎርሺፕ ሴንተር (Christ International Worship Center)በሚል መጠሪያ የሚኒስትሪ ፈቃድ አውጥቶ “በአምልኮና ወንጌል ሥርጭት ዙሪያ” እየሠራ እንዳለ ተናግሮ ነበር፡፡
ኦርቶዶክሳዊነቱን ክዶ ወደ መናፍቃን አዳራሽ የኮበለለበት ኹኔታም ዴማሳዊ እንደነበር፣ ‘አባ’ ናቲ እየተባለ በተጠራበት በዚያው ቃለ መጠየቅ ግልጽ አድርጓል፡፡ ደጋጎቹ አባቶቻችን፣ ፍትወታት እኵያትን በማሸነፍ ከነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ የደረሱበትን ሥርዓተ ምንኵናና ገዳማዊ ሕይወት ለማጥላላት ቢሞክርም ሆዱ ስለበለጠውና ለዓለማዊ ምቾት ስለተሸንፈ ነበር፣ በገዛ ፈቃዱ የተዋት፡፡
pastor-nati-on-trinity-mag
ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያን የሚፈለፍሏቸውን የእፉኝት ልጆች የኾኑ የኑፋቄ ማኅበራት ፈለግ በመከተል የራሱን ‘ቸርች’አቋቁሞ ለቅሠጣ የተንቀሳቀሰው ናትናኤል፣ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ዐጸደ ሕፃናት የመጣበት ኹኔታ፤ ዋነኞቹ የኑፋቄው አዝማቾች በአኹኑ ወቅት እየተከተሉት ያለውን ስልት እንደሚያሳይ ተጠቁሟል፡፡
“የቤተ ክህነቱን ጉዳይ ጨርሰናል፤ በኹሉም መዋቅር ውስጥ ገብተናል፤ የቀረን በማኅበረ ቅዱሳን መዋቅር ውስጥ መግባት ነው፤” እያሉ የሚለፍፉ ሲኾን፤ ለሰርጎ ገብነቱም የትኩረት ቦታ ያደረጉት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተደራጀ መልኩ የሚማሩባቸውን ግቢ ጉባኤያትን ነው፤ ተብሏል፡፡ በአብነት ትምህርት ከሚሳተፉትም፣ ወደ መንፈሳውያን ኮሌጆች የሚገቡትንና በምንኵስና ካሉትም ለጵጵስና ሢመት የሚታጩትን በመመልመል በአምሳላቸው የመቅረፅ ውጥን እንዳላቸው ከቀሣጢው ናትናኤል ተልእኮ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
mahibere-kidusan-logo
የማኅበረ ቅዱሳን ዶክመንቴሽን ክፍል፣ “የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከትላንት እስከ ዛሬ” በሚል ርእስ በሚያዝያ ወር 2003 ዓ.ም. ባወጣው ኅትመት፣ ቤተ ክርስቲያናችንን በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠርና ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ ትኩረት ያደረጉባቸው ስትራተጅያዊ ቦታዎች፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የአብነት ት/ቤቶች እና ገዳማት እንደኾኑ ዘርዝሯል፡፡
በእኒኽም ወስጥና ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያን ባለፉት ዐሥር ዓመታት፣ “ከጓዳ ወደ ሜዳ፤ ከኅቡእነት ወደ ግልጽነት፤ ከግለሰብ ወደ ማኅበር፤ ከድርጅት ወደ ድርጅቶች” መበራከታቸውን ገልጿል፡፡ የኑፋቄአቸው ሤራና አደጋ እንዳይነቃበትም፣ ማኅበረ ቅዱሳን የፈጠረው እንጂ በእውን የሌለ አጀንዳ እንደኾነ አድርገው ሲያዘናጉ መቆየታቸውን፤ ጉዳዩን አስመልክቶ የሚቀርቡ ማስረጃዎችንና ማጋለጦችንም የግለሰቦችና የማኅበራት ጠብ በማስመሰል ውስጥ ውስጡን ብዙ ለመሥራት እንደተጠቀሙበት አትቷል፡፡
ይኹንና በተጠቀሱት ተቋማት ያሉ ቀናዕያን አገልጋዮችና ምእመናን ባካሔዱት ተጋድሎና የቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር፤ የኑፋቄው አካሔድ ውስጥ ውስጡን እየጎዳን ያለና በአስቸኳይ ካልተቀለበሰም የህልውና ስጋት መኾኑን በመገንዘብ ዐበይት ሲኖዶሳዊ ውሳኔዎችን አሳልፏል፤ በውሳኔዎቹ ላይ ተመሥርቶ በተደረገው የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ፣ የኑፋቄ ማኅበራቱ ባተኮሩባቸው ተቋማትና በአህጉረ ስብከት የማይናቁ ውጤቶች እየተመዘገቡ እንዳለ ይታወቃል፡፡
የአኹኑ የናትናኤል ታዬና የመሰሎቹ አካሔድ፣ በፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ተጋድሎው የቤተ ክርስቲያናችን አንዱ ኀያል አቅም በኾነው ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥም ገብተናል ብሎ ለማሳየት የተደረገ መቃጣት ነው፡፡ የማኅበሩ መርበብ ይህንኑ ዓቅዳቸውን በቀላሉ ሊያከሽፈው እንደሚችል የሚጠበቅ ቢኾንም፤ ጥንተ መሠረቱ ለኾነውና ተረካቢ ትውልድ ለሚያወጣባቸው ግቢ ጉባኤያት ግን፣ በስትራተጅያዊ ዕቅዱ መሠረት ኹለንተናዊ ክትትሉንና ድጋፉን ሊያጠናክር እንደሚገባ የሚጠቁም ነው፡፡
ከዚኽም ባሻገር ናትናኤል ታዬ የሚቀሥጠው፥ የቤተ ክርስቲያናችንን አልባሳት እንዲኹም መቋሚያ፣ ከበሮ፣ ጸናጽል የመሳሰሉትን ንዋያተ ማሕሌት በመጠቀም ጭምር እንደኾነ ባወጣው ቪሲዲ ታይቷል፡፡ የራሳቸውን ያልኾነውን የራሳቸው በማስመሰል የሚጠቀሙ የእምነት ተቋማት መኖራቸውን የሚያረጋግጥ በመኾኑ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በጥቅምት 2008 ዓ.ም. ምልዓተ ጉባኤው፣ በጉዳዩ ሰፊ ጥናት ቀርቦ

ፕ/ር መረራ ጉዲና ታፍነዋል


ክንፉ አሰፋ
30 ኖቬምበር 2016 – የመድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ ረቡእ ማምሻውን በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
Dr.-Merara-Gudina
በዛሬው እለትፕ/ር መረራ ጉዲና መኖርያ ቤት በደህንነቶች እና ከባድ መሳርያ በጣጠቁ የአጋዚ አባላት ተከብቦ መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ብእር ብቻ ለያዘ አንድ ሰላማዊ ሰው ይህን ሁሉ ሃይል ማሰማራት ስር ዓቱ ምን ያህል እንደተብረከረከ የሚያሳይ መሁኑን እማኞቹ ጨምረው ገልጸዋል።
በአውሮፓ ህብረት ጥሪ ተደርጎላቸው ሃገሪቱ ስላለችበት መስቀለኛ መንገድ ገለጻ አድርገዋል። ከዚያም በሆላንድ፣ በጀርመን እና በስዊዘርላንድ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ስለ ሃገሪቱ ሁነታ መወያየታቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ችግር በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ያገኛል ብለው በምርጫ እና በሰላማዊ አግባብ ሲታገሉ የነበሩት ፕ/ር መረራ ጉዲና ለምን እንደታፈኑ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። ከዶ/ር ብርሃኑ ጋር በአውሮፓ ህብረት ተጋብዘው መገኘታቸው ወንጀል መሆኑን የገዥው ፓርቲ ልሳኖች ሲያረግቡት እንደነበር አይዘነጋም።

Äthiopien muss die Menschenrechte respektieren !

Äthiopien muss die Menschenrechte respektieren !

Äthiopien muss die Menschenrechte respektieren, fordert die EU-Abgeordnete Barbara Lochbihler im DW-Interview.
Äthiopien wird seit Jahrzehnten von autoritären Regimen geführt. In den vergangenen Jahren hat das ostafrikanische Land einen beeindruckenden Wirtschaftsaufschwung erlebt. Doch mit Hilfe eines umstrittenen Anti-Terrorgesetzes werden Oppositionelle mundtot gemacht oder verhaftet. Seit einigen Jahren dürfen äthiopische Nichtregierungsorganisationen (NGO) nicht mehr aus dem Ausland finanziert werden. Rund ein Drittel der etwa 3.000 registrierten NGOs hätten ihre Arbeit inzwischen einstellen müssen, sagt die EU-Abgeordnete Barbara Lochbihler (Bündnis 90/Die Grünen) am letzten Tag ihres viertägigen Aufenthalts (14.-17.07.2013) in Äthiopien mit einer Delegation des Menschrechtsausschusses des EU-Parlaments.
DW: Sie haben in Addis Abeba mit äthiopischen Regierungsvertretern gesprochen. Was waren die wichtigsten Themen?
Barbara Lochbihler: Wir sehen in Äthiopien Fortschritte bei sozialen, wirtschaftlichen und kulturellen Themen, etwa beim Recht auf Bildung. Aber es gibt auch eine andere Seite dieses Fortschritts: Nichtregierungsorganisationen in den Bereichen Entwicklung, Menschenrechte oder Frauenrechte leiden unter einem Gesetz, das so streng ist, dass sie ihre Arbeit nicht fortsetzen können. Wir haben die äthiopischen Regierungsvertreter aufgefordert, das zu ändern. Wir haben auch mit dem Beauftragten für Menschenrechte gesprochen, der zwar aktiv ist, dessen Unabhängigkeit wir aber anzweifeln. Die Pressefreiheit haben wir ebenfalls auf den Tisch gebracht. Für unabhängige Journalisten ist es wirklich schwierig, kritisch über die Regierungspolitik zu berichten. Kritisiert haben wir außerdem das gezielte Stören von Radioprogrammen durch Störfrequenzen, das dazu führt, dass Radiosender – wie etwa die Deutsche Welle – nicht permanent in der lokalen Sprache senden können. Thema war auch das Anti-Terrorgesetz: Es wird so vage ausgelegt, dass viele Menschen verhaftet werden oder sogar ins Gefängnis kommen. Daher sehen wir ganz klar die Notwendigkeit, dass die Unabhängigkeit der Justiz gestärkt werden muss.
Wie haben die äthiopischen Gastgeber auf Ihre Kritik reagiert?
Sie haben auf die Verfassung verwiesen – die ist ja auch sehr gut. Wir sind uns allerdings uneins bei der konkreten Umsetzung. Bei dem NGO-Gesetz zu Beispiel, heißt es von offizieller Seite, es handle sich nicht um echte NGOs, sondern um Gruppierungen, die mit radikalen Elementen in der Gesellschaft in Verbindung stünden.
Haben Sie auch mit zivilgesellschaftlichen Organisationen gesprochen?
Wir haben sehr viele Vertreter von NGOs getroffen. Sie haben uns ermutigt, weiterhin kritisch auf die Menschrechtslage in Äthiopien zu blicken und sie auf europäischer und internationaler Ebene zu thematisieren.
Nach Medienberichten konnten am Wochenende (13./14.07.2013) im Norden Äthiopiens ungehindert Demonstrationen stattfinden, die eine Oppositionsgruppe organisiert hatte. Glauben Sie, dass sich hier eine Öffnung abzeichnet oder war das nur ein taktischer Schachzug der Behörden?
Demonstrationsrecht ist Teil der Demokratie – und als solche versteht sich Äthiopien ja. Insofern ist das positiv. Aber ich habe auch gehört, dass rund vierzig Mitglieder einer Partei verhaftet wurden, weil sie Flugblätter verteilt hatten. Wir unterstützen natürlich jede Öffnung und jede Verbesserung. Aber als Menschrechtspolitiker schauen wir auch auf solche Menschenrechtsverletzungen und Entwicklungen, die nicht positiv sind. Und die Vertreter von Menschenrechtsorganisationen, mit denen ich gesprochen habe, sagten mir, dass sie immer weiter eingeschränkt werden.
Der Westen will seine Entwicklungshilfe verstärkt an gute Regierungsführung, Pressefreiheit, Rechtsstaatlichkeit und Demokratie knüpfen. Werden die Entwicklungsgelder aus Deutschland und der Europäischen Union weiter wie bisher nach Äthiopien fließen?
Ich hoffe, dass die betroffenen Politiker und Agenturen für Entwicklungshilfe das nicht tun, ohne auf die Situation der Menschenrechte hinzuweisen und vehement Verbesserung einfordern. Man kann nicht sagen, dass diese oder jenes Menschenrecht wichtiger ist. Daher müssen meine Kollegen genauso auch die Reform der Justiz fordern und, dass dieses NGO-Gesetz zurückgenommen oder reformiert wird, so dass die Organisationen ihre Arbeit tun und im Lande selbst Entwicklungsarbeit leisten können.
Barbara Lochbihler ist seit 2009 Abgeordnete des Europäischen Parlaments für die Partei Bündnis 90/Die Grünen in Brüssel und Straßburg. Sie ist Vorsitzende des parlamentarischen Menschenrechtsausschusses. Davor war sie zehn Jahre lang Vorsitzende von Amnesty International Deutschland.
Das Gespräch führte Tekle Yewhala
www.dw.de

ትግሬ ሁሉ ወያኔ አለመሆኑን አሳዩና

አጭር ጠቃሚ ምክር «ሕወሐት ተነካብን፣ የትግራይ ህዝበ ተደፈረ» እያላችሁ ላላችሁ የትግራይ ተወላጆች በተለይ የአረና ፓርቲ አባላት። 
እኔ እናንተን ብሆን ይህን ባገራችን አይተነው ያማናውቅ ዘረኝነት ማን አመጣው ብዬ እጠይቅ ነበር። ወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘርን የፖለቲካ መደራጃ ያደረገ ጊዜና ይህንን ይዞ የበላይነት ለመመስረት ሲሞክር ነው ነገሩ የተበላሸው። የዚህ አደገኛ የጥላቻ ፖለቲካ እናትም አባትም ወያኔና ወያኔ ብቻ መሆኑን መረዳት የመፍትሔው ፍለጋ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። በየትም ቦታ እንዳየነው ማንም ህዝብ በአንድ ሀገር ውስጥ የተለየ ጥቅም ሲያገኝ ሲያይ ወይም ባያገኝም እንኩዋን ሊያገኝ ይችላል የሚል ምክንያት ሲኖረው ይበሽቃል፣ ጥላቻ ያድርበታል። ጥላቻ ደግሞ እንደፍቅርና እንደሌላው ስሜት ሁሉ ሰብዓዊ ስሜት ነው። ሩዋንዳ የተጫረሱት ሰዎች እብዶች ወይም የተለየ ስብዕና ያላቸው ሰዎች አይደሉም። መድሎ ተደረገብን የሚሉ ሰዎች የፈጠሩት ቂምና ጥላቻ ያመጣው አስቀያሚ ጥፋት ነው። ። በኢትዮጵያ ውስጥ ከዘረኝነት ጋር ጠብ ያለው ሁሉ ከወያኔ ራስ ላይ መውረድ አይችልም። አሁን ወያኔ የያዘው አካሄድ ከቀጠለ የበለጠ አደጋ የመጣል ብዬ እፈራለሁ። በተለይ የትግራይ ወገኖቻችን ከባድ ችግር ውስጥ ሲወድቁ ይታየኛል። ይህን ነገር ካሁኑ መፍትሔ ልናበጅለት ይገባል። የትግራይ ተወላጅ የሆነ ሁሉ የወያኔውን መንግስት ከህዝብ አታጣሉን የሚል ዘመቻ መጀመር አለበት።ሌሎቻችንም ማገዝ አለብን።

የአማራ ተጋድሎ ከዚህ ወዴት? ክፍል ሦስት





​(ባለፉት ጊዜያት ክፍል አንድና ሁለት ለአንባቢያን እንዲመች ሆኖ ቀርቧል። ሦስተኛውና የመጨረሻው ክፍል እንሆ፤ ምስጋና በጎንደርና በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ላገዙኝ የአማራ ምሁራን)

ሠ. ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ያለንን ግንኙነት እናሻሽል፤

የሕዝባችን ስም ካለፉት ሥርዓቶች ጋር ተያይዞ የሚነሳው፣ ወይም የአማራ ሕዝብ ባለፉት አገዛዞች እንደተጠቀመ ተደርጎ የሚቀርበው መሠረተ ቢስ ክስ በወያኔና መሰሎቹ ብቻ የሚሰነዘር አይደለም። የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ቢሆን ለአማራ ሕዝብ ያለው አመለካከት በእጅጉ የተበላሸ ነው። በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ስትራቴጂክ ጥቅማቸውን ለማስከበር በሚራኮቱት ምዕራባውያን ኃያላን አገሮች አካባቢ የአማራ ሕዝብ በአክራሪ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት የተፈረጀ ስለሆነ እንዲዳከም ይፈለጋል። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ባለፉት 40 ዓመታት በሕዝባችን ላይ መጠነ ሰፊ ውርጅብኝ ሲደርስ፣ በተለይ ደግሞ ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት በወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ሕዝባችን በማንነቱ ምክንያት ከያለበት ሲፈናቀልና ሲሳደድ፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ የአማራ ልጆች ታፍነው እየተወሰዱ በወያኔ ማሳቀያ ቤቶች (አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባ ቪላ ቤቶች ናቸው) ውስጥ እየተቆለፈባቸው ሰው ይችለዋል የማይባል መከራ ሲቀበሉ፣

ሰውነታቸው ሲተለተልና ከፍተኛ የሆነ የሥነ ልቦና ጠባሳ ሲደርስባቸው፣ ሲገደሉና ደብዛቸው ሲጠፋ የሚገደው አገርም ሆነ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋም አልተገኘም።

በአንድ በኩል ይህ ሁሉ የሚሆነው በእኛ በራሳችንም ድክመት ነው ለማለት ይቻላል። የሕዝባችን መከራ አንገብግቦን አማሮች እንደአማራ ተደራጅተን ባለመንቀሳቀሳችን፣ ብዙ ጥፋት ፈጽመናል። በዘመነ ወያኔ እንደአማራ ሕዝብ የተበደለ፣ እንደአማራ ሕዝብ በጠላትነት የተፈረጀና ስትራቴጂ ተነድፎ እንዲዳከም (በእነሱ አነጋገር አከርካሪቱ እንዲሰበር) የተሠራበት ሕዝብ የለም። ሆኖም ባለመደራጀታችን ምክንያት ይህን በሕዝባችን ላይ ሲፈጸም የቆየውን ጥቃት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማስገንዘብ አልቻልንም። እንደሕዝብ ተደራጅተንና ሁላችንም የሕዝባችን ዲፕሎማቶች ሆነን ተንቀሳቅሰን ቢሆን ኖሮ፣ በማያሰልስ ትግልና ውትወታ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሕዝባችንን በደል እንዲገነዘብ ከማድረግም አልፈን፣ ከኃያላኑ አገሮች ድጋፍ እንኳን ባናገኝ ጠላታችንን ከመደገፍ እንዲቆጠቡ ማድረግ በቻልን ነበር።

የሚያሳዝነው የወልቃይት አማሮች ከ30 ዓመት በላይ ሲገደሉና ሲጮሁ የኖሩ ቢሆንም የወልቃይት ስም በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እንዲነሳ በርካታ ወገኖቻችንን መገበር ነበረብን። አማሮች በሶማሌ ክልል የተለያዩ ቦታዎች፣ በኦሮሚያ ክልል በአርባ ጉጉ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በምዕራብ ወለጋ ወዘተ.፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በደቡብ ክልል በጉራ ፈርዳ፣ በኮንሶ ወዘተ.፣ በአፋር ክልልና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከያለበት እየታደኑ ሲገደሉና ሲሳደዱ የደረሰላቸው ኃይል የለም። በአማሮች ላይ ሲደርስ የቆየውንና አሁንም የቀጠለውን መከራ የሚዘግብ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ሆነ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ተቋም አልተገኘም። ይህም አማሮች እንደሕዝብ ሳንደራጅ ተበትነንና ተዳክመን በመኖራችን ምክንያት የመጣ ችግር ነው። መበተናችን በከፍተኛ አዳክሞናል፤ ለጠላቶቻችን አጋልጦናል። ስለሆነም ካለፉት ስህተቶቻችን ተምረን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ድጋፍ ለማግኘት ከፍተኛ ትግል ማድረግ ይኖርብናል።

ያለንበት የአፍሪካ ቀንድ በዓለም ላይ እጅግ አስቸጋሪ ከሚባሉት ቀጠናዎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ አስቸጋሪ ቀጠና ውስጥ ኃያላን አገሮች ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሽኩቻ ሲያደርጉ እንደቆዩና አሁንም በዚኸው ተግባራቸው እንደቀጠሉ ይታወቃል። በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ አሜሪካና አጋሮቹ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ምክንያት በዚህ ቀጣና ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ በግልጽ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። የወያኔ መንግሥት የእነዚህ ኃያላን አገሮች የጸረ ሽብር ትግል ጉዳይ ፈጻሚ በመሆኑ ከፍተኛ ድጋፍ ሲደረግለት እንደቆየ፣ እነዚህ ኃያላን አገሮችም ቆመንለታል ከሚሉት የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጥበቃ መርሆ ይልቅ ብሔራዊ ጥቅማቸው ስለሚበልጥባቸውና ይህንን ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ደግሞ ከወያኔ የተሻለ አገልጋይ እንገኛለን ብለው ስለማያምኑ፣ ለዚህ ጸረ ሕዝብ ቡደን መጠነ ሰፊ ድጋፍ ሲያደርጉለት ቆይተዋል። ይህ ቡድን የሚፈጽመውን መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት አይተው እንዳላዩ ሲያልፉ እንደቆዩም ተደጋግሞ የታየ እውነታ ነው።

ነጻነታችንን ማረጋገጥ የምንችለው በራሳችን ትግልና መስዋዕትነት መሆኑ የማያጠራጥር ቢሆንም፣ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ድጋፍ እስካላገኘን ድረስ፣ ወይም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለወያኔ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲገታ እስካላደረግን ድረስ የምንከፍለው መስዋዕትነት ከፍተኛ እንደሚሆን ግልጽ ነው። ስለሆነም የሕዝባችን ጥያቄ ፍጹም ፍትሐዊ ጥያቄ መሆኑን፣ የሕዝባችን ትግል ለነጻነት፣ ለእኩልነትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚደረግ ትግል መሆኑን ወዘተ. አበክረን ማስገንዘብና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከሕዝባችን ጎን እንዲቆም ለማድረግ ያለመታከት መታገል ይኖርብናል።

ይህን ትግል በድርጅትም በግልም ደረጃ መፈጸም ይቻላል። በአማራ ሕዝብ ስም የሚንቀሳቀሱ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ የዲፕሎማሲ ሥራና ተዛማጅ ጉዳዮችን የሚሠሩ ክፍሎችን አቋቁመው የኃያላን አገሮችን የፓርላማ አባላትን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣትን፣ ታዋቂ ሰዎችን፣ ምሁራንና ተመራማሪዎችን፣ ጋዜጠኞችንና የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅቶችን ወዘተ. ሳይታክቱ ማስረዳትና ሳያሰልሱ መወትወት ይገባቸዋል። ሥራው በቋሚነትና ያለመታከት የሚሠራ እንጂ ብልጭ ድርግም የሚል የአንድ ሰሞን ሆይ ሆይታ መሆን የለበትም። በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ይህንን ሚና መወጣት ይቻላል። ከዚህ ወሮበላ ቡድን ጋር እየታገለ የሚሞተው ወገናችን በደል አንገብግቦን፣ ሁላችንም የሕዝባችን ዲፕሎማቶች ሆነን መንቀሳቀስ ይኖርብናል፤ እንችላለንም። አንድ የውጭ መገናኛ ብዙሃን የሚሠራው ዘገባ፣ አንድ የታወቀ ምሁር የሚሠራው ጥናታዊ ጽሑፍ፣ አንድ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅት የሚያዘጋጀው ሪፖርት ወዘተ. በጣም ትልቅ ዋጋ አለው። ትግሉ ዘርፈ ብዙ ነውና በዚህም ረገድ ከፍተኛ ሥራ እንድንሠራ ያስፈልጋል።

ረ. በመናበብ እንታገል፤

በጣም በርካታ የአማራ ልጆች ሕዝባችን እንደሕዝብ ተደራጅቶ መብቱን ከማስከበርና ክብሩን ከማስጠበቅ ውጪ ምርጫ የለውም ብለው፣ ሌት ተቀን በአማራ ጉዳይ ላይ እየሠሩና እየታገሉ ነው። የአዲሱ ታሪክ ሠሪ የአማራ ትውልድ አባላት ሕዝባችን በአማራነቱ እንዲደራጅ፣ በአማራ ሕዝብ ስም የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች በጋራ፣ በትብብርና በመናበብ እንዲሠሩ ሳያሰልሱ ይጽፋል፤ ይታገላሉ። በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ስለሚገኘው ፍጅት መረጃዎችን እያሰባሰቡ ለሕዝባቸው ያደርሳሉ፤ የነብሰ ገዳዩን ፋሽስታዊ ቡድን ጽረ አማራ ድርጊት ከሥር ከሥር እየተከታተሉ ያጋልጣሉ፤ ሕዝባችን ሊወስድ ስለሚገባው እርምጃ አቅጣጫ ይጠቁማሉ፤ ከጠላት ጋር ይተናነቃሉ፤ ለአማራ ሕዝብ መስዋዕት እየሆኑ ሕዝባቸውን ነጻ ለማውጣት ሌት ተቀን ከጠላት ጋር ይዋደቃሉ። በእርግጥም ይህ ታሪክ ሠሪ ትውልድ ታሪክ መሥራት ጀምሯል!! በልጆቻችን መካከል ይበልጥ የመቀናጀት፣ ይበልጥ የመናበብና አብሮ የመሥራት ልምድ እንደሚዳብር እና ሕዝባችን የጀመረውን እልህ አስጨራሽ ትግል በድል እንደሚወጣ አንዳችም ጥርጣሬ የለንም። የሕዝባችን ህልውና ለመጠበቅ እንደአማራ ከመደራጀት ውጪ ምንም ዓይነት ምርጫ የለንም። እንደአማራ እናስብ፣ እንደአማራ እንደራጅ፣ ለአማራነት እንሰዋ!!!!

እንደሚታወቀው የትግሉ መሪም አንቀሳቃሽም አገር ቤት ያለው ሕዝብ ነው። የሚሞተውም የሚታሰረውም የቶርቸር ሰለባ የሚሆነውም እሱ ነው። በግልጽ እንደሚታየው ሕዝባችን ከወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ከነብሰ ገዳዩ አጋዚ ጋር እየተዋደቀና ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። ይህ ሕዝብ ሊደገፍና ‹አይዞህ› ሊባል ይገባዋል። የሕዝባችን የስቃይና የመከራ ጊዜ እንዲያጥርና መስዋዕትነቱ እንዲቀንስ ተጋድሎውን ሳያሰልሱ መደገፍ ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ የሕዝባችን ትግል በመደገፍና ልዩ ልዩ አስተዋጽዖ በማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ድርጅቶች በውጪ አገሮች በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። እነዚህ ድርጅቶችና የድርጅቶቹ አባላት የሕዝቡን ተጋድሎ ሌት ተቀን እየደገፉና ትልቅ አስተዋጽዖ እያደረጉ ይገኛሉ።

እንደቤተ አማራ፣ ሞረሽ፣ ዳግማዊ መዐሕድ ወዘተ. ያሉ አማራ ድርጅቶች ይበልጥ እንዲጠናከሩና እንዲጎለብቱ መደገፍ ይገባናል። እነዚህ ድርጅቶች ራሳቸውን በገንዘብና በሰው ኃይል አቅም እንዲያጎለብቱ፣ የጥናትና ምርምር፣ የመረጃና የሕዝብ ግንኙነት፣ የፋይናንስ ወዘተ. ክፍሎች እንዲኖሯቸውና መሠረት ያለው ሥራ መሥራት እንዲችሉ ጠንካራ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል። ከዚህም በላይ የወያኔን ጸረ አማራ አገዛዝ ማስወገድ የሚቻለው በትጥቅ ትግል ጭምር ነውና በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ ታጋይ ድርጅቶችን መደገፍም ያስፈልጋል (ብዙ ወገኖች በአማራ ሕዝብ ስም የሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች እንዲዋሐዱ ተደጋጋሚ ጥሪ እንደሚያቀርቡ ይታወቃል። እነዚህ ወገኖች የአማራ ድርጅቶች እንዲዋሐዱ የሚወተውቱት፣ ድርጅቶች በፋይናንስ፣ በሰው ኃይልና በድርጅታዊ አቅማቸው እንዲጎለብቱ ከመፈለግ እንደሆነ ግልጽ ነው። ሆኖም የአማራ ድርጅቶች እርስ በርሳቸው እየተናበቡና እየተደጋገፉ እስከሠሩ ድረስ፣ ይልቁንም አንዱ ሌላውን ለማጥፋት እስካልሠራ ድረስ የግድ መዋሐድ አለባቸው ማለት አይደለም።

የአማራ ሕዝብ በቁጥር ብዙ ነው፤ የገጠሙን ፈተናዎችም በርካታ ናቸው። ስለሆነም እነዚህን ፈተናዎች ለመወጣት ሁሉም ድርጅቶች ለትልቁ ዓላማ (አማራን ነጻ ለማውጣትና የሥልጣኑ ባለቤት ለማድረግ) እስከሠሩ ድረስ ብዙ ድርጅቶች መኖራቸውና የተለያዩ የትግል ስትራቴጂ መከተላቸው የሚጠበቅና ተፈጥሯዊ ነው። ቁም ነገሩ ሁሉም ለትልቁ ዓላማ መሥራታቸው ነው። አንድ ድርጅትና አንድ ስትራቴጂ የሚለው አካሔድ በብዙ መልኩ ተጨባጭ (realistic) ያልሆነና ከዘመኑ ጋር የማይሔድ ነው። በውስጣችን ያለውን የአመለካከት ብዝሃነት አክብረን ሁላችንም ለትልቁ ዓላማ ከሠራን ውጤታማ የማንሆንበት ምንም ምክንያት የለም። በድርጅቶች መካከል የሚኖር መተባበር አስፈላጊ የሆነውን ያህል ጤናማ ውድድርም መለመድና መደገፍ አለበት። መጥፋት ያለበት ‹መጠፋፋት› ነው። እሱ ነቀርሳ ነው። ከእስራኤል ድርጅቶች እንማር!!!)። ሁሉም አማራ እንደቀደመ ባህሉ ራሱን አስታጥቆ በተፈለገበት ጊዜ እየተጠራ ራሱን እንዲከላከል (በcitizen army መልክ) ለማድረግም ልዩ ልዩ ዘዴዎችን ማዘጋጀት ያስፈልገናል። ሕዝባችን በሕዝባዊ ሠራዊትነት ከታጠቀና ከተደራጀ ከጎያው ውስጥ ያሉትን ምንደኞችም ሆነ ቀንደኛ ጠላቱን ማንኮታኮት ይችላል። ስለሆነም በዚህ ሕዝባችንን በማደራጀትና በማስታጠቅ ረገድም ብዙ ሥራ ይጠብቀናል (በዚህ ረገድ ከሕዝባችን ነባር ባህል በተጨማሪ የእስራኤልንና የታይዋንን ተሞክሮ አካቶ ብዙ መሥራት ይቻላል።)።

እነዚህን ሁሉ ሥራዎች ለመሥራት በአማራ ድርጅቶች ዘንድ መናበብ እንዲኖር ያስፈልጋል። እጅግ በጣም ያስፈልጋል። ሁሉም ርካሽ ለሆነው የግል ዝና ወይም የድርጅት ጥቅም ሳይሆን ለትልቁ ሕዝባዊ ዓላማ፣ ሕዝባችን ከወያኔ ጸረ ሕዝብ አገዛዝ ነጻ ለማውጣትና አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲሔድ ለማስቻል ተቀናጅቶና ተናቦ መሥራት ይኖርበታል። ለግል ዝና ወይም ጠባብ ለሆነ ድርጅታዊ ጥቅም መሯሯጥ በሞቱት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አጥንት ላይ መሳለቅ ነው!!! ርካሽነት ነው!!! በማደግ ላይ ባለው የአማራ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ላይ ውኃ መቸለስና ሕዝብን ለባርነት ማመቻቸት ነውና ጨርሶ አዝማሚያውም መታየት የለበትም!!!

የየድርጅቶቻችን ህልውና ይዘን፣ ነገር ግን በጋራና በተቀናጀ ሁኔታ ለትልቁ ዓላማ መሥራት ይኖርብናል። እንወያይ፤ እንመካከር፤ በጋራ ለጋራ ዓላማ እንሥራ፤ ተቀናጅተንና ተናበን እንታገል። ማግለል፣ መፈራረጅ፣ መቧደን፣ መጠፋፋት፣ ቂመኝነት፣ ሐሜትና አሉባልታ ብዙ የአማራ ልጆችን አስፈጅተው አይወድቁ አወዳደቅ ከወደቁት ከ1960ዎቹ እና ከዚያም በኋላ ከተመሠረቱት ድርጅቶች የመጣ ርካሽ አስተሳሰብ ነውና የዚህ ርካሽ አስተሳሰብ ሰለባ እንዳንሆን ሁልጊዜም እንጠንቀቅ!!!

ወያኔ የብሔረሰብ ደርጅት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት መላ ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ ይህ ነው የማይባል ሀብት ያጋበሰ፣ ግዙፍ የቢዝነስ ኢምፓየር የገነባ፣ የኢትዮጵያን የመከላካያና የጸጥታ ተቋማት ሙሉ በሙሉ በእጁ ያደረገ፣ ከወያኔ ጋር ተጠጋግቶ በአንድ ጀንበር ሀብት ያፈራና ወያኔን ለመጠበቅ የማያመነታ ከበርቴ ቡድን ከጎኑ ያሰለፈ ግፈኛ ቡድን በመሆኑ እንዲህ በቀላሉ ይንኮታኮታል ብለንም አናምንም። ይህ ጸረ ሕዝብ ቡድን የሀብቱና የምቾቱ ምንጭ የሆነውን ሥልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ የተገደሉት፣ የተሰደዱትና በገፍ የታሰሩት ወገኖቻችን፣ እንዲሁም በቅርቡ ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቂ ማስረጃዎች ናቸው። ወደፊትም ቢሆን ሥልጣኑን ለማስጠበቅ ወገኖቻችን ይገድላል፣ ያስራል፣ ያሳድዳል።

ሆኖም እንደ ሕዝብ ከተደራጀን ወያኔን ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ አሽቀንጥረን ጥለን ነጻነታችንን ማወጅ እንደምንችል ደግሞ አንጠራጠርም። በእኛ በኩል የአማራ ሕዝብ የተደቀነበትን የዘር ፍጅት አደጋ ለመቋቋም፣ ነጻነቱን ለማረጋገጥና ከዚያም በኋላ ዘላቂ ጥቅሙን ለማስጠበቅ እንደሕዝብ መደራጀትና መታገል አለበት የሚል የማያወላውል አቋም አለን። ይህ በሕዝብ ደረጃ ተደራጅቶ የመታገልና ዘላቂ ጥቅምን የማስከበር ጥረት ተጀምሮ የሚቆም የአንድ ዘመን እንቅስቃሴና የአንድ ሰሞን የወረት እንቅስቃሴ አይደለም። ‹የአማራ ተጋድሎ እስከ ወያኔ ውድቀት ብቻ የሚዘልቅ ነው፣ ወይም የሕዝባቸን ተጋድሎ ወያኔን በመጣል የሚጠናቀቅ ነው› የሚል ብዥታም ጨርሶ የለንም። ይልቁንም በእኛ እምነት በአማራነት መደራጀታችንም ሆነ የምናደርገው ተጋድሎ ሕዝባችን እስካለ ድረስ የሚቀጥል የማያቋርጥ ሒደት ነው። ወያኔ መውደቁ ለሕዝባችን ትልቅ ድል ቢሆንም፣ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ ከወያኔ ባሻገር የሚሔድ መሆኑ ግን በሚገባ ሊሰመርበት ይገባል። በእኛ እምነት ጠንካራ ድርጅቶች የሚያስፈልጉንም ለዚህ ነው።

በሕዝብ ስም የተቋቋሙት ድርጅቶች ሊዳከሙ፣ ከዚያም አልፎ ተፈጥሯዊ ሞት ሊሞቱ ይችላሉ። ሆኖም ሕዝቡ እስካለ ድረስ አንድ ድርጅት ሲዳከም ወይም ሲሞት፣ ሌሎች በርካታ ድርጅቶች እየተወለዱና እየተጠናከሩ ይቀጥላሉ እንጂ ከዚህ በኋላ ሕዝባችን እንደሕዝብ ሳይደራጅ ተበትኖ የግፈኞች የጥቃት ሰለባ የሚሆንበት ምንም ዓይነት ሁኔታ አይኖርም። ደጋግመን እንደምንለው የአማራ ሕዝብ በወያኔ ከታወጀበት የዘር ፍጅት ጦርነት ራሱን መከላከል የሚችለው እንደሕዝብ ሲደራጅ ብቻ ነው። ከወያኔ መንኮታኮት በኋላ ዘላቂ ጥቅሙን ማስከበር የሚችለውም እንደአማራ ሲደራጅ ነው። አዲሱ የአማራ ትውልድ ይህን መሠረታዊ ሐቅ በሚገባ ተገንዝቦ እየታገለና ውድ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል።

እንደሕዝብ ከተደራጀን ለአማራ ሕዝብ ነጻነት ሲሉ መስዋዕት የሆኑ ወገኖቻችን መስዋዕትነት እንዲሁ መና ሆኖ የሚቀር አይሆንም። ስለሆነም እንደአማራ ተደራጅተን ወገኖቻችን የተነሱለትን ዓላማ ከግቡ ለማድረስ እየተንቀሳቀስን፣ እዚያው በዚያው እነሱ የሚታወሱበትን መንገድም መቀየስ ይኖርብናል። የተሰውትን ወገኖቻችን ማንነትና እንዴት መስዋዕት እንደሆኑ በዝርዝር ሰንዶ መያዝ፣ በስማቸው ልዩ ልዩ ተቋማትን መመሥት፣ ቤተሰቦቻቸው እንዳይበተን ልዩ ልዩ ድጋፍ ማድረግ ወዘተ. ወዘተ. ይገባናል።
ከዚህም በላይ እስካሁን የመጣንበትን የትግል ሒደት፣ በትግላችን ያገኘናቸውን ስኬቶችና ያመለጡንን ዕድሎች በሚገባ መርምረንና ከአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ቃኝተን ልዩ ልዩ የትግል ስትራቴጂዎችን መቀየስ ይገባናል። ብዙ ርቀት የመጣን ቢሆንም አሁንም ገና ብዙ ሥራ እንደሚጠብቀን ተገንዝበን አምርረን መታገል ይጠበቅብናል። እነዚህንና ሌሎች ተግባሮችን ለመወጣት ደግሞ ሁላችንም በጊዜ የለኝም መንፈስ መሥራት እና እርስ በርሳችን መናበብና መደጋገፍ ይኖርብናል። ገዳዮቻችን እኛን ለማጥፋት ሌት ተቀን እየሠሩ ነው። እኛም አጥፊዎቻችን ለማጥፋትና ራሳችንን ከጥፋት ለመታደግ ያለ እረፍት ከመሥራት ውጪ ምርጫ የለንም። እነሱ እያሉ ሰላም አይኖረንምና ከእነዚህ ጸረ አማራ የባንዳ ልጆች ራሳችንን ለመገላገል ሁላችንም (በምንችለው መንገድ ሁሉ) ሌት ተቀን እንታገል። በትግላችን ነጻነታችንን እናረጋግጣለን!!!

ሰ. ቀጣይነት ያለውና ሁሉዐቀፍ የሆነ ትግል እንታገል፤

የተጋረጠብን ፈተና በጣም ግዙፍ ሲሆን፣ የገጠመን ወደረኛም በእጅጉ የተደራጀ ነው። ስለሆነም ከላይ እንደተገለጸው ትግላችን ከወረተኛነት የተላቀቀ፣ ቀጣይነት ያለውና ከሚገጥሙን አገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎች አንጻር እየተቃኘና እየሻሻለ የሚሔድ እንዲሆን ያስፈልጋል። በውሱን ድሎች ረክተን፣ ወይም በአንድ ግጥሚያ (battle) ላይ በሚደርስብን ሽንፈት ተስፋ ቆርጠንና ተሸመድምደን ከዋናው ግባችን የምናፈገፍግ መሆን የለብንም። የአርበኞች አባቶቻችን የተጋድሎ ታሪክ የሚያስተምረን ወረተኝነትንና የአንድ ሰሞን ሆይ ሆይታን ሳይሆን፣ አይቻልም በሚባሉ ፈተናዎች ውስጥ በጽናትና በአይበገሬነት ማለፍን በመሆኑ ሁላችንም (በምንችለው ዘዴ ሁሉ) በጽናት መታገል ይኖርብናል።

በሌላ በኩል ትግላችን በአንድ የትግል ስልት ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ሳይሆን ሁሉዐቀፍ እንዲሆን ያስፈልጋል። ትግላችን በመሬት አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍና በቤት ውስጥ አድማ፣ ሕዝባችን በሚያስገድሉ ወያኔዎችና ምንደኞች ላይ እርምጃ በመውሰድ፣ የወያኔ የአፈና ተቋማት እንዳይሠሩ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ በማሽመድመድ፣ የሕዝባችን በደል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዲያገኝ የዲፕሎማሲ ትግል በማድረግ ወዘተ. ብቻ የሚወሰን አይደለም። ጠንካራ ሕዝባዊ ሠራዊትም ያስፈልገናል። እነዚህ ሁሉ የትግል መስመሮች እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉና የሚመጋገቡ ናቸው። በአንዱ ስልት ብቻ ተንጠልጥለን ሌሎችን ስልቶች ገሸሽ ማድረግ የለብንም። የተራዘመ የትጥቅ ትግል አስበንና በእሱ ላይ ብቻ ተንጠልጥለን ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገን ከተውነው ትልቅ ዋጋ እንከፍላለን። በከተሞቻችን ውስጥ በሚደረግ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ተጋድሎ ላይ ብቻ ከተንጠለጠልንም አሸናፊ መሆን አንችልም። መፍትሔው ቀጣይነት ያለውና ሁሉዐቀፍ የሆነ ትግል መታገል ነው።

#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!!!

The Proof is in the Pudding-Nonviolent Resistance Works

By Olaanaa Abbaaxiiqi
Olaanaabbaaxiiqi@yahoo.com


Nonviolent resistances have led to numerous dramatic changes in many countries around the globe. Understandably, there are also many nonviolent resistances that have failed. I am not claiming that there is a guaranty that all nonviolent resistance will be successful, at least in the short run. There are many scholarly works that studied social movements and the nonviolent means and tried to understand why some are successful while the others fail. Here we are not going into that.
There is a deeply held misconception around many people that nonviolent resistance works only in a benevolent dictatorship or in cases of mild tyranny. Others further argue that nonviolence works only in addressing some civil rights or environment issues and does not work to overthrow a tyrannical government in the face of extreme violence and repression. Those who argue this, conveniently forget stark historical evidence.
In fact some of the most repressive regimes in history fell as a result of nonviolent resistance. Suffice to mention the defeat of Marcos in the Philippines, Pinochet in Chile, the apartheid regime in South Africa, and the communist regime in Poland. And even if we look at recent events, Hosni Mubarak in Egypt and Ben Ali in Tunisia were chased out of power through the nonviolent resistance. None of them were benign.
We can add to the above, the 2005 Lebanon popular movement that ended foreign occupation, and the 2006 Nepal uprising that forced the monarch to make major concession, and the 2000 Serbia, the 2002 Madagascar and the 2003 Georgia nonviolent resistances that led to regime changes. If you look at these examples, one can easily see that nonviolent movements can be successful in less developed, economically poor countries as well as in developed, affluent societies. This means it does not matter whether one is in Europe and North America, or Africa, Asia or elsewhere, or whatever type of regime it is, nonviolent resistance could work everywhere and in every situation. Nonviolent resistance does not need a kinder and gentler ruler in order to prevail.
Erica Chenoweth and Maria Stephan, in their seminal work, “Why Civil Resistance Works”, meticulously and rigorously analyzed 323 violent and non-violent resistance campaigns between 1900 and 2006. Their finding is compelling and provocative. According to their statistical analysis with in-depth case studies of specific countries and territories, campaigns of nonviolent resistance were more than twice as likely to achieve full or partial success compared to violent counterparts. Their groundbreaking findings showed that nonviolent campaigns succeeded 53% of the time versus 26% of the time for violent campaigns.
Thus, based on historical experience alone, there is justification why we should opt for nonviolent resistance over armed struggle.
Why are Nonviolent Struggles More Successful than the Alternatives?
Nonviolent resistance (civil resistance) is preferable due to several reasons. Compared to civil war it is more effective, has a better chance to succeed and also has a better chance to peacefully transitioning to democracy. On the contrary, violent resistance has less chance to succeed, and even when successful, usually results in a dictatorship. Violence begets violence; it is self-perpetuating, and therefore, civil war that relies on violence does not in most cases secure a peaceful end.
Nonviolent resistance method starts from one fundamental assumption: authoritarian regimes survive because they get a wide range of obedience from the population they lord over. Without such obedience there is no way they could continue to rule. Thus, the immediate and cardinal purpose of any resistance should be to bring about the withdrawal or denial of obedience the people have hitherto given to an authoritarian regime.
Compared to violent resistance, nonviolent resistance is better positioned to attract active participation of the people. The very fact that nonviolent resistance has less risk compared to its counterpart makes it a better vehicle for attracting more people. People who because of age, gender and disability cannot participate effectively in violent struggle can easily participate in a nonviolent resistance. Nonviolent resistance can also attract business elites, intellectuals, religious personnel and institution, etc., who for one or reason or another cannot support armed struggle. All these expands the participatory advantage of nonviolent resistance over armed insurrection.
Unlike violent resistance, nonviolent resistance is relatively open to all, it’s not only for able bodied men. People of every walks of life can participate actively in it without leaving their home or work, relatively with less risk to themselves and their families. The same is not true in the case of a civil war. The moment civil war starts, immediately the number of mobilized shrinks. Once the method of struggle shifts, hundreds of thousands of people who used to be actively protesting in the street go back to their home and become aloof. Thereafter, the confrontation, rather than being between the populace and the government, becomes between two armed groups.
The larger the number of participants and the more diverse people are mobilized by a nonviolent resistance, the more chance it has to bring about loyalty shift. The more defection there is, the more undermined and weakened will be the tyrannical regime. And the more it is weakened, the more people dare to defy it further. The high level of mobilization is the most important feature for success. Thus, the participatory advantage of the nonviolence resistance is the key factor in destabilizing the incumbent and giving a chance for the nonviolent resistance to be victorious. Thus, every effort should be done lest we take action that diminishes or minimizes the participation of the people.
It should also be noted that it is this participatory advantage of nonviolent resistance that makes it an excellent conduit to transition to democracy. Evidence clearly shows that struggles that unwaveringly avoid violence have much more chance to bring about democracy. Once they degenerate into violence, their chance of bringing about democracy diminishes. Those who come to power through violence mostly end up turning tyrannical. It should not be forgotten that violence is what brought EPRDF to power, and if we want to break this vicious cycle, violence should not be the way to get rid of it.
Because violent resistance has less chance of mobilizing participants, it also has less chance of bringing about loyalty shift. In fact when there is violence, the police, military and security, rather than shifting their allegiance, dig theirs hills in. If huge defection does not occur, it is always extremely difficult to win an entrenched adversary in power that is controlling all the repressive state machinery.
As nonviolent resistance attracts a large size of participants, and especially when it has reached a certain stage and is diversified, repression against it becomes extremely difficult and costly to the tyrannical government. And when repressive actions are taken in such situations, they could have a boomerang effect. In fact, sometimes, widely publicized repressive incidents are precisely the sparks that trigger mass uprisings. With the continuation of the growth of participants in the nonviolent resistance, the likelihood of division within the government and its institutions, like the police, military, media and bureaucracy becomes certain.
Nonviolent resistance is more advantageous because it could be done relatively on the cheap compared to the violent insurrection. Conducting a protracted insurrection is an extremely expensive undertaking. It is so expensive that most armed struggles that became successful in history had to partly or mostly rely on foreign backers or allies for arms and money. Propaganda aside, it is a rarity for self-reliant armed movement to become successful.
For the Oromo people who do not have external allies, one could easily discern why choosing the nonviolent resistance is a no-brainer. Moreover, because you don’t owe anybody anything when conducing nonviolent resistance, you will not be anybody’s client or stooge and you will not be controlled by an outside force. On the contrary when you rely on foreign forces to conduct armed struggle, the chance of your being controlled and used by them is enhanced.
It should also be noted that armed struggle is not viable in many places. Factors such as having foreign backers, suitable terrain for defense, geo-politics, internal cohesion, having outlet to neighboring countries, and many others are determinative in conducting a successful armed struggle.
Having grievances, just cause and an extremely brutal regime as adversary, does not by itself justify blindly opting for an armed struggle for the sake of it. Before undertaking such a far-reaching scheme, one should first meticulously and seriously take stock of pros and cons and the possibilities of winning and the cost involved in it and then decide. Nothing justifies pursuing and supporting unpractical ideas and myopic strategy that in practice has failed again and again.
In the third and final part we will why the #Oromo Protest should stay the course of Nonviolent Resistance.

Tuesday, November 29, 2016

የአማራ ተጋድሎ ከዚህ ወዴት? ክፍል ሁለት




1. ምን አጣን?

እስካሁን ባካሔድነው ትግል በጣም ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን አጥተናል። የአማራ እናቶች ዳግም ምርር ብለው አዝነዋል፤ አልቅሰዋል። ሕጻናትና ወላድ እናቶች ሳይቀሩ አማራ በመሆናቸው ብቻ ተጨፍጭፈዋል። በሺሕ የሚቆጠሩ የአማራ ልጆች በየአካባቢው በሚገኙ እስር ቤቶችና የማሰቃያ ቤቶች ታጉረው የወያኔ ቶርቸር ሰለባ እየሆኑ ነው። መተማ ውስጥ በርካታ አማሮች በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። እንደበለጠ ንብረቱ ቸኮለ ያሉ ብሩህ አእምሮ ያላቸውና የአማራ ሕዝብ ተስፋ የሆኑ ወንድሞቻችን በአነጣጥሮ ተኳሾች ተገድለዋል። አሁንም በአማራ ክልል በየቀኑ ልጆቻችን ይገደላሉ፤ ይታሰራሉ። ከዚህም አልፎ የአማራ ተጋድሎ ያርበተበተው ወያኔ፣ በአማራና በሌሎች ሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ከአማራ ክልል ውጪ በሚኖሩ አማሮች ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ከፍቶ እያሰቃያቸው ይገኛል።

በአጠቃላይ በዚህ የአማራ ተጋድሎ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን አጥተናል፤ አሁንም ልጆቻችን በየቀኑ እየተነጠቅን ነው። አሁንም የአማራ አርሶ አደር ራሱንና ንብረቱን ለመጠበቅ ከብቶቹን ሸጦ የገዛውን መሣሪያ ለመግፈፍ ብዙ ጥረት እየተደረገና በርካታ አርሶ አደሮች በገፍ እየታሰሩና እየተሰቃዩ ነው። በእኛ በኩል ለሕዝባችን ነጻነት ሲሉ የወደቁትንና አሁንም በየማጎሪያ ቤቱ የሚሰቃዩትን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ዓላማ ከግቡ ሳናደርስ እንቅልፍ እንደማይወስደን ብናውቅም፣ በመገደላቸውና የእነዚህ ዘረኞች የጥቃት ሰለባ በመሆናቸው የደረሰብን ሐዘን መራር ነው!!!

2. ምን እናድርግ?

ሀ. ወያኔ ካልወደቀ ሰላም የለንም!

ወያኔ እያለ ሰላም አናገኝም። ወያኔ ካልወደቀ ሰላም የለንም። ለእኛ ሰላም ማለት ከወያኔ ነጻ መሆን ማለት ነው። ስለሆነም ወያኔን ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሽቀንጥረን ለመጣል ሌት ተቀን ከመታገል ውጪ ምርጫ የለንም። የወያኔና የእኛ ግንኙነት የአጥፊና ጠፊ ግንኙነት ነው። ወይ ያጠፉናል፣ ወይ እናጠፋቸውና ያወጁብንን የዘር ማጥፋት ጦርነት እንቋቋማለን። ከዚህ ውጪ ምርጫ የለም!!! መቼም ቢሆን ከወንድሞቻችንና እህቶቻችን ገዳዮች ጋር ኅብረት አይኖረንም!!!

ስለሆነም እያንዳንዱ የአማራ ልጅ ከእነዚህ ደመኞቻችን ጋር ሒሳቡን ለማወራረድ ያድባ! አምርረን እንጥላቸው! እንጸየፋቸው! ሁላችንም በምንችለው መንገድ እንታገላቸው! የወንድሞቻችን ደም ሳንመልስ እረፍት የለንምና ሁላችንም ወያኔን ለማጥፋት እንትጋ!!! ከወንድሞቹ ገዳዮች ጋር የሚተቃቀፍ ባንዳና ምንደኛ ብቻ ነው። ባንዳነት ደግሞ የአማራ ሕዝብ ዕሴት አይደለም። የወንድሞቻችን ደም ይጮሃል!!!!!

ለ. ከባንዳዎች ጋር ያለንን ሒሳብ እናወራርድ፤

የአማራ ሕዝብ ከወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ጋር የሚያደርገውን ትግል የሚደግፉ በርካታ የብአዴን አባላት አሉ። እነዚህ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ምንም እንኳን ትግሉ የራሳቸው ትግል ቢሆንም፣ ወያኔ ሊያደርስባቸው የሚችለውን መከራ እያወቁ ከሕዝባቸው ጋር በመቆማቸው ሊመሰገኑና ክብር ሊሰጣቸው ይገባል። የእነዚህን የሕዝብ ልጆች ውለታ ሕዝባቸው እንደሚከፍላቸው አንጠራጠርም። በነበረከት ስምዖንና ከበደ ጫኔ የሚመራው የብአዴን ምንደኛ አመራር ከወያኔ የሚሰጠውን ተልዕኮ በመያዝ የሕዝብ ወገንተኝነት የሚያሳዩትን የብአዴን አመራሮች ለመመንጠር ደፋ ቀና እያለ እንደሚገኝ እናውቃለን። ሆኖም ይህ የብአዴን ምንደኛ አመራር ከሕዝቡ ጋር የተቆራረጠ ስለሆነ፣ ለጊዜው በወያኔ ጫንቃ ላይ ታዝሎ እንቡር እንቡር ቢልም በሰፊው የአማራ ሕዝብ ትግል እንክትክቱ እንደሚወጣ ጥርጥር የለንም።

በእኛ በኩል ግንባር ቀደም ጠላታችን ወያኔን እየታገልን፣ እዚያው በዚያው የዚህ ጸረ አማራ ቡደን ተላላኪ ሆነው በሕዝባችን ላይ መጠነ ሰፊ በደል የሚፈጽሙትን ምንደኞችና ባንዳዎችም መመንጠር ይኖርብናል። እነዚህ የሕዝባቸውን ጡት የሚነክሱ የለየላቸው ከሃዲዎች ከጥፋት ድርጊታቸው እንዲመለሱና የሕዝቡን ትግል እንዲቀላቀሉ እንዲመከሩ ከተደረገ በኋላ፣ የሕዝቡን ጥሪ አልሰማም ብለው በጥፋት ተግባራቸው የሚቀጥሉ ከሆነ ጠላት ናቸውና መደምሰስ ይኖርባቸዋል። እነዚህን ተመክረው አልሰማ ያሉ ባንዳዎች ሁሉም አማራ፣ ሴት ወንድ ሳይባል በሚችለው መንገድና መሣሪያ እንዲያስወግዳቸው ያስፈልጋል። ወያኔ ያለነዚህ መንገድ መሪዎች ወደመንደሮቻችን መግባት አይችልም። ስለሆነም እነዚህ የጥፋት ተባባሪዎች እንዲመከሩ፣ ተመክረው የማይሰሙ ከሆነ ደግሞ እንዲደመሰሱ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። ከእነዚህ ጸረ ሕዝቦች ጋር አብሮ መዋል፣ አብሮ መብላትና መጠጣት፣ ከእነሱ ለቅሶ መድረስም ሆኖ ሌላ ማንኛውንም ማኅበራዊ ግንኙነት መመሥረት ከጠላት ጋር መተባበር ስለሆነ ግንኙነታችንም መልክ መያዝ ይገባዋል። ጠላት መጠላት አለበት፤ ከዚያም አልፎ ጠላት ነውና እንዲወገድ ያስፈልጋል።

እነዚህ ባንዳዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ እንደገና የአማራ ልጆችን ለወያኔ አራጆች አሳልፈው ለመስጠት ደፋ ቀና እያሉ ነው። እነዚህ ከንቱዎች የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሁሉንም ነገር የሚያረጋጋውና እነሱም ወደቀደም የምቾት ሕይወታቸው የሚመለሱ ይመስላቸዋል። ሆኖም እነዚህ የታሪክ አተላዎች ከሐቅና ከታሪክ ጋር የሚጋጭ አቋም እንደሚያራምዱ የአማራ ሕዝብ በቅርብ ጊዜ ያስገነዝባቸዋል። የእነዚህ ምንደኞች የምቾት ሕይወት ላይመለስ ተቀብሯል። ለአዲሱ ትንታግ የአማራ ትውልድ ምስጋና ይግባውና እነዚህ ወንድሞቻችንን ለጠላት አሳልፈው የሚሰጡ ምንደኞች ይመነጠራሉ፤ የእጃቸውን ያገኛሉ። በየዕለቱ ማን ምን እንደሚሠራ፣ ማን ታጋይ እንደሆነ፣ ማን የሕዝብ ወዳጅ፣ ማን ጠላት እንደሆነ በሚገባ እየተጣራ ይሰነዳል፤ ጊዜው ሲደርስ በምንደኞች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል።

ሐ. ከአንድነት ኃይሉ ጋር ያለንን ሚና እንለይ፤

በእኛ በአማራ ልጆችና በአማራ ብሔርተኞች ዕይታ፣ የአማራ ሕዝብ በነብሰ ገዳዩ ወያኔ አገዛዝ ሲቀጠቀጥ የኖረው በማንነቱ፣ አማራ በመሆኑ ምክንያት ነው። ስለሆነም ሕዝባችን ከዚህ የወያኔ ጭቆናና ከታወጀበት የዘር ፍጅት ራሱን መከላከል እና ነጻነቱን ማስከበር የሚችለው እንደአማራ ሲደራጅና እንደአማራ ሲታገል ነው የሚል የማያወላውል አቋም አለን። የአንድነት ኃይል ነን የሚሉት ሰዎች ይህን አይፈልጉም። ብዙ አማሮች ሳይቀሩ፣ ሕዝባችን በማንነቱ ተደራጅቶ የተደቀነበትን አደጋ እንዳይቋቋምና ዘላቂ ጥቅሙን እንዳያስከብር አማራ ከተደራጀ ኢትዮጵያ ትበተናለች በሚል ምክንያት ሕዝባችን ለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል በመስዋዕት በግነት ሲያቀርቡት ቆይተዋል። በዚህ ምክንያት ብዙ ዋጋ ከፍለናል።

እነዚህ ወገኖች የአማራን መደራጀት አጥብቀው ይቃወማሉ። ዋናው ምክንያታቸው በአማራ ሕዝብ መስዋዕትነት የኢትዮጵያን አንድነት መጠበቅ ቢሆንም፣ የሚያቀርቡት መከራከሪያ ግን የተለያየ ነው። ‹በአማራነት መደራጀት ጠባብ መሆን ነው፤ የወያኔን አጀንዳ መፈጸም ነው፤ አማራ የሚባል ብሔር የለም› ወዘተረፈ እያሉ ውኃ የማይቋጥር፣ ነገር ግን ሕዝባችንን ትጥቅ የሚያስፈታ አስተያየት ይሰነዝራሉ። እነዚህ አካላት የአማራ ሕዝብ ከያለበት ሲሳደድና ልጆቹን በግፍ ሲነጠቅ ይህ ነው የሚባል እንቅስቀሴና ድጋፍ አድርገው አያውቁም። ነገር ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የአማራን ሕዝብ መደራጀት አጥብቀው ይቃወማሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ ከእነዚህ ወገኖች ጋር የማይታረቅ አቋም አለን።

እነዚህ ወገኖች የአማራን ሕዝብ መደራጀት ከመቃወምም አልፈው የሕዝባቸው ጥቃት አንገብግቧቸው ለአማራ ሕዝብ መደራጀት ሌት ተቀን የሚሠሩ ልጆቻችንን ልዩ ልዩ ስም እየሰጡ ማሸማቀቁን ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል። ይህ ጸረ አማራ አካሔድ መታረም ይኖርበታል። እነሱ ስለኢትዮጵያ አንድነት እንጨነቃለን ይላሉ። እኛም አባቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ስለመሠረቷትና በደማቸው ነጻነቷን ጠብቀው ስላቆዩዋት ኢትዮጵያ ይገደናል። ሆኖም አማራነታችን ይዘን፣ እንደአማራ ተደራጅተን እንጂ እንደከዚህ ቀደሙ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለቱ ለሕዝባችን ያበረከተው ነገር በተናጠል መገደልንና መጨፍጨፍን ብቻ ነው ብለን በጽኑ እናምናለን።

ስለዚህ ከእነዚህ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጋር የጋራ ጠላታችን የሆነውን ወያኔን ለመቅበር መረባረባችን እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሕዝባችን እንዳይደራጅ የሚያደርጉት ቅስቀሳ አውዳሚና ልንታገሰው የማንችለው ጉዳይ ነውና እነሱንም በዚህ ረገድ መታገላችን ተገቢ ነው እንላለን። አማራ በአማራነቱ እንዳይደራጅ የሚቀሰቅስ ማንኛውም ኃይል ትጥቅ አስፈችና ለማንም አላፊ አግዳሚ ኃይል አሳልፎ የሚሰጠን ስለሆነ አንቀበለውም፤ እንታገለዋለን።

እንግዲህ፣ በእኛ በኩል ግንባር ቀደም ጠላታችን ወያኔ መሆኑን አሳምረን እናውቃለን። ሁሉም ኃይል በዚህ የጋራ ጠላት ላይ መረባረብ እንዳለበትም በሚገባ እንገነዘባለን። ሆኖም ወያኔን ለመቅበርም ሆነ ከወያኔ በኋላ የሕዝባችን ጥቅም ማስከበር የምንችለው እንደሕዝብ፣ እንደአማራ ስንደራጅ ነው ብለን በጥብቅ ስለምናምን በዚህ በኩል መሰናክል የሚፈጥሩብንን ወገኖችም አንታገስም። ወያኔን በመቅበሩ ላይ ብቻ እንረባረብ ማለት ያለብን እኛ ብቻ አይደለንም። እነሱም እኛ የቆምንለትን ዓላማ መጎንተሉን ትተው በዚህ የጋራ አጀንዳ ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ያስፈልጋል። በእኛ በኩል የአማራን ሕዝብ ጥቅም እስካስጠበቀ ድረስ ሁልጊዜም ከአንድነት ኃይሉ ጋር ለመሥራት ዝግጁ ነን።

መ. ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ያለንን ሚና እንለይ፤

የአማራ ሕዝብ ለዘመናት ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በአብሮነት ኖሯል። ጸረ አማራ የሆነው የወያኔ ቡድን በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን ሲያስተጋባና ሰነድ አዘጋጅቶ ሲሰብክ እንደኖረው ሳይሆን የአማራ ሕዝብ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ጠብ ኖሮት አያውቅም፤ አሁንም የለውም። ሕዝባችን ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በክፉም በደጉም አብሮ የኖረ ደግ ሕዝብ እንጂ፣ የትኛውንም ዓይነት ጭቆና የማይቀበለው የአማራ ሕዝብ ሌሎችን ሕዝቦች የጨቆነበት ጊዜ እንደሌለ ታሪክ ምስክር ነው። ማንም እንዲጨቁነን የማንፈልገውን ያህል እኛም ማንንም የመጨቆን ዓላማ የለንም፤ ኖሮንም አያውቅም።

እንደሚታወቀው ወያኔ የአማራን ሕዝብ በጨቋኝነት መፈረጅ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦችም ይህንን ጸረ ሕዝብ አስተሳሰብ እንዲቀበሉ በከፍተኛ ደረጃ ቀስቅሶ ቀላል የማይባል ውጤት አግኝቶበታል። ሆደሰፊው ሕዝባችን ግን አሁንም ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አንድነት መገንባት እንደሚፈልግ፣ ለዴሞክራሲና ለሕዝቦች እኩልነት እንደሚታገል እና የሌሎች ሕዝቦች በደል እንደሚያንገበግበው በማያወላውል መልኩ ገልጿል። ሕዝባችን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ሆኖ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚፈልግ በማያሻማ ሁኔታ አሳይቷል።

ይህ ማለት ግን የአማራ ሕዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በሁሉም ጉዳዮች ላይ ይግባባል ማለት አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም። ከሌሎች ሕዝቦች ጋር የሚያግባቡን በጣም ብዙ አጀንዳዎች ያሉትን ያህል በርካታ ልዩነቶች እንዳሉንም እንረዳለን። ሆኖም ልዩነቶቻችን እንደተጠበቁ ሆነው፣ ወይም ልዩነቶቻችንን አክብረን በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ አብረን መሥራት ደግሞ እንችላለን፤ ይገባናልም።

በእኛ በአማራ ልጆች እምነት የሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ነው። እንዳንተባበርና እርስ በርሳችን እንድንጠራጠር የሚያደርገንም ይኸው አናሳ የወያኔ ቡድን ነው። ስለሆነም ይህን የሁላችንም ጠላት የሆነ ጸረ ሕዝብ ኃይል ለማንኮታኮት፣ ከላይ እንደተገለጸው ልዩነቶቻችን እንደተጠበቁ ሆነው በሚያስተሳስሩን በርካታ ጉዳዮች ላይ አተኩረን መሥራት እንችላለን፤ ይገባናልም። ሕዝባችን ለዚህ ሁልጊዜም ዝግጁ ነው።

#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!!!

Monday, November 28, 2016

Ethiopian National Movement Public Meeting in Munich, Germany

የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር መሪ አቶ ሌንጮ ለታ በጀርመን  ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ጥምረት ከመሰረቱ በኋላ የመጀመሪያውን ሕዝባዊ ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑ ተሰማ::

Ethiopian National Movement Public Meeting in Munich, Germany

የባለሥልጣናቱን ኪስ ነፍስ የሚዘራበት የኢትዮጵያ የስኳር ምርትና ፍላጎት


የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) ስኳር የጫኑ 101 የከባድ ጭነት መኪናዎች አዋሽ ፍተሻ ጣቢያ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ እየተጉላሉ ነው ሲል አገር በዝምታ ተውጣ በትዝብት የምትከታተለውን የስኳር ወሬ ወደ ፊት አምጥቶታል።

ዜናው በማከልም “ዘጠኝ የደረቅ ትራንስፖርት ማኅበራት ተሽከርካሪዎችም ወደ ሀገር ውስጥ ምርቱን በማመላለስ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ 101 ተሽከርካሪዎች አዋሽ አርባን እንዳያልፉ መከልከላቸውን የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ለኤፍኤም አዲስ 97.1 ባቀረቡት ቅሬታ ተናግረዋል። በተናጠል ከ430 እስከ 450 ኩንታል የጫኑትን ተሽከርካሪዎች ባሉበት እንዲቆሙ ያዘዘው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ነው። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ተሽከርካሪዎቹ አዋሽ አርባን እንዳያልፉ የተደረጉት መጫን ከተፈቀደላቸው ክብደት በላይ ስለጫኑ ነው ብሏል።” በማለት የስኳሩን ጉዳይ ወደ ጎን በማለት የትራንስፖርት ችግሩ ላይ በማተኮር ዘግቧል።

በአገራችን የስኳር ምርጥ እጥረትና ችግር በአጭር ጊዜ እፈታለሁ ብሎ ለዓመታት ሲለፍፍ የከረመው መንግሥት ለዚህ አይነት ችግሮች ምላሽ ያለው እንደሆነ በማለት ኢብኮ ጋዜጠኞቹን ሊልክባቸው አልደፈረም፣ አይደፍርምም።

ባለፍው ዓመት 88 ሚሊየን ብር የት እንደደረሰ አጣሁ ያለው የስኳር ኮርፖሬሽን ለሕዝብ ፍላጎት የሚሆን አንዳችም ተግባር ሳይፈጽም ባዶ ወረቀት በፓርላማ አንብቦልን በነጻ የተሰናበተ ሲሆን፣ የኮርፖሬሽኑ ዳይሬክተርና የዚሁ ፕሮጄክት ዋና ተዋናይ የነበሩት አቶ አባይ ጸሀዬም ኮርፖሬሽኑን ጥለው ሹልክ ብለው እንዲወጡ ተደርጓል።

በየጊዜው የስኳር እጥረት የሚያሰቃየው የአገራችን ገበያ ለችግሩ መፍትሄ ማምጣት ያን ያህል ቀላል ሆኖ አልተገኘም። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን መረጃ እንደሚያሳየው የአገሪቱ የስኳር ምርት ፍላጎት ከምርት መጠን ጋር በፍጹም የማይጣጣምና፤ ይህም የፍላጎት መጠን በየዓመቱ እየጨመረ ከመጣው የህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመሄድ ላይ መሆኑን ያሳያል።

ለምሳሌ እ.ኤ.አ. 2010 የስኳር ፍጆታ 500000 የነበረ ሲሆን፣ የምርት መጠኑ ደግሞ 290934 ብቻ ነበር። ይህም ፍጆታው ከምርት መጠኑ ጋር ፈጽሞ ያልተመጣጠነ እንደነበር ያሳያል። ይህንንም ክፍተት አገሪቱ እስከ 150000 ሜትሪክ ቶን ስኳር ከውጭ በማስገባት የአገሪቱን ገበያ ለማረጋጋት ተሞክሯል።

ይሁን እንጂ መንግሥት ይህን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታትና ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የስኳር አምራች በመሆን የውጭ ንግዱን እመራለሁ በማለት ቁጥራቸው ወደ 10 የሚጠጉ የስኳር ፋብሪካዎችን እገነባለሁ ብሎ ወደ ሥራ ከገባ ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፤ አንዳቸውም ግንባታ ጨረሰው ወደ ሥራ አለመግባታቸው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል። እናም ዛሬም የአገሪቱ የስኳር ምርት ቀድሞ በነበሩት ሦስቱ የስኳር ፋብሪካዎች ጫንቃ ላይ እንደወደቀ ቀጥሏል።

በተለይ ደግሞ ይህንኑ ኃላፊነት በበላይነት ሲመሩ የነበሩት አቦይ ጸሀዬ ሥልጣናቸውን በጡረታ ሳቢያ መልቀቃቸው እጅጉን አነጋጋሪ ሆኗል። “የኮርፖሬሽኑን የስኳር ፋብሪካ ግንባታ ዕቅድ ከምን አድርሰውት ነው?” ከሚል ጥያቄ ጋር።

ይሁንና “መንግሥትስ ይህንን የገባውን ቃል አክብሮ መች ነው እነዚህ ፋብሪካዎች ለፍጻሜ ደርሰው የገበያውን ብርሃን ለማየት የሚበቁት? በዚህ ሰበብስ የሚበጀተው የሕዝብ ገንዘብ ማነው ሀይ የሚለው?” የሚሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዳነጋገሩ ይቆያሉ።

በአሁን ወቅት በሥራ ላይ ያሉት ሦስቱ የስኳር ፋብሪካዎች
ተ.ቁ የፋብሪካው ስም ያለበት አካባቢ ስፋት የተመሰረተበት አ.ም የማምረት አቅም
1 ወንጂ/ሸዋ ወንጂ 7050 ሄክታር 1947 80000 ቶን
2 መተሀራ መተሀራ 9919 ሄክታር 1961 115000ቶን
3 ፊንጫ ምስራቅ ወለጋ 6800 ሄክታር 1990 8500 ቶን


ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ (እ.ኤ.አ. 2012)

Dr. Fikre Tolossa: A Presentation of new book entitled “True origin of Oromos and Amharas”

fikre-tolosa-bookBy Berhane Tadese, New York City
December 12, 2016
Hosted by Ethiopian Community Mutual Association (ECMAA), Dr. Fikre Tolossa came to New York City on Saturday, December 10, 2016 to talk about his new book entitled “True origin of Oromos and Amharas”. Dr. Fikre Tolossa is a poet, playwright and an author. His new book has new revelation on Amharas and Oromos origin that have never read anywhere else. The book also explained that the name Ethiopia is derived from “Ethiops”, descendants of one common origin. He dismissed the name Ethiopia as originating from the ancient Greek. Many previous books written about Ethiopia’s history do not focus and address true origin Amhara and Oromo groups. They describe the Amharas and the Tigrians in the north as a Semitic group and the Oromo and the other southern ethnic groups as Cushitic. Dr. Fikre Tolossa’s new book challenge this assertions and describe the origin of the various ethnic groups in Ethiopia as decedents of the ten brothers of the same family. He tries to uncover the origin of Ethiopia going back to 4000 years.
dr-fikre
Today the face book generations politics focus in current ethnic power politics rather than the common history of the various ethnic groups of Ethiopia. Now, Dr. Tolossa’s untold history of Ethiopia discover the common heritage and origin of the Amhara and Oromo people. It is an unprecedented revelation for most ordinary Ethiopians. The academicians and historians are now set in motion to examine his researched findings.  Dr. Fikre presented his work as educational contribution to the new generation. He claimed that all ethnic groups as Ethiopians faced many challenges. He referred historical instances where the gallant Ethiopian people stood side by side to defend the country from foreign invaders. The book also asserts that the current distorted view of Ethiopian history in some quarters imply that the Amhara’s ruled Ethiopia by force imposing their power and will on Oromos and other ethnic groups as false presentation of history of Ethiopia. In fact Dr. Tolossa in his book demonstrates that the roles and contribution the Oromos made in the making of Ethiopian state and history. He states that the kings of Ethiopia during the last 700 years were or have an Oromo ethnic back ground.
In addition the book covers several significant topics on current Ethiopian issues such as:
The impact of the of the late 1960th Ethiopian student movements on current ethnic politics in Ethiopia.
The history and use of Latin alphabet for Oromo language and engage the reader to examine whether the Geze alphabet would be better than the Latin alphabet for the writings of Oromo language.
This book presents a new and fresh perspective on Ethiopian history using ancient Ethiopian documents as its primary source. I urge all Ethiopians interested in the history of Ethiopia to get hold of the book and read it.
This presentation was held at 220 Manhattan Avenue in New York City. Quite a good number of people from New York metropolitan area attended the presentation. At the end of the meeting the author gave answer to several questions raised by the attendees. The Ethiopian community mutual assistance association (ECMAA) regularly invites Ethiopians and interested individuals in the metropolitan area to attend events, book reviews and presentations. It sponsors on relevant topics of Ethiopia. Stay tuned!

Sunday, November 27, 2016

በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ እንደቀጠለ ነው ፥ ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ ኢሳት በሰበር ዜናው ለተያያዘው ምስል ይቅርታ ጠየቀ


ከአርበኞች ግንቦት 7 የጦር አዛዦች አንዱ በሆነው በሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት የለውጥ ደጋፊዎች ሃዘንና ቁጭታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። በሌላም በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ አሁንም መቀጠሉን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ ኢሳት በሰበር ዜናው ለተያያዘው ምስል ዝግጅት ክፍሉ የሟቹ ቤተሰቦቹንና ተመልካቾቹን ይቅርታ ጠየቀ።
የቀድሞ የደርግ መንግስት ለመጣል በተደረገው ትግል በብዓዴን/ኢህአዴግ ትግል ተሳታፊ የነበረው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ስልጣን ላይ ያለውን ቡድን በመቃወም ለትምህርት በሄደበት ፈረንሳይ መቅረቱንናበኋላም በስደተኝነት ሉክሰምበርግ መሻገሩን ፣ ከሁለት አመት በፊት በረሃ ላይ ለኢሳት በሰጠው ቃለ-ምልልስ ገልጾ ነበር።
ስርዓቱን መቃወሞ ብቻ ሳይሆን፣ መታገል ያስፈልጋል በሚል የአውሮፓ ኑሮውን በመተው ከቤተቦቹ ተለይቶ ኤርትራ በረሃ የገባው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ፣ መከበቡን ተከትሎ እጅ ላለመስጠት ራሱን ማጥፋቱን የአካባቢ ምንጮችና አርበኞች ግንቦት 7 ገልጸዋል።
ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ከመከበቡና ራሱን ከማጥፋቱ በፊት በቀደሙት ቀናትና በዕለቱ በተካሄዱ ውጊያዎች እርሱ የሚመራው ጦር በደፈጣና በፊት ለፊት ውጊያዎች ጉዳት ማድረሱም ተመልክቷል።
በፈረንሳይ ፖሪስ የሁለት አመታት ወታደራዊ ትምህርቱን አጠናቆ ከስርዓቱ ለመለየት በመወሰን በስደት ሉክሰምበርግ የቆየው የሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት የብዙዎችን ሃዘንና ቁጭት መቀስቀሱ ታውቋል።
በኢሳት የድምፅ መልዕክት ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ የመጡ በርካታ አስተያየቶችም ሻለቃ መሳፍንት በጀግንነቱ ያወደሱ ሲሆን፣ መስዋዕትነቱ ትግሉን ያፋፍማል ሚሊዮኖችን ያፈራል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተያያዘ ዜና ከጦር መሪዎቹ አንዱ የተሰዋበት አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ መቀጠሉን የአካባቢው ምንጮች ሲገልጹ ግንባሩም ይህንኑ አረጋግጧል።
በስርዓቱ ተቆጥተው መሳሪያ ይዘው የሸፈቱ የነጻነት ሃይላትም በተለያዩ የሰሚን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ውጊያ መቀጠላቸውን መረዳት ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ በሰበር ዜናችን ውስጥ ለተካተተው ምስል ኢሳት የሻለቃ መሳፍንት ቤተሰቦችን እንዲሁም ተመልካቾቹን ይቅርታ ጠይቋል። በአሰራር ላይ በተፈጠረ ግድፈት የአስከሬኑ ምስል በቪዲዮው ዘገባ ውስጥ ማካተቱ ተገቢ ባለመሆኑም፣ ኢሳት ምስሉን በዕለቱ ያስወገደ መሆኑን የኢሳት ዝግጅት ክፍል አስታውቋል።
15109542_10210938344445355_8898449061103277225_n


ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አቶ ጌታቸው በከፍተኛ ህክምና ታይላንድ ባንኮክ ይገኛሉ።


በቅርቡ ጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ባወቀሩት ካቢኔ ውስጥ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት አቶ ጌታቸው አምባዬ ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ በስራ ገበታቸው ላይ አለመሆናቸው ታወቀ። የቅርብ ምንጮች እንደገለጹት ባለስልጣኑ በታይላንድ ባንኮክ በከፍተኛ ህክምና ላይ ይገኛሉ። ሹመቱ የተሰጣቸው በውጭ ሃገር በህክምና ላይ መሆናቸው እየታወቀ መሆኑን መረዳት ተችሏል።
በቅርቡ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓም በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ በነበሩት ቦታ እንዲቀጥሉ ከተወሰነላቸው ሚኒስትሮች አንዱ የሆኑት አቶ ጌታቸው አምባዬ ብዓዴንን ወልከው ስፍራውን በመያዛቸው፣ ብዓዴን እርሳቸውን የሚተካ ሰው ባለማቅረቡ በህመም ላይ ባሉበት በድጋሚ መሾማቸውም ተመልክቷል።
ጥቅምት 22፣ 2009 ዓም በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ እንደገና በጠቅላይ አቃቤ ህግነት የቀጠሉት አቶ ጌታቸው አምባዬ በ1982 የትጥቅ ትግል የተቀላቀሉና በትጥቅ ትግል እንዳለፉት ሁሉ በልዩ ዕገዛ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም መማራቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ በአስቸኳይ አዋጁ ዙሪያ ማብራሪያ ሲሰጡ የታዩትና ከዚያ በኋላ በድንገት ጤናቸው ታውኮ በታይላንድ ባንኮክ አንድ ወር ያህል ያስቆጠሩት የአቶ ጌታቸው አምባዬ ህመም ምን እንደሆነ ምንጮች አልገለጹም። ሆኖም ባለስልጣናት ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ህክምና ያለፉ መሆናቸውን በመግለጽ ችግሩ የቆየ የጤና ችግር የተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረ አመልክተዋል።
ከአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ወደ አዲስ አበባ ካቢኔ በመጨረሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከፍትህ ሚኒስትርነታቸው በተነሱት የብዓዴኑ አቶ ብርሃን ሃይሌ ምትክ ፍትህ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ አቶ ጌታቸው አምባዬ፣ ፍትህ ሚኒስቴር ፈርሶ ወደ ጠቅላይ አቃቤህግነት ሲሻገሩም ከነስልጣናቸው ቀጥለዋል።

የአማራ ተጋድሎ ከዚህ ወዴት? (ከሙሉቀን ተስፋው) ክፍል አንድ



(ሲያትል በነበረው ስብሰባ ሊቀርብ የነበረ ጽሑፍ ነው፤ ፕሮግራሙ ላይ እንዲቀርብ ለ27 ደቂቃ የተቀዳው ሪከርዱ በቴክኒክ ችግር ባለመሥራቱ መቅረብ አልቻለም፤ እኔም አዘጋጆቹም በጣም አዝነናል። ይህን ጽሑፍ በማዘጋጀት በአዲስ አበባ እና የጎንደር ዩንቨርሲቲዎች ያሉ የአማራ ምሁራን አግዘውኛል። ምስጋና ይገባቸዋል፤ ብዙ የአማራ ምሁራን ከጀርባ ሆነው የሚያደርጉት አስተዋጽኦ እጅግ ያስደስታል። በነጻነታችን ጊዜ ስማቸውን ከፍ አድርገን ሥራቸውን እንዘክራለን። ለማንኛውም ላቀርበው የነበረውን ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል እንሆ)



1. እንደመግቢያ

ወሮበላው የወያኔ ቡድን ሥልጣን የያዘበት 1983 ዓ.ም. ለእኛ ለአማሮች ወገኖቻችን በጅምላ የሚታረዱበትን፣ በገፍ የሚፈናቀሉበትንና በዘረኞች ያለማቋረጥ የሚሰቃዩበትን ዘመን ያዋለደ ክፉ ዘመን ነው። ይህ ጊዜ የአማራ ሕዝብ ከጨለማ ወደባሳ ጨለማ የገባበት፣ በሕዝባችን ላይ የታወጀው የጥፋት ደወል የተደወለበት፣ በርካቶች በአማራነታቸው የታረዱበት፣ ቤት ንብረታቸውን በትነው ለዘመናት ከኖሩባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉበትና በአገራቸው ባይተዋር ሆነው እንዲኖሩ የተወሰነበት የክፉ ጊዜ መጀመሪያ ነው። በደርግ አምባገነናዊ አገዛዝ ልጆቹን ሲነጠቅ የኖረው፣ ከየትኛውም ሕዝብ በላይ ልጆቹን ለጦርነት እንዲያዋጣ ሲገደድ እና በኮታ፣ በግብር ወዘተ. ሲማቅቅ የቆየው ሕዝባችን፣ ከመከራ ወደባሰ መከራ እንዲገባ የተደረገበት ጊዜም ነው።

በሺሕዎች የሚቆጠሩ የአማራ ልጆች ለኢትዮጵያ ሕዝቦች እኩልነትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሥረታ እንዳልታገሉ እና የንጉሠ ነገሥቱንም ሆነ የደርግን ሥርዓቶች ታግለው መስዋዕትነት እንዳልከፈሉ፣ ሕዝባችን ባለፉት ሥርዓቶች ከሌላው ሕዝብ በተለየ መልኩ እንደተጠቀመና ያለፈው ሥርዓት ተቆርቋሪ እንደሆነ ተቆጠረ፤ መብታቸውን የሚጠይቁ አማሮች ሁሉ ባለፈው ሥርዓት ናፋቂነት፣ በትምክህተኝነት፣ በነፍጠኝነት ወዘተ. እየተወነጀሉ ከየአቅጣጫው የጥቃት ሰለባ ሆኑ፤ የአማሮች ከየአካባቢው መሳደድና መገደል ለማንም የማይገደው ተራ ጉዳይ ሆነ። በዘመነ ወያኔ በሕዝባችን ላይ የደረሰውና እየደረሰ ያለው ግፍ ገና በዝርዝር ሊጠናና ሊተነተን የሚገባው ትልቅ የቤት ሥራ ነው።

ጸረ አማራው የወያኔ ቡድን ንጹሐን አማሮችን እያደነ እንደጨፈጨፈ፣ ከቤት ንብረታቸው እንዳፈናቀለ፣ ሁሉም ሕዝብ በአማራ ላይ እንዲዘምት ሰነድ አዘጋጅቶና የመንግሥት በጀት በጅቶ እንደቀሰቀሰ፣ ተስፋ የሚጣልባቸውን የአማራ ልጆች እስር ቤት እያጎረ የቶርቸር ሰለባ ሲያደርግ እንደቆየ ወዘተ. ወዘተ. አይዘነጋም። በሚያሳዝን መልኩ፣ የአማራ ሕዝብ በዚህ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ መጠነ ሰፊ ውርጅብኝ ሲወርድበት የቆየ እና አሁንም ይኸው የዘር ማጥፋት ጦርነት ግልጽ በሆነ መልኩ ታውጆ የቀጠለ ቢሆንም፣ ለሕዝባችን የሚጮህለት ኃይል የለም። የሕዝባችን በደል የሚገደው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅትም አልተገኘም። የዚህ ነብሰ ገዳይ ቡድን ወዳጅ የሆኑ ኃያላን አገሮችም በሕዝባችን ላይ የታወጀውን የዘር ፍጅት እያዩ እንዳላዩ ማለፍን መርጠዋል። በአጭሩ ለአማራ ሕዝብ ከራሱ ውጪ ማንም እንደማይጮህለት፣ ማንም እንደማይገደው በሚገባ ተረጋግጧል። ለዚህ ነው ሕዝባችን በሕዝብ ደረጃ ተደራጅቶ ከመታገል ውጪ ምርጫ የለውም የምንለው።

እንደአማራ ተደራጅተን የምንታገለው ራሳችንን ከወያኔ የዘር ፍጅት ጦርነት ለመከላከል፣ ራሳችን ከጥፋት ለማዳን፣ የሕዝባችን ቀንደኛ ጠላት የሆነውን ወያኔን ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ አሽቀንጥረን ለመጣልና የአማራ ሕዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ለማስቻል ነው። ትግላችን የአማራ ሕዝብ መሳደድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቆምና ሕዝባችን በነጻነት እንዲኖር ለማስቻል ነው። ትግላችን የአማራ ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት እንዲሆን ለማድረግ ነው።

2. በትግላችን ምን አሳካን?

ከሁሉ አስቀድሞ ለአማራ ሕዝብ ነጻነት ግንባሩን አሳልፎ የሚሰጥ፣ የማይፈራና ጠላትን እረፍት የሚነሳ ታጋይ ትውልድ ፈጥረናል። ይህ ትልቅ ስኬት ነው። እስካሁን ባካሔድነው ትግል ማን የአማራ ሕዝብ ጠላት እንደሆነ፣ ማን ወዳጃችን እንደሆነ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ይዘናል። ይህም በራሱ ትልቅ ስኬት ነው። በሕዝባችን መሃል ተሰግስገው፣ ያጎረሳቸውን እጅ የሚነክሱ ውለታ ቢስ ወያኔዎችን መንጥረን ማስወጣት መጀመራችንም ትልቅ ድል ነው። ከሁሉ በላይ የአማራ ሕዝብ ልጅ አዋቂ፣ ሴት ወንድ፣ አርሶ አደር ከተሜ ሳይል ሁሉም በአማራነት ተደራጅቶ መታገል እንዳለበት ግንዛቤ መያዙ ትልቅ ስኬት ነው!!!

ባሌ ላይ ያለው አማራ መተማ ስለሚሞቱት ወገኖቹ የሚቆጭበት ብቻ ሳይሆን ጎንደርና ጎጃም ድረስ ሔዶ ትግሉን የሚቀላቀልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ጎንደር ለተገደሉት ወንድሞቻቸው ደሴ ላይ ሐዘን የሚቀመጡ፣ ጎጃም ላይ የታረዱ ወንድሞቻቸውን ደም ለመመለስ ማጀቴ ላይ የሚመክሩ አማሮችን አግኝተናል። ኅብረቱ ከዚህ በላይ እንዲጎለብትና ሥር እንዲኖረው መኮትኮት ከሁሉም የአማራ ልጆች የሚጠበቅ ትልቅ የቤት ሥራ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የአማራ ብሔርተኝነት ማንም ባልጠበቀውና ባልገመተው ፍጥነትና ብስለት ብዙ እርምጃዎች ወደፊት እንደሔደ ታይቷል።
ሕዝባችን ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ያለውን ወገንተኝነት በሳልና አርቆ አስተዋይ በሆነ መልኩ በማሳየት፣ ወያኔ አማራውን እንደጭራቅ ስሎ ሲሰብከው የኖረበትን ጸረ ሕዝብ ተግባር መና አስቀርቶታል። የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሠረተ አንድነት መመሥረትና አብሮ መኖር እንደሚፈልግ በግልጽ ቋንቋ ተናግሯል። ይህ ሁሉ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነገር ነው።

በሌላ በኩል ወያኔ በአማራና በኦሮሞ ሕዝቦች ትግል ተርበትብቶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ በኢትዮጵያውያንም ሆነ በመላው የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ፊት እርቃኑን ቀርቷል። ይህም በወገኖቻችን መስዋዕትነት የተገኘ ትልቅ ድል ነው። ብዙዎች ወያኔ አምባገነን መሆኑ እንዲታወቅ ብዙ ለፍተዋል። ሁላችንም ወያኔ ጸረ ሕዝብና ጸረ ዴሞክራት ቡድን መሆኑን በተመሳሳይ ደረጃ ባለመረዳታቸን፣ አንዱ እስኪ ጊዜ እንስጣቸው እያለ የሚያወላውልበት፣ ሌላው አብሮ እየሠራ ሕዝብ የሚበድልበት፣ ሌላው እውነታው የገባውና ጥያቄ የሚጠይቀው የቶርቸር ሰለባ የሚሆንበትና የሚገደልበት ድብልቅልቅ ያለ ጊዜ አሳልፈናል። የዚህ ዓመት ትግል ይህንን ሁኔታ በማያወላውል መልኩ የለወጠ፣ ከሞላ ጎደል ሁላችንም ወያኔ ፍጹም ግፈኛና ጸረ ሕዝብ ቡድን መሆኑን የተረዳንበት እንቅስቃሴ በመሆኑ ትልቅ ስኬት ያስገኘ ትግል ነው። ከዚህ በኋላ ወያኔ ሊያጭበረብር የሚችልበት ምንም ዓይነት ዕድል የለውም። እስካሁን ኢትዮጵያችን ሲመዘብራት የኖረው አንድ በመሣሪያ ኃይል የተንጠለጠለ ያገጠጠ ያፈጠጠ አናሳና አምባገነን ቡድን መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ሆኗል።

የታወጀው ጸረ ሕዝብ አዋጅ ወያኔ ምን ሊሆን እንደሚችል፣ ሥልጣኑን ለመጠበቅ እስከምን ደረጃ ድረስ ሊዘቅጥና ፋሽስታዊ ተግባር ሊፈጽም እንደሚችል በግልጽ ያሳየ ሰነድ ነው። ወሮበላው ቡድን ይህን ጸረ ሕዝብ አዋጅ ‹ከሞት ተነስቷል› ያለውን አማራን ለማንበርከክ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እየገደለና በገፍ እያሰረ የቶርቸር ሰለባ በማድረግ እየሠራበት ነው። ሆኖም ይህ ፋሽስታዊ ቡድን ከዚህ በኋላ የትኛውንም ያህል ቢወራጭ፣ የትኛውንም ያህል ቢገድለንና ልጆቻችን በገፍ እያሰረ ግፍ ቢፈጽም በምንም ዓይነት ሁኔታ ለእነዚህ ግፈኞች የሚንበረከክ አማራ ከቶ አይኖርም።

ወሮበላው ቡድን መብታቸውን የጠየቁ ንጹሐን የአማራ ልጆችን በግፍ ጨፍጭፎ ሲያበቃ፣ በሕዝባቸን ላይ የፈጸመውና በመፈጸም ላይ የሚገኘው ዘግናኝ ፍጅትና ቶርቸር አልበቃው ብሎ፣ የሕዝቡን መሠረታዊ ጥያቄ ለማስቀየስ መሣሪያ ደግኖ ‹በጸረ ሰላም ኃይሎች ተወናብደን ንብረት አውድመናል፤ መንግሥት ለመገልበጥ ተንቀሳቅሰናል፤ ወዘተ.› እያሉ በሕዝብ ፊት አንዲዋረዱና አንገታቸውን እንዲደፉ በየዕለቱ እየሠራ ይገኛል። ደንቆሮው የወያኔ ቡድን ያልተረዳውና ሊረዳውም የማይችለው ቁም ነገር፣ የተጣላውና ደም የተቃባው የወንድሞቹንና የእህቶችን ደም ሳይመልስ ከማይተኛው በሚሊዮኖች ከሚቆጠረው የአማራ ወጣት ጋር መሆኑን ነው። እነዚህ የባንዳ ልጆች ያልተረዱትና ሊረዱትም የማይችሉት ቁም ነገር፣ ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት የአማራ ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ እየተበደለ በዝምታ የኖረው ለኢትዮጵያ አንድነት ካለው ቀናዒነት የተነሳ መሆኑን ነው። እነዚህ የለየላቸው ወሮበሎችና ነብሰ ገዳዮች ያልተረዱት ቁም ነገር፣ ከዚህ በኋላ የአማራ ልጅ የወንድሞቹንና የእህቶቹን ደም ሳይመልስ፣ ወያኔን አሽቀንጥሮ ጥሎ የአማራን ሕዝብ ነጻ ሳያወጣና የሕዝቡን ክብር ሳይመልስ የማይተኛ መሆኑን ነው።

ወያኔ በሚቆጣጠረው ሚዲያ ቱልቱላውን እንደሚነፋው ይህ አዋጅ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ሊያመጣ አልቻለም፤ አይችልምም። ይልቁንም የዚህ አዋጅ መታወጅ ሕዝቡ ‹ወያኔ ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ አሽቀንጥረን እስካልጣልን ድረስ ከመታሰር፣ ከመሳደድና ከመሞት አናመልጥም፤ ወያኔ ካልተንኮታኮተ ሰላም የለንም፤ ወያኔ እስካለ ድረስ ከመሸበርና ከመታወክ አንገላገልም› የሚል ግልጽ አቋም እንዲይዝና በሚችለው ሁሉ ይህን ነብሰ ገዳይ ቡድን እንዲታገለው ዕድል ይከፍታል። መሣሪያ ተደግኖብን፣ በየዕለቱ እየተሳደድን፣ እየታሰርንና ወገኖቻችንን እየተነጠቅን ምንም ዓይነት ሰላም አይኖረንም።
የሰላም ጠላት፣ የሁከትና የሽብር አባት የሆነው የወያኔ ቡድን እስካልተንኮታኮተ ድረስ የአማራ ሕዝብ ሰላም አይኖረውም። በዚህ ጸረ ሕዝብ አዋጅ የሚሸበር አማራ የለም።

የዚህ አዋጅ መታወጅ ትግሉን ብዙ እርምጃ ወደፊት ያራምደዋል እንጂ አንዲትም ጋት ወደኋላ አይጎትተውም። ይህ ጸረ ሕዝብ አዋጅ እርስ በርሳችን እንዳንረዳዳ ሊያደርገን አይችልም፤ አዋጁ ድርጅቶቻችን እንዳንደግፍና እንዳናጠናክር ሊያደርገን አይችልም፤ አዋጁ መስዋዕቶቻችንን እንዳናስብ፣ ስለእነሱ የትግል ታሪክ እንዳንጽፍና ቤተሰቦቻቸውን እንዳንረዳ ሊያግደን አይችልም፤ አዋጁ ስለቀጣዩ የትግል ስትራቴጂያችን እንዳንመካከር ሊያደርገን አይችልም፤ አዋጁ ወያኔን እንዳንጠላና እንዳንጸየፍ ሊያግደን አይችልም ወዘተ. ወዘተ. እንዲያውም ከላይ እንደተጠቀሰው ‹ወያኔ ጸረ ሕዝብና ጸረ ዴሞክራሲ ዘረኛ ቡድን ነው› በሚለው መሠረታዊ ሐቅ ላይ ብዥታ የነበራቸው እና ትግሉን ወደኋላ ሲጎትቱ የነበሩ ወገኖች ሁሉ በዚህ አዋጅ ምክንያት ትልቅ ግንዛቤ ስለጨበጡ ትግሉ ብዙ እርምጃ ወደፊት ሄዷል።

#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!!!

የትግሉ ዋና ዓላማ ለሥልጣኔ ወይንስ ሥልጣንን ለመያዝ?



ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)
በሰፊ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ያልተደገፈ የፖለቲካ ትግል የሥልጣኔ እንቅፋት ነው!
መግቢያ

በአብዛኛዎቹ የሦስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮችና፣ በጠቅላላው የካፒታሊስት አገሮች ተብለው በሚታወቁትና የሳይንስና የቴክኖሎጂ የበላይነትን በተጎናጸፉት አገሮች ያለውን ልዩነት ስንመለከት ልዩነቱ እጅግ ከመስፋቱ የተነሳ እንደዚህ ዐይነቱን የተወሳሰበ ሕብረተሰብ ለመገንባት የብዙ መቶ ዓመታት ሥራ እንደሚያስፈልገን ይታየኛል። በአጠቃላይ ሲታይ የካፒታሊስት አገሮች ይህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ደርሰው ዓለምን መቆጣጠር ሲችሉ እኛን ምን ነካን ብለን የምንጠይቅ ብዙ ላንሆን እንችላለን።

እንደሚታወቀው እንደዚህ ዐይነቱን ጥያቄ ሊያነሱ የሚችሉት ሰዎች በጣም የተወሰኑና የአንድን ሕዝብ ዕድል ሥልጣን ከመያዝ ባሻገር ሊያዩ የሚችሉ ሰዎች ብቻ እንደሆነ መገመት ይቻላል። ያም ሆነ ይህ የእነሱን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የሚሊታሪ የበላይነትና ዓለምን መቆጣጠር ጠጋ ብለን በምንመረምርበት ጊዜ የምናገኛው መልስ እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፈውና፣ በተለይም ደግሞ የአዕምሮን ዋና ቁልፍነት በመረዳትና፣ ከዚህ የሚፈልቀውን የማሰብ ኃይል ቅድሚያ በመስጠት እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን። ይሁንና ግን የአውሮፓውን የምሁር እንቅስቃሴና የሕብረተሰብ አገነባብ ታሪክ ለተከታተለ የተፈጥሮንና የሰውን ልጅ ሚና፣ እንዲሁም የፖለቲካን ትርጉም ለመረዳት የተለያየ አስተሳሰብና የጦፈ ትግልም ይካሄድ እንደነበር መገንዘቡ እስከዚህም ከባድ አይደለም። በተጨማሪም ሥልጣን መጨበጥና በአንድ ዶግማ ወይም አመለካከት መመራት ስር የሰደደም እንደነበር እንገነዘባለን። ይህም ማለት አንዳንዶች ካልሆኑ በስተቀር ሥልጣን ላይ ቁጥጥ የሚሉት ኃይሎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈልጓቸው ዕቅዶች ሁሉ በጊዜው በነበረው ምሁራዊ ኃይል ጥንካሬና የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ፣ በራሳቸው ሥልጣን በጨበጡት ኃይሎች የንቃተ-ህሊና ሁኔታና በአካባቢያቸው ባሉ አገሮች የዕድገትና የፀረ-ዕድገት ሁኔታ የሚወሰን እንደነበር መገንዘብ እንችላለን።

የአገራችንና የሌሎችን የአፍሪካ አገሮችን ሁኔታ ስንመረምር ግን ከሃምሳ ዓመት “የፖለቲካ ነፃነት“ በኋላ አሁንም ቢሆን እዚያው በዚያው ሲንደፋደፉና፣ ሥልጣን ላይ ቁጥጥ የሚሉት ኃይሎች በሙሉ የራሳቸውን ኑሮ ከማደላደልና ዝናን ከመጎናጸፍ በስተቀር ሕብረተሰብዓዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፓለቲካዊና እንዲሁም የባህል ኃላፊነት የሚሰማቸው እንዳልሆኑ በምድር ላይ የሚታየው ሁኔታ ያረጋግጣል። ለዚህ ዋናውና አንደኛው ምክንያት የባሪያ ንግድና የቅኝ-ግዛት አስተዳደር የአፍሪካን የሕብረተሰብ አወቃቀር ስላዘብራረቁትና ቀስ ብሎ የማደግ ዕድገቱን ስላጨናገፉበት ታሪክ ሊሰራ የሚችል የሕብረተሰብ ክፍልና ኢንስቲቱሺናዊ አወቃቀር ሊዳብሩ ያለመቻላቸውን ታሪክ ያረጋግጣል። በተጨማሪም የፖለቲካ ነፃነትን ተቀዳጁ ከተባለ በኋላ በራሳቸው ጥረት አገሮቻቸውን እንዳይገነቡ ብዙ አሻጥሮች ይሰራባቸው እንደነበር ይታወቃል። ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዳይኖርና አትኩሮአቸው በበሕብረተሰብ ግንባታ ላይ እንዳይሆን የአብዛኛዎቹ አፍሪካ አገሮች ከስድሳ በላይ የሚቆጠሩ የመንግስት ግልበጣዎች ተካሂዶባቸዋል።

ወደ ኢትዮጵያችን ስንመጣ ግን አገራችን የሦስት ሺህ ዓመት ታሪክ ያላትና በቅኝ-ገዢዎች ቁጥጥር ስር ያልነበረች አገር ነች እያልን ብንመፃደቅም፣ የሕብረተሰብን አገነባብና የኢኮኖሚ ዕድገትን ጉዳይ፣ እንዲሁም ደግሞ አጠቃላዩን የሥልጣኔ ፕሮጀክት በሚመለከት እስከዚህም ድረስ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተሽለን የምንገኝ እንዳልሆነ የአገራችን ነባራዊ ሁኔታና የራሳችንም የፖለቲካ ትግልና የአስተሳሰባችንም ሁኔታ በበቂው ያረጋግጣል። ያለፈውን የሃምሳ ዓመት ታሪካችንን ለተከታተለ በተደጋጋሚ በረሃብ የሚታወቅና ለልመና የዓለምን ማኅበረሰብ የሚማፀን እንደኛ ያለ አንድም የአፍሪካ አገር የለም። ይህም የሚያረጋግጠው እኛ የሦስት ሺህ ዓመት የሥልጣኔ ታሪክ አለን እያልን የምንመፃደቀው እስከዚህም ድረስ የማኅበረሰብዓዊና የሕብረተሰብዓዊ ኃላፊነት እንደሌለንና፣ ንቃተ-ህሊናችንም ሕዝባችን ከሚመኘው የሥልጣኔና የሰላም ፕሮጀክት ጋር በፍጹም የሚጣጣም እንዳልሆነ ነው።

ከዚህ ስነነሳ በተለይም አብዮቱ ፈነዳ ከተባለበት ጀምሮና እስከዛሬ ድረስ ያለውን የፖለቲካ አሰላለፍና ሁኔታ ስንመረምር የፖለቲካ ተዋናይ ነን የሚሉት ዋና ተግባርና ዓላማ ሥልጣንን ከመጨበጥ ጋር የተያያዘ እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን። በጊዜው የተነሳው የፖለቲካ ጥያቄ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ትክክል ቢሆንም፣ ይህ በራሱ የሥልጣኔ ፕሮጀክትና ቁልፉም እንዳልሆነ በሳይንስ ማረጋገጥ እንችላለን። ያም ሆነ ይህ በተለይም ሥልጣኔን ማዕከላዊ ያላደረገ የፖለቲካ አካሄድ የመጨረሻ መጨረሻ ለደም መፋሰስና ዛሬ አገራችን ለምትገኝበት ሁኔታ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል ማለት ይቻላል። በጊዜው የፖለቲካ ተዋንያን የነበሩት ድርጅቶችና ዛሬም በህይወት የሚገኙት መሪዎቻቸው ለመቀበል የማይፈልጉትና የማይዋጥላቸውም ነገር እነሱ ብቻ የታሪክ መነሻና መጨረሻው አድርገው መውሰዳቸው ብቻ ሳይሆን፣ እነሱ ብቻም የዕውቀትን ቁልፍ እንደያዙ መረዳታቸውን ስንገነዘብ በጣም ነው የምናዝነው። ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት የታሪክን ኃላፊነት ሊወጣ የሚችለው በየጊዜው ራሱን መመርመር የቻለና ከሌሎች እሱን ቀድመው ከሄዱ ጋር ማወዳደር ሲችልና ትምህርትም ሲቀስም ብቻ ነው። ይህንን በሚመለከት ያ ብዙ የተጠበቀበትና ወደ መጨረሻ ላይ ደም ማፋሰስ ያበቃ አብዮት ለምንድነው ያልተሳካ? ብሎ ከራሱ ስሜት ውጭ ኦብጀክቲብ በሆነ መንገድ የራሱን ቦታ የመረመረና በጥናት መልክ ለተከታዩ ትውልድ ያቀረበ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የለም። ሁሉም በየፊናው የራሱን ሚና ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ስለሚፈልግ በአብዮቱ ውስጥ ላልተሳተፈው እንደኛ ላለው የነበረውን ሁኔታ በቀላሉ ሊገነዘብው በፍጹም አይችልም። አዲስ ኃይል ብቅ ብሎ ወገናዊ አቋም ሳይወስድ የብዙ ዓመታት ምርምር ካደረገ በኋላ ምናልባት ሀቁን መረዳት እንችል ይሆናል።

ያም ተባለ ይህ በማንኛውም አገር አንድ ሕዝብ የዕድገትና አጠቃላይ የሆነ የሥልጣኔ ባለቤት እንዲሆን ከተፈለገ ተቀባይነትን ካገኘ (Conventional Wisdom) የትግልት ስልትና ዕውቀት ባሻገር አልፎ መሄድ እንዳለበት መረዳት አለበት። እንደምንመለከተው ከስላሳ ዓመት የግሎባል ካፒታሊዝም የበላይነት ዘመን በኋላ የዓለም ማህብረሰብ በመረጋጋት ላይ ያለ አይደለም። አብዛኛዎቹ የሦስተኛው ዓለም አገሮች ተብለው የሚጠሩት፣ በተለይም የአፍሪካ አገሮች በትርምስ ውስጥና የርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። ከዚህ በመነሳት የታወቁ የሥልጣኔ ተመራማሪዎች እንደሚሉትና እንደሚያረጋግጡት የዓለም ሁኔታ በዚህ መቀጠል ያለበት ሳይሆን የግዴታ በከፍተኛ ንቃተ-ህሊና በመታገዝ (Quantum Consciousness) ወደ ዕድገትና ወደ ከፍተኛ ሥልጣኔ ማምራት እንዳለበት ያሳስባሉ። ስለሆነም እኛም ከዚህ ውጭ መሆን ያለብን አይመስለኝም። በአገራችን ምድር ዕውነተኛ ሥልጣኔና በግለሰብ ፈጠራ ላይ የተመረኮዘ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ዲሞክራሲያዊ ነፃነት እንዲመጣ ከፈለግን የትግል ስልታችንን መቀየር አለብን። ሽወዳን ሳይሆን ሀቀኝነትንና ፕሪንስፕልን በማስቀደም ወደፊት ወጥተን መታገል አለብን። መድረኩን ሰፋ ላለ ምሁራዊ ጥናትና ክርክር መክፈት አለብን። ታሪክ እንደሚያረጋግጠው አስተሳሰቡን የገደበና ለክርክርና ለውይይት ያልተዘጋጀ ሕብረተሰብ በምንም የሥልጣኔ ባለቤት ሊሆን እንደማይችል ነው።

በታሪክ ውስጥ ከላይ ወደታች የመጣ ሥልጣኔና ዴሞክራሲያዊ ነፃነት አልታየም

በታሪክ ውስጥ እንደተረጋገጠው ሥልጣንን የጨበጡ ኃይሎች በራሳቸው ፈቃድ ዲሞክራሲን ያወጁበትና የሥልጣኔ ፕሮጀክት የነደፉት ጊዜ በጣም አነስተኛ ነበር። ይህም በአምስተኛው ክፍለ-ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ሲሆን፣ ሶሎን የሚባለው መሪ ልዩ የሆነ ፍጡርና ጊዜው የወለደው (Zeitgeist) ውጤት ነው ማለት ይቻላል። ሶሎን ተራ ፖለቲከኛ ሳይሆን ሕብረተሰብና ሥልጣኔ ማለት ምን ማለት እንደሆኑ የገባውና የሰውን ልጅነት ምንነት የተረዳ ታላቅ መሪ እንደነበር መገንዘብ እንችላለን። ፈላስፋና ገጣሚ እንዲሁም የቲያትር ደራሲ እንደመሆኑ መጠን ፖለቲካን የተረዳው ከቀን ተቀን ተግባራዊ ሂደት አልፎ ሰፋ ያለ የሥልጣኔ ፕሮጀክት መንደፊያ አድርጎ በመረዳቱ የግሪክ የፊዩዳል አሪስቶክራሲ መደብ ጭንቅላቱን ከተበተበውና የሕብረተሰብን ዕድገት ከሚቀናቀነው አስተሳሰቡ እንዲላቀቅ በማድረግ ሕብረተሰቡን አንቀው ያየዙ ማነቆዎችን ለማስወገድ ቻለ። በሱ ሰፋ ያለ የጥገና ለውጥ የተነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ በግሪክ በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ በተለይም ሂሌን በሚባሉት ግዛቶች ውስጥ ሥልጣኔ ማሸብረቅ ቻለ። ፍልስፍና፣ ማቲማቲክስ፣ አርኪቴክቸር፣ ሰዕልና ድራማ፣ እንዲሁም ግጥሞችና ሙዚቃ፣ ክርክርና የሊትሬቸር አጻጻፍ፣ በተጨማሪም ልዩ ዐይነት የታሪክ አተረጓጎም ሥራዎች እንደአሸን በመፍለቅ በተለይም የታዳጊውን ትውልድ ጭንቅላት በመያዝ የሥልጣኔ መረብ ውስጥ ከተቱት። የግሪክ ሕዝብ ራሱን በራሱ ሲያገኝ ዋናው የዲሞክራሲና የነጻነት እንዲሁም የሥልጣኔ ፕሮጀክት ከራሱ የሚመጣ እንደሆነ መረዳት ቻለ። ሥራዎች ሁሉ በስርዓትና በግንዛቤ የሚሰሩ፣ ዲሞክራሲያዊ ህይወትና ሥልጣኔ እንዲሁም ግለሰብዓዊ ነፃነትና ሕብረተሰብዓዊ ኃላፊነት፣ በተጨማሪም ሞራልና ስነ-ምግባር ተያይዘው እንደሚሄዱ ግንዛቤ ውስጥ ተገባ። ይሁንና ግን ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ኃሎችም ወሳኝ ሚናን የሚጫወቱ ስለሆነ፣ ተፈጥሮአዊና የኮስሞስን ሕግ ሳይሆን በራሳቸው ስሜትና ኤጎ የሚመሩ ከሆነና ወደ ውስጥ ጭንቅላታቸውን የማይመለከቱ ከሆነ የግዴታ የጦርነትና የድህነት ምንጮች ሊሆኑ እንደሚችሉ በፕላቶንና በሶክራተስ እንዲሁም በአርስቲቶለስ ዘንድ ከፍተኛ ግንዛቤ ነበር። ስለዚህም ነው ፕላቶ ፖለቲከኞች የፍልስፍና አዋቂዎች መሆን አለባቸው ወይም ደግሞ ፖለቲካ በፈላስፋዎች መመራት አለበት የሚለው።

የሶክራተስና የፕላቶን እንዲሁም የአርስቲቶለስ አመለካከት በፖለቲካ ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን ስለ ኢኮኖሚ ያላቸው ግንዛቤም የቱን ያህል እንደነበረ መገንዘብ እንችላለን። በነሱ ትክክለኛ አመለካከት አንድ ማኅበረሰብ የግዴታ በሥራ-ክፍፍል መደራጀት ሲኖርበት፣ በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች መሀከል በገንዘብ ሊገለጽ የሚችል የንግድ ግኑኝነት መፈጠር እንዳለበት ያሳስባሉ። ይህም ማለት አንድ ሕብረተሰብ የግዴታ ተከታታይነት ሊኖረው የሚችለው ሰፋ ያለ የኢኮኖሚ መሰረት ሲዘረጋለትና፣ ሕዝቡም በተለያዩ የሙያ መስኮች ተሰማርቶ የመፍጠር ችሎታውን ተግባራዊ ለማድረግ አመቺ ሁኔታ የተፈጠረለት እንደሆነ ብቻ መሆኑን ያሳስባሉ። ይሁናን ግን የገንዘብን ጉዳይ በሚመለከት ከሕብረተሰቡ ፍላጎት ውጭ መውጣት እንደሌለበትና የሰውንም ሞራል እንዳያበላሽ ሆኖ መካሄድ እንዳለበት ያሳስባሉ።

ያም ሆነ ይህ በግሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ ያለው ዲሞክራሲ አንዳንድ የኢትዮጵያ የተማሪው እንቅስቃሴ መሪዎች በጊዜው ለማሳመን እንደሚሞክሩት ከገዢው መደብ አንፃር ብቻ ታይቶ ተግባራዊ የሆነ ሳይሆን፣ ስፋ ያለ ፕሮጀክት ያለውና፣ ለሥልጣኔና ለግለሰብዓዊ ነፃነት በር የከፈተ ከፍተኛ የጥገና ለውጥ ነው ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። ስለሆነም ነው ይህ የዲሞክራሲና የሥልጣኔ ፕሮጀክት ከአሥራአራተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ ብቅ ላለው የተሃድሶ (Renaissance) መሰረት ሊሆን የበቃው።
በአሥራአራተኛው ክፍለ-ዘመን ብቅ ያለውና እየተስፋፋ የመጣው የተሃድሶ እንቅስቃሴ ከግሪኩ ለየት የሚያደርገው ከላይ ወደ ታች የተወረወረና ከስር በመነሳት ደግሞ እየተቀጣጠለ በመምጣት ለሥልጣኔ በር የከፈተ ሳይሆን ግለሰቦች በራሳቸው ተነሳሽነት ያቀጣጠሉትና፣ አንድ ሕዝብ በጊዜው ሰፍኖ በነበረው እጅግ አሰቃቂ ሁኔታ መኖር የለበትም ብለው በተረዱ በከፍተኛ ዕውቀት በታነጹ ምሁራኖች አማካይነት ነው። የነዚህ ምሁራንም ዋና ዓላማ ሥልጣንን መያዝ ሳይሆን በሁሉም መልክ የሚገለጽን ሥልጣኔን ማምጣት ነበር። ዳንቴ፣ ጀርመናዊ ቄስ ኩዟኑስ፣ ፔትራርካ፣ ጋሊሊዮ፣ ዳቪንቺ፣ ሚካኤል አንጀሎና ብሩኖ ጋርዲያኖና፣ ሌሎችም ሺህ በሺህ የሚቆጠሩ ፈላስፋዎች፣ የማቲማቲክስና የተፈጥሮ ሳይንስ ተመራማሪዎች፣ የህንፃና የከተማ ዕቅድ አውጭዎችና፣ ለተፈጥሮ ልዩ ውበት ለመስጠት የሚንቀሳቅቀሱ የተገለጸላቸው ኃይሎች በሙሉ ጭንቅላታቸው በሥልጣን የተሳከርና ሥልጣን ለመያዝ የሚቅበዘበዙ ሳይሆኑ፣ ዋናው ዓላማቸው ሥልጣኔ ወይም ሞት ብለው በመነሳት ዲሞክራሲያዊ ህይወት ሁለንታዊነት ያለውና የተፈጥሮና የህዋን ሕግ በመረዳትና ተግባራዊ በማድረግ ይገለጻል ብለው በማመናቸው ነው ውብ ውብ ነገሮችን ሊሰሩ የቻሉት። አስተሳሰባቸው ልቅ ያለ ሳይሆን በፍልስፍና ላይ የተመሰረተና ስልትን የተከተለ ሳይንሳዊ አካሄድ ነበር።
የሪፎርሜሽንና የኋላ ኋላ ደግሞ በኢንላይተንሜንት የተገለጸውን ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ስንመለከት በጊዜው ከነበረው የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ ባሻገር የተደረጉ በግለሰቦች ተነሳሽነት ተግባራዊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ታሪክ ያረጋግጣል። የግዴታ በተለያየ መልክ የሚገለጹት እንቅስቃቅሴዎች እየተስፋፉና ስር እየሰደዱ ሲመጡ ሥልጣን ላይ ተቀምጠው ድህነትን የሚያራምዱትን መሪዎች መፈናፈኛ አሳጧቸው። የገዢ መደቦችና የኃይማኖት መሪዎች አንዳንድ ሊቃውንቶችን በማቃጠልና በመስቀል እንቅስቃሴውን ሊያግዱት ቢሞክሩም የመጨረሻ መጨረሻ እየተስፋፋ የመጣው እንቅስቃሴና በተጨማሪም ደግሞ ራሱን እየቻለ በማደግ ላይ የሚገኝውን በኢኮኖሚ ተሳትፎነት እየበለጸገ በመጣ ኃይል በመወጠራቸው የሥልጣኔውን ፕሮጀክት በፍጹም ሊያቆሙት አልቻሉም። ይህ ዐይነቱ ሂደት በተለይም የማርቲን ሉተሩ የኃይማኖት ህዳሴ እንቅስቃሴ ብቅ ካለበትና ሰፋ እያለ ከመጣበት ጀምሮ በኃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ መሀከል ያለውን አሰላለፍና የአስተሳሰብ ልዩነት ግልጽ እያደረገው መምጣት ቻለ። በተለይም የፕሮቴስታንት ዕምነትን የተቀበሉት የሕብረተሰብ ክፍሎች በካቶሊክ ኃይማኖት ተከታዮች ላይ በማመጽና አብዮት በማካሄድ ለከበርቴው አብዮትና ለኢንዱስትሪ ካፒታሊዝም በር እንደከፈቱ ግልጽ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንደ ሊበራሊዝም የመሳሰሉት አስተሳሰቦች በመስፋፋትና የከበርቴውን የበላይነት በማወደስ ለካፒታሊዝም ዕድገት የበላይነትን መቀዳጀት ሁኔታውን እንዳመቻቹ እንመለከታለን። እዚህ ላይ ሰፋ ያለ ምሁራዊ እንቅስቃሴና ኃይልም ለሕብረተሰብዓዊ ዕድገትና ለቴክኖሎጂ ምጥቀት ወሳኝ ሚናን እንደተጫወቱ መረዳት ይቻላል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምሁራዊ አስተሳሰቦች እየተስፋፉ በመምጣት እንደ ፖለቲካ ኢኮኖሚክስ የመሳሰሉት ራሳቸውን የቻሉ ዘርፎችና መከራከሪያ ነጥቦች ሆነው በመውጣት እያደገ በመምጣት ላይ ላለው የከበርቴ መደብና የፖለቲካ ተጽዕኖ ማድረግ ለቻለው የሕብረተሰብ ክፍል ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን በስነስርዓት ሊያካሂድና ግለሰብዓዊና ሕብረተሰብዓዊ ሀብት ለመፍጠር የሚችልበትን ዘዴ ማግኘት ቻለ። የሊበራሊዝም አስተሳሰብ ሲስፋፋና ነፃ የገበያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚለው በመንግስት ደረጃ ሲካሄድ ተጠቃሚው ጠቅላላው ሕዝብ መሆኑ ቀርቶ የከበርቴው መደብ ብቻ ሆነ። ይህ ዐይነቱ የነፃ ገበያ ፖሊሲ በእንግሊዝ አገር ድህነት በከፍተኛ ደረጃ እንዲስፋፋ አደረገ። እንደዛሬው የሦስተኛው ዓለም አገሮች አስከፊ ሁኔታዎች በመፈጠር በደሃና በሀብታም መሀከል ያለውን ልዩነት ጉልህ አድርጎ ማሳየት ቻለ።

ይህ ዐይነቱ የሊበራሊዘም አስተሳሰብ ዕውነተኛ ሕብረተሰብዓዊ ነፃነትን ሊያመጣ እንደማይችል የተረዱ የጀርመን ፈላስፋዎች የእንግሊዙን ኢምፔሪሲስታዊ አስተሳሰብ በመቃወምና የራሳቸውን አስተሳሰብ በማዳበርና ከግሪኩ ጋር በማነፃፀር ለጀርመኑ የሥልጣኔ ፕሮጀክት መሰረት ይጥላሉ። ይህንና ግን ይህ ዐይነቱ የሥልጣኔ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለመሆን የግዴታ ሥልጣን በያዙ ኃይሎች ዘንድ ፉክቻን እንዳስከተለና፣ የኋላ ኋላ ከእንግሊዙ ለየት ያለ የሊበራል አስተሳሰብ ያላቸው ኃይሎች የበላይነትን በመቀዳጀት ሰፋ ላለው የሥልጣኔ ፕሮጀክት በር እንደከፈቱና እስከተወሰነም ደረጃ ድረስም የመሬት ከበርቴውን የበላይነት ገፍትረው ለመጣል እንደቻሉ መገንዘብ እንችላለን። ልክ እንደ ጣሊያኑና እንደ እንግሊዙ የኢላይተንሜንት እንቅስቃሴ የጀርመኑም በግለሰቦች የተካሄደና አንድ ቦታ ላይ በመቀጣጠል ቀስ በቀስ ሰፋ ላለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ በር የከፈተ ነው። ኬፕለር፣ ጋውስ፣ ሁለቱ ወንድማማች አሌክሳንደር ሁምቦልድና ቪሊሄልም ሁምቦልድ፣ ሳይንቲስቱና ፈላስፋው ላይቢኒዝ፣ ሺለርና ጎተ፣ ካንትና ሄገል እንዲሁም ማርክስ፣ እነዚህና አያሌ ፈላስፋዎችና የተፈጥሮ ሳይንስ ተመራማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ሥልጣንን ሳይሆን ሥልጣኔን በማስቀደም ሰፋ ላለው የሕብረተሰብ ፕሮጀክት በር የከፈቱ ታላላቅ ምሁራን ናቸው። በእነሱ የምርምር ዘዴና የቴክኖሎጂ ግኝት አማካይነት ነው ካፒታሊዝም ቀስ በቀስ የበላይነትን ሊቀዳጅ የቻለው። ይሁንና ግን የእነዚህ ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶች ምርምርና ዕውቀት ዓለም አቀፋዊ (Universal) ሲሆን፣ ዓላማቸውም በዓለም ማኅበረሰብ ዘንድ ሰላምና ስምምነት እንዱሁም ሥልጣኔ እንዲዳረስ ማድረግ ነበር። ዓላማቸውም ካፒታሊዝምን ማሳደግ ሳይሆን በቴክኖሎጂ ምጥቅት አማካይነት የሰውን ልጅ ኑሮ ለማሻሻል ነበር። ትምህርታቸው ዓለም አቀፋዊ እንጂ ብሔራዊ እንዳልሆነ ጹሁፋቸውን ላነበበ መረዳት ይቻላል። አስተሳሰባቸው ከማንኛውም ተንኮልና ዕቡይ አስተሳሰብ ውጭ የነበረና ሰብዓዊነትን ያካተተ ከፍተኛ የጭንቅላት ሥራ መሆኑን እንረዳለን።

ይህ ዐይነቱ ሰፋ ያለና ስር የሰደደ ምሁራዊ እንቅስቃሴ በአስተሳሰቡ የዳበረ፣ የፖለቲካን ትርጉም የተረዳና ብሔራዊ ባህርይ ያለው የሕብረተሰብ ክፍል ብቅ እንዲልና፣ ፊዩዳላዊ አስተሳሰብ ያለውንና ዕድገትን የሚቀናቀንን ኃይል ገፍትሮ በመጣል ኃይሉን ሁሉ በኢንዱስትሪ አብዮት ላይ በማትኮር ብሔራዊ ኢኮኖሚ እንዲገነባ ማድረግ እንዳስቻለው መገንዘብ ይቻላል። ይህ የሕብረተሰብ ክፍል የተገለጸላቸውን የሚሊታሪና የሲቪል ሰዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የእነዚህ ምሁራን ዋና ዓላማ ርስ በርስ መሻኮትና ተንኮል በመሥራት ብሔራዊ አጀንዳን ማጨናገፍ ሳይሆን አንድ ሕብረተሰብ እንዴት አድርጎ በጠነከረ መሰረት ላይ ሊገነባ ይችላል በሚለው ላይ ያተኮረ ነበር። ሃርደንበርግ፣ ፍራይኸር ፎን ስታይን፣ ቢስማርክ፣ ግናይዘናውና ሻርንሆርስት፣ አርኪተክቸሩ ሺንክል፣ ኢንጂነሩ ቦይትና ሌሊች የሲቪልና የሚሊታሪ ሰዎች ሰፋ ያለውና ጥልቀትን ያገኘው የምሁራዊ እንቅስቃሴ ውጤቶች ናቸው። እነዚህ ምሁራን በጊዜው ቀድመው የሄዷቸውን እንግሊዝንና ፈረንሳይን በመጎብኘት ከተመለሱ በኋላ ከእነሱ የተሻለና ጥበባዊ ሕብረተሰብ መገንባት አለብን ብለው በቆራጥነት የተነሱ ታላላቅ ሰዎች ናቸው። ዕውቀታቸውም ሁለ-ገብና የጠለቀ በመሆኑ ሥራዎቻቸው በሙሉ ዘላቂነት ያለውና ጥበባዊ ነበር። ስለሆነም ከዚያ በኋላ የተነሳው ተከታታይ ትውልድ አገሩን በዚያው ላይ ተመርኩዞ ለመገንባትና ለማጠናክር ከፊቱ የተደቀነ አስቸጋሪ ሁኔታ አልነበረበትም። ይሁንና እንደዚህ ዐይነቱ ፖለቲካ በአውሮፓ ውስጥ ተመሳሳይነት አልነበረውም። ብሔራዊ ባህርይን ባላዳበሩ እንደነ ፖርቱጋልና ስፔይን የመሳሰሉ አገሮችና በዓለም አቀፍ ደረጃ ወርቅና ብርን በመዝረፍ ባተኮሩ አገሮች ወደ ውስጥ በቀጥታ ብሔራዊ ባህርይ ያለው መደብ እንዳይፈጠር እንቅፋት በመፍጠር ዕድገትን አጨናግፈዋል ማለት ይቻላል። የተገለጸላቸውንና ከፍተኛ ዕውቀት ያላቸውን በተለይም አይሁዲዎችን በማባረር ዕድገትን ለማጨናገፍ በቅተዋል። እነዚህ ኃይሎች ሆላንድና እንግሊዝ አገር በመሰደድ ለዕድገትና ለሥልጣኔ መሰረት ሊጥሉ ችለዋል።

ከዚህ ሁሉ እጅግ አጠር መጠን ብሎ ከተዘረዘረው ምሁራዊ እንቅስቃሴ የምንረዳው ቁም ነገር ለሥልጣን የሚታገሉና ሥልጣኔን ተግባራዊ እንዲሆን የሚታገሉ ኃይሎች የተለያየ ዓላማ እንዳላቸው ነው። በተጨማሪም አንድ የሕብረተሰብ ኃይል ብሄራዊ ባህርይ ለመያዝና ሰፋ ያለ የሥልጣኔ ፕሮጀክት ለመንደፍ ራሱ ሰፋ ያለ የምሁራዊ እንቅስቃሴ ውጤት መሆን አለበት። ዕድገትንና ሥልጣኔን ሁለመንታዊ በሆነ መልክ ለመረዳት ሁለ-ገብ የሆነ ምሁራዊ እንቅሳቅሴ ለአንድ ሕብረተሰብ ቀሰ በቀስና እንዲሁም በሰከነና በጠነከረ መሰረት ለመገንባት ዋናውና መሰረታዊ ቅድመ-ሁኔታ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። በሌላ ወግን ደግሞ ሥልጣን ላይ የተቀመጡ ኃይሎች የፖለቲካ ስልትና አካሄድ በኃይል አሰላለፍ መለዋወጥ እንደሚለወጥና፣ በኢኮኖሚ ጠንከር ብሎ የሚገኘው የሕብረተሰብ ክፍል በፖለቲካው መስክ ላይ ተጽዕኖ ማድረግ እንደሚችልና የዕድገትንም አቅጣጫ ለሱ በሚስማማው መልክ ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ እንደሚችል ከአውሮፓው የሕብረተሰብ ግንባታ ታሪክ ውስጥ መማር ይቻላል። ስለሆነም ለሥልጣን የሚታገሉና ሥልጣንም ላይ ቁጥጥ የሚሉ ኃይሎች ዕድገት የሚለውን ፕሮጀክት የሚረዱትና ተግባራዊም የሚያደርጉት በተወሰነ መልክ ብቻ ይሆናል። አስተሳሰባቸው የፖለቲካን ትርጉም ከሥልጣን መያዝ ብቻ ጋር ስለሚያያይዙትና ሥልጣንንም ቶሎ ብለው ላለመልቀቅ ስለሚፈልጉ የሆነ ያልሆነ ዘዴ በመፈለግ አንድን ሕዝብ መሉ በሙሉ ነፃ ሊያወጣ የሚችለውን የሥልጣኔ ፕሮጀክት አሽቀንጥረው ይጥላሉ። በተለይም ዕውቀት የሚባለውን ነገር በሌላ መልክ በሚተረጉሙትና ወደ ርዕዮተ-ዓለምነት በሚለውጡ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አማካሪዎች በሚከበቡበት ጊዜ ሳይወዱ በግድ የተወሰነ ሕብረተሰብ-ክፍልን ጥቅም ብቻ የሚያንፀባርቅ ፖሊሲ በማውጣት ተግባራዊ ያደርጋሉ። በዚህም መልክ የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ተጣሞ እንዲቀር በማድረግ በአንድ ሕብረተሰብ ውስጥ የሀብት ክፍፍል በተዛባ መልክ እንዲዳረስ ያደርጋሉ። በሌላ ወገን ግን በከበርቴው ሕብረተሰብ ውስጥ ሰፋ ያለ የሲቪል ማኅበረሰብ ስለዳበረና በየጊዜው የሚከሰቱ መዛባቶችን ስለሚያጋልጥ ሥልጣንን የጨበጡ ኃይሎች እንደፈለጉት የአንድን ሕብረተሰብ ጥቅም የሚያስጠብቅ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ብቻ በቀላሉ ተግባራዊ ሊያደርጉ አይችሉም።

ያም ሆነ ይህ ዕድገት ሁለንታዊ ባህርይ እንዲኖረው ከተፈለገ ሰፋ ባለ ምሁራዊ እንቅስቃሴና ክርክር መደገፍ እንዳለበት ከአውሮፓው የሕብረተሰብ አገነባብ ታሪክ መገንዘብ ይቻላል። በሁሉም መልክ የሚገለጽ በጭንቅላት ምርምር ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ በማይካሄድበት አገር ዕውነተኛ የሥልጣኔ ፕሮጀክት በፍጹም ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። በተለይም በአሁኑ ዘመን በካፒታሊዝም መስፋፋትና በኒዎ-ሊበራሊዝም አስተሳሰብ የሁላችንንም ጭንቅላት በያዘበትና በሚያሽከረክርበት ዘመን የግዴታ የሃሳብ ጥራት እስከሌለና ህይወትንም እስከማጣት የሚያደርስ ድፍረት የተሞላበት ክርክር እስካልተካሄደ ድረስ አንድ ሕዝብ ዕውነተኛ ነፃነትንና ሥልጣኔን ሊጎናጸፍ በፍጹም አይችልም። ስለዚህም ትግሉ ሥልጣኔን በሚመኘው ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብና፣ በዚህም በዚያም ብሎ የሕዝባችንን ህልምና ምኞት ለማኮላሸት እዚህና እዚያ በሚሯሯጠው፣ ይህንን ወይም ያንን የፖለቲካ ፓርቲ ስም በያዘ መሀከል የሚደረግ የሞት-የሸረት ትግል ነው ማለት ይቻላል። ወደድንም ጠላንም የወደፊቱ ትግልም ሥልጣኔን በሚመኙትና፣ ተግባራዊ ለማድረግ በሚፈልጉ በአንድ በኩል፣ በሌላ ወገን ደግሞ ሥልጣንን ለመያዝ በሚሽቀዳደሙና ዕውነተኛ ዕድገት እንዳይመጣ በሚፈልጉ ኃይሎች መሀከል ይሆናል።

በአገራችን ምድር ለዲሞክራሲና ለሥልጣን የተደረገውና የሚደረገው ትግል

የአገራችንን የፖለቲካ ትግል ታሪክ ለተገነዘበ ሰፋ ባለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ላይ የተመረኮዘ እንዳልሆነ በራሱ በተማሪው ማኅበር ይወጡ የነበሩ ታገልና ታጠቅ የሚባሉትን መጽሔቶች ላገላበጠ መረዳት ይቻላል። ከጽሁፎቹ ይዘት መረዳት የሚቻለው የመሬት ላራሹ ጥያቄ፣ የዲሞክራሲና የብሔረሰብ ጥያቄዎች ዋናውን ድርሻ ሲይዙ፣ ለአገራችን ዋናው የዕድገት እንቅፋቶች ፊዩዳሊዝም፣ ቢሮክራሲያዊ ካፒታሊዝምና ኢምፔሪያሊዝም ናቸው የሚሉ አስተሳሰቦች ነበሩ። ሌሎች አስተሳሰቦች የሚስተጋቡ ቢሆንም፣ በእነዚህና በሌሎች የሕብረተሰብ ጥያቄዎች፣ በተለይም የመንግስት አወቃቀርና የዕድገት ጠንቅ መሆንና በአገሪቱ ውስጥ በተበላሸ የኢንዱስትሪ ፓለቲካ አማካይነት እንዴት የተዛባ ዕድገት የሚመስል ነገር እንደተፈጠረና የተወሰነውንም የሕብረተሰብ ክፍል የህሊና አውቃቀር እንደበረዘውና እንዳዘበራረቀው በደንብ ተብራርቶ ውይይትና ክርክር የሚካሄድበት የምሁራዊ እንቅስቃሴ አልነበረም። በተጨማሪም ለአገራችን የሚስማማና ሕዝባችንን ከድህነት አውጥቶ ወደ ከፍተኛ ደረጃ በሚያደርሰው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ ውይይትና ከርክር ይካሄዱ እንዳልነበሩ ዶኩሜንቶች ያረጋግጣሉ። ራሱ የተማሪው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ፊዩዳሊዝምና ውጥንቅጡ የወጣ ካፒታሊዝም ውጤት በመሆኑ እንደ አውሮፓው የምሁር እንቅስቃሴ ነገሩን ሰፋ አድርጎ በማየት ተከታታይነት ለሚኖረው የሥልጣኔ ፕሮጀክት ሊታገል አልቻለም። በኋላ ላይ የአስተሳሰብ አለመግባባት ሲፈጠር የሚወጡት ጽሁፎች ትምህርታዊ መሆናቸው ቀርቶ የእንካ ስላንቲሃ በመሆን የፓለቲካ ትግሉን መንፈስ መበረዝ ቻሉ። ይህ ጉዳይ የኋላ ኋላ አብዮቱ ሲፈነዳ የባሰበትና ወደ ርስ በርስ ጦርነት እንዲያመራ ያደረገ ሁኔታ ነው። ከክርክርና ከውይይት ይልቅ የጊዜው ጥያቄ የመሳርያ ጥግል ጥያቄ ነው በሚለው ላይ በማትኮሩ የጠቅላላውን የአብዮት ሂደት መልኩን ሊቀይረው ችሏል። ለዚህ አስከፊ ሁኔታ መፈጠር ደግሞ ሁሉም የተማሪው እንቅስቃሴ መሪዎች ተጠያቂ ሳይሆኑ፣ በዚህም በዚያም ብሎ ሥልጣን ላይ ለመውጣት የሚሽቀዳደመውና፣ ከዚህም ሆነ ከዚያኛው ብሔራዊ አጀንዳ ከሌለው የብሔረሰብ እንቅስቃሴ ጋር የተባበረውና ኃላፊነት የጎደለው የጦር ትግል የሚሉትን ፈሊጥ ማካሄድ የጀመረው ኃይል ነው ተጠያቂው።

አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ በተማሪው እንቅስቃሴ ውስጥ የታየውና ወደ ጦርነት ያመራው መከፋፈልና መገዳደል በወታደሩ ውስጥ በመስፋፋቱና ወታደሩን በመከፋፈሉ አመኔታ እንዳይኖር አደረገ። ወታደሩ ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ በመከፋፈሉ ርስ በርሱ እንዳይተማመን ተደረገ። በጊዜው የተፈጠሩት ወይም ብቅ ያሉት አምስት የማርክሲስት-ሌኒንስት ድርርጅቶችና ከውጭ ሆኖ የሚታገለው ኢህአፓ የወታደሩና የተቀረውን የሕብረተሰብ ክፍል ርስ በርስ በመቀራመት ለቡድናዊ ስሜት መዳበርና የኋላ ኋላ ለርስ በርስ መገዳደል አመቺ ሁኔታን ፈጠሩ። ዋናው ዓላማቸውም ብሔራዊ አጀንዳን መከተልና ኃይልን ሰብስቦ ወደ አገር ግንባታ ላይ ከመሰማራት ይልቅ ሁሉም ድርጀት ራሱን ለማጠንከር ሲል ካድሬዎችን በመመልመልና በማግበስበስ ሕብረተሰብዓዊ ቅራኔውን አስፋፉት። በዚህ ላይ ሲአይኤ (CIA) የራሱን ሥራ ይሰራ ስለነበር በአንድ በኩል አብዮቱ ሊጨናገፍ የሚችልበትን ሁኔታ ከውስጥ ሲሰራ፣ በሌላ ወገን ደግሞ የብሔረሰብ እንቅስቃሴዎች የሚባሉትን በማስታጠቅና ጦርነቱ እንዲፋፋም በማድረግ ቢያንስ ለዕድገት የተነሳሳው ኃይል አትኩሮው በሱ ላይ ብቻ እንዳይሆን አደረገው። ሽኩቻው ሥልጣን ከመያዝ አልፎ እንዴት አድርጎ ራስንና ድርጅትን ማዳን ይቻላል በሚለው ላይ አተኮረ። የኋላ ኋላ የወታደሩ አገዛዘ ራሱ በጠፈጠፈውና ከዚህም ከዚያም ባግበሰበሰው ኃይል በመታገዝ የተቀረውን ምሁራዊ ኃይል በመደምሰስ አገሪቱን የምሁር አልባ አደረጋት። የወታደሩም ዋና ዓላማ አገርን መገንባት ሳይሆን እንዴት አድርጌ ሥልጣን ላይ መቆየት እችላለሁ በሚለው ላይ ያተኮረ በመሆኑ በተለይም ለውጭ የስለላ ድርጅቶች በሚሰሩ በመከበቡና ወታደሩም በጦርነት በመዳከሙና ራሱም በሰላዮች በመቦርበሩ ውድቀቱን አፋጠነው። ወያኔና ሻቢያ በሲአይኤ በመታገዝና ሥልጣንን በመጨበጥ የኢምፔሪያሊስት ፕሮጀክቶችን ማካሄድ ጀመሩ። ጨቅላ አስተሳሰባቸውን ተግባራዊ በማድረግ አገራችን ከውስጥም ተዳክማ በውጭ ኃይሎች በቀላሉ ልትጠቃ የምትችልበትን ሁኔታ አመቻቹ። አጀንዳቸውም ሁሉ ጠንካራ የሆነ ብሔራዊ ኢኮኖሚና ሕብረተሰብ እንዳይገነባ ማድረግ ነበር፤ ነውም።

ከፖለቲካው ፕሮጀክት ባሻገር በአገራችን ምድር የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ መሆን ብሔራዊ ባህርይ ያለውና ብሔራዊ ሀብት ሊፈጥር የሚችል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተግባራዊ እንዳይሆን በመታሰቡ ነው። በጊዜው ይህንን ፖሊሲ የሚቃውም የነቃና የገባው ኃይል ባለመኖሩ እነ መለሰ ዜናዊ ከእነ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና (IMF) የዓለም ባንክ ጋር በመመካከርና ትዕዛዝ በመቀበል ተግባራዊ በማድረግ ራሳቸው ሊናጥጡና ሕብረተሰቡን ሊያራቁቱት በቁ። ከዚህም መገንዘብ የምንችለው ለሥልጣን የሚስገበገብና በተለይም ደግሞ በቂም በቀል የተወጠሩ ኃይሎች የሥልጣኔ ተልዕኮ እንደሌላቸው ነው። ራሳቸው ወያኔና ሻቢያ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ የማቴሪያል ሁኔታና የባህል ውጤቶች በመሆናቸው ሰፋ ያለና ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ የሚያመች ብሔራዊ ፕሮጀክት በፍጹም ሊኖራቸው አይችልም። ከሌላው ተነጥለው በራሳቸው ዓለም ብቻ ሊኖሩ የሚችሉ ስለመሰላቸው ሰፋ ያለ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የውስጥ ገበያ እንዳይገነባ የዘረፋ ተግባራቸውን አጧጧፉት። ራሳቸውንና ብሔረሰባቸውን የጠቀሙ ስለመሰላቸው ባካሄዱት የተፈጥሮንና የሕብረተሰብ ሕግን በሚጻረር አጉል ፖለቲካቸው የራሳቸውንም ዜጋ በመንፈስም ሆነ በማቴሪያል አራቆቱት። በርግጎ እንዲኖር አደረጉት። ነፃነት እንዳይሰማው አደረጉት።

እስከ ግንቦት 7 ድረስ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ ስንመለከትና በጊዜው መጽሔቶች ላይ ይወጡ የነበሩትን ጽሁፎች ስንመረምር እስከዚህም ድረስ በሰፊው ለማሰብ የሚረዱ የሥልጣኔን መልዕክቶች ያዘሉ እንዳልነበሩ ማረጋገጥ እንችላለን። በተለይም አገዛዙ ተግባራዊ ባደረገው በኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ አንዳችም ትችት አይቀርብም ነበር ማለት ይቻላል። ያም ሆነ ይህ በ1997 ዓ.ም የተካሄደው የግንቦቱ 7 ምርጫ የመጨረሻ መጨረሻ በእነ መለስ ዜናዊ የተጨናገፈ ሳይሆን ራሳቸው በአሸናፊነት በወጡት የቅንጅት መሪዎች ሁኔታውን በቅጡ ባለመረዳታቸውና፣ በተለይም ደግሞ በውጭ ኃይሎች በመመከርና በመተማመን ለሥልጣኔ ሳይሆን ለሥልጣን በመስገብገባቸውና የውስጥ ሽኩቻ በመጀመራቸው ነው። ቀደም ብለው በደንብ የተዘጋጁ ኃይሎች ባለመሆናቸውና ብሔራዊ ባህርይንም ያላዳበሩ በመሆናቸው ለሕዝባችንና ለአገራችን ጠበቃ በመሆን ከውስጥ የሚደረገውን ትርምስና ከውጭ የተቀነባበረብንን ሴራ ለመዋጋት የሚያስችል ሳይንሳዊ መሳሪያ አልነበራቸውም። ስለሆነም በእነሱ የስትራቴጂ ስህተት የኢትዮጵያ ሕዝብ 12 ዓ.ም ያህል እንዲሰቃይ ተደረገ። በራስ ያለመተማመንና በውጭ ተማምኖ ሰፊውን ሕዝብ መናቅ የመጨረሻ መጨረሻ ልንወጣ የማንችለው ማጥ ውስጥ እንደከተተን መረዳት እንችላለን።

ከአብዮቱ መክሸፍ በኋላና ከግንቦቱ ሰባት ምርጫ ድል መነጠቅ በኋላ አሁንም ቢሆን ተቃዋሚ ነኝ የሚለው ኃይል ብዙም የተማረው ነገር የለውም። ዋናው ዓላማም ሥልጣኔን ማምጣት ባለመሆኑ ኃይልን ወደሚሰበስብ ሰፋ ወዳለ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ሊያመራ በፍጹም አልቻለም። እዚህና እዚያ የሚመሰረቱት ፓርቲዎች ነን የሚባሉት ነገሮች በመሰረቱ የግለሰብ ኩባንያዎች የሚመስሉ እንጂ በደንብ ተደራጅተው የሚያስተምሩና የሚማሩም አይደሉም። በዚህ ዐይነቱ ፊዩዳላዊ ጨዋታቸውም ተከታታይነት ያለውና የጠነከረ፣ እንዲሁም ታሪካዊ ኃላፊነትን ሊሸከምና የሥልጣኔ ፕሮጀክት ሊነድፍ የሚችል ድርጅት እንዳይፈጠር እያገዱ ነው። እዚህና እዚያ የሚደረጉት „የትብብር ሥራዎችና የአንድነት መፈክሮች“ ሰፋ ያለ ምሁራዊ መሰረት ያላቸው አይደሉም። ሰፋ ካለ ምሁራዊ ክርክርና ውይይት በኋላ የተፈጠሩም ባለመሆናቸው ስለ ወደፊቱ የሕብረተሰብ ዕድገትና የሥልጣኔ ፕሮጀክት፣ ስለዲሞክራሲና ስለ ግለሰብዓዊ ነፃነት፣ ስለሳይንስና ስለቴክኖሎጂ፣ ስለከተማዎችና ስለመንደሮች በዕቅድ ስለመገንባት ጉዳይ፣ ለሕዝባችን መሰረታዊ ፍላጎቶችን በቅድሚያ ስለማሟላት ጉዳይና፣ እነዚህንም ተግባራዊ ለማድረግ ምን ምን እርምጃዎች በቅድሚያ መወሰድ አለባቸው በሚለው ላይ ውይይትና ክርክር እንዲሁም ጥናት ስለማይካሄድ ስብስቡ ሥልጣን ከመያዝ የሚያልፍ አይመስለም።

ከዚህ ስንነሳ ያለው አማራጭ አንድ ብቻ ነው። የአንድ አገር ዕድገት ሊወሰንና መስመር ሊይዝ የሚችለው ሰፋ ባለ ምሁራዊ ኃይል በመሆኑ ሥልጣንን ስሌቱ ውስጥ ያላስገባ ምሁር ሁሉ በየሙያው የየበኩሉን አስተዋጽዖ ማድረግ አለበት። ይህ ዐይነቱ ምሁራዊ እንቅስቃሴ በስዕል፣ በአርኪቴክቸር፣ በሊትሬቸር፣ በድራማ፣ በተፈጥሮ ሳይንስና በፍልስፍናና በሌሎችም የሚገለጽ መሆን ሲገባው፣ ማንኛውንም ለፖለቲካ ሥልጣን ብቻ የሚታገለውን መፈናፈኛ የማያሳጣው መሆን አለበት። ከሁሉም አቅጣጫ ግፊት ሲመጣ የፖለቲካው መድረክ አስተሳሰቡ በመስፋት ለሃሳብ መንሸራሸር አመቺ ሁኔታ ይፈጠራል። ይህ ዐይነቱ ሁኔታ በሌለበት አገር፣ የዛሬው አገዛዝ ቢወድቅም እንኳ ሁኔታው በዚያው መልክ ይቀጥላል ማለት ነው። የብዙ የሦስተኛው ዓለም አገሮች ልምድ ይህንን የመሰለውን ሁኔታ ነው የሚያስተምረን።

ስለሆነም አገራችንን ዛሬ ካለችበት የተወሳሰበ ችግር አውጥተን ሰፋ ባለ መሰረት ላይ ለመገንባት ከፈለግን የፖለቲካ ሥልጣን አሁኑኑ ከሚለው ስንኩል አስተሳሰብ መላቀቅ አለብን። ከቡድናዊ ስሜትና ከራስ ኤጎ በመላቀቅ ተሰባስቦ መከራከርና መወያየት እጅግ አስፈላጊ ነው።፡የዓለም የፖለቲካ ሁኔታ እጅግ አወዛጋቢ እየሆነ በመምጣቱና፣ በተለይም ደካማ አገሮች የመበታተናቸው ሁኔታ አመቺ በመሆኑ የግዴታ የአስተሳሰብ አድማስን ማስፋትና በሁሉም ሕብረተሰብን በሚመለከቱ ነገሮች ላይ መወያየትና መከራከር የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። አገርን በሚመለከት ጉዳይ ላይ ይሉኝታ የተሞላበት ፖለቲካ ትክክለኛው አካሄድ ስላልሆነ ሁሉም በድፍረት የሚፈልገውንና የሚያምንበትን ርዕዮተ-ዓለም በግልጽ ውጭ አውጥቶ ማስተማርና ለማሳመን መሞከር አለበት። በደፈናውና በጨዋነት የሚካሄድ ትግል የሚሉት ፈሊጥ ውጤቱ የሚያምር አይሆንም።

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)
ታህሳስ 14፣ 2016
fekadubekele@gmx.de

Saturday, November 26, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ኮማንደር ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ለትግራዩ መንግስት ጦር እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን ሰዋ

በሰሜን ጎንደር ከአማራ ታጋዮች በተጨማሪ ውጊያ እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 በአርማጭሆ አብደራፊ ባደረገው ውጊያ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ (ገብርዬ) በሕወሓት ወታደሮች በተከበበት ወቅት እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን በያዘው ጠመንጃ ማጥፋቱ ተሰማ::
ምንጮች እንዳሉት በሰሜን ጎንደር በተለያዩ ግንባሮች የአማራ ገበሬዎች እና የአርበኞች ግንቦት 7 የሕወሓትን መንግስት እየተዋጉት ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ኮማንደር የነበረው ሻለቃ መሳፍንት በአብራፊ የሄደውን አርበኞች የግንቦት 7 ጦር ሲመራ እንደነበር የዘ-ሐበሻ ምንጮች ያስታወቁ ሲሆን የህወሓት ጦር በሜካናይዝ ደረጃ ቢከበውም ራሱን አጥፍቷል:: ሆኖም ግን እርሱ ይዞት የገባው ጦር ይህ ዜና እስከተሰማበት ጊዜ ድረስ እየተዋጉ ይገኛሉ::
እንደ ምንጮች ገለጻ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ወደ ኤርትራ ሄዶ አርበኞች ግንቦት 7ን የተቀላቀለው የተደላደለ ኑሮውን ከአውሮፓ ሉክዘምበርግ ትቶ ነው::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በሰሜን ጎንደር እያደረኩት ባለሁት ውጊያ የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት ለጊዜው የመሸግኩበትን ቦታ በሄሊኮፕተር ቢደበድብም መክቻቸዋለሁ ሲል መግለጫ ማውጣቱን  አይዘነጋም::
በሌላ ዜና በዚሁ አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዋጉ የሚገኙትን የአማራ ታጋዮችን በርካታ ሕዝብ እየተቀላቀላቸው መሆኑን የደረሰው መረጃ አመልክቷል:: በጎንደር የተለያዩ ግምባሮች ወያኔን እየገጠሙ የሚገኙት የአማራ ታጋዮች በአንድነት ወያኔን ለመውጋት ተስማምተው በጋራ ስር ዓቱን እያርበደበዱት እንደሚገኙም ተሰምቷል::

15109542_10210938344445355_8898449061103277225_n

wanted officials