በጎንደር እየተደረገ ያለውን ትግል፤ “የአማራው ገበሬ ትግል” “የአርበኞች ግንቦት 7 ትግል እያላችሁ” አታክሽፉት – እነዚህን 3 ነገሮች እየመረሯችሁም ቢሆን ተቀበሏቸው
ከደረሰ ለማ
ወያኔ የተባለውን የጥፋት ሃይል አስወግዶ ነፃ ለመውጣት ከተፈለገ የራሳችንን ፍላጎትና ምኞት ትተን 3 ነገሮችን ሁላችንም እየመረረንንም ቢሆን የግድ መቀበል ይገባናል።
1. ግንባር /ህብረት/ ቅንጅት መፍጠር ወያኔን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን ከዛም በኋላ ለሚመጣው ሽግግር እና ሁሉን የወከለ አስተዳደርና ሥርዐት መመስረት የግድ አሥፈላጊ ነው።
ይህ ሲሆን ታዲያ ከሁሉ በላይ ዋናው መመዘኛ ሊሆን የሚገባው በሃገሪቱ አንድነት ውስጥ ችግሮችን ሁሉ እንፈታለን ብሎ መቀበል ነው። ሌሎች ጉዳዮች ውስጥ በዝርዝር ገብቶ ለመወሰንም ሆነ ለመስማማትም ወይንም ላለመስማማትም በመሰረቱ ስልጣኑ የህዝብ እንጂ የቅንጅቶች የህብረቶች ወይንም የግንባሮች መሆን የለበትም።
አ.ግ7ትም ከመነሻው ያለው ህዝቡ የሚፈልገውን በትክክልኛ የምርጫ ሂደት የሚመርጥበትን ዲሞክራሲያዊ ሥርዐት እንዲመጣ እታገላለሁ እንጂ ይሄ የኢኮኖሚ ይሄ የአስተዳደር ይሄ የትምህርት ወዘተ… ፖሊሲ ነው ሥራ ላይ መዋል ያለበት የእኔ ፕሮግራም ነው ልክ ብሎ አይደለም የተነሳው።
ስለዚህ በእነዚህ መስረታዊ መርሆች ላይ ሃገር አንድ ናት መገንጠል አላማዬ አይደለም ካሉና ህዝብ በትክክል ይምረጥ/ይወስን ብለው ከሚስማሙ ጋር ግንባር መፍጠር እጅግ የሚደገፍ ቅዱስ ሃሳብ ነው። ደግሞስ ተቀራርበው እየተነጋገሩ ችግሮችን እና የሚያለያዩ ነገሮችን በውይይት እያስተካከሉ ለመሄድ እድል ካልተፈጠረ እዛ ማዶና እዛ ማዶ ሆነው እንዴት በህብረት መቆም ይቻላል? እንዲህ ተቀራርበው ቢያንስ ግንባር ፈጥረው ትግሉን በጋራ ማካሄድ ወሳኝ ነው።
2. በመሬት ላይ ያለውን እውነታ እየመረረም ቢሆን በግድ መቀበል ያስፈልጋል። ይህም በሁለት ወገን ነው።
ሀ. በትክክልም ይሁን በሸፍጥ የሆነውን እና ከእንግዲህ ሊቀለበስ የማይችልን ታሪክ የሆነን ድርጊት መቀበል የግድ ነው። ለምሳሌ የኤርትራ ጉዳይ። ኤርትራ ራሷን የቻለች ሃገር መሆኗን አሰብም ሆነ ባድሜም የኤርትራ መሆናቸውን ያመነበትም ያላመነበትም በውድም በግድም መቀበልና እንኳን አሁን ወደፊትም ቢሆን በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ወሳኙ የኤርትራ ህዝና መንግሥት ብቻ እንደሆነ ማመን የግድ ነው።
አንዳንድ ሰዎች ይህን ለመዋጥ ሲቸገሩ ይታያሉ። ነገር ግን ይህ ጉዳይ በስህተት የሆነ ነው እንኳን ቢባል ተጠያቂውና ዋጋም ሊከፍል የሚገባው ወያኔ እንጂ ሌላ ተጠያቂ የለም።
ወያኔ ግን ራሱ አሳልፎ የሰጠውን ወደብና ግዛት የኢትዮጵያ ነው እናስመልሳለን በማለት ተቃዋሚዎችም ይህንን ሃሳብ እንዲያንጸባርቁ በማድረግ ከኤርትራ ጋር በማጣላት ምንም አይነት በሃይል ለሚደረግ ትግል መንቀሳቀሻ እና ድጋፍ እንዳያገኙ ለማድረግ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው። ይህንን ጉዳይም ታሪክ እንደሆነ ለመቀበል ያልቻሉ ሰዎች ከሻአቢያ ጋር መተባበርን ሲኮንኑ በወያኔ ወጥመድ ወድቀው ባርነትን ለዘለቄታው ፈርመው ሲቀበሉ ይታያሉ።
ስለዚህ የኤርትራ ጉዳይ የሞተና ያለቀለት ስለሆነ ወደፊትም ወሳኙ ኤርትራውያን ብቻ መሆናቸውን ተቀብሎ ወያኔን ለማስወገድ በሚችሉት ሁሉ ሊረዱን ከተስማሙ እድሉን ማባከን ጅልነት ብቻ ሳይሆን በወያኔ እስከ ወዲያኛው ለመገዛትም መስማማት ነውና ይህ ሊስተካከል ይገባዋል።
ለ. የተቃዋሚ ድርጅቶች አደረጃጀትን አስመልክቶም ሳንወድ በግድ መቀበል ያለብን ጉዳይ አለ። ይህም በጎጥ/ዘውግ መደራጀትን ይመለከታል። በመሬት ያለው እውነታ ብዙዎቹ ድርጅቶች በብሄር የተደራጁ ናቸው። ይህ አደረጃጀት የሚደገፍ አይደለም። ይሁን እንጂ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ይህን ቀይረው አሁኑኑ ህብረ ብሄር እንዲሆኑ ማሰብ ፈጽሞ የማይሆን ነው። ይህ ራሱን የቻለ ረዢም ጊዜና ከፍተኛ ትግል የሚጠይቅ ነው። አሁን ይህ ይሰራ ወይንስ ከወያኔ ጋር ትግል ይደረግ? ይህ ረዥም ጊዜ የሚፈልግ ብቻ ሳይሆን ችግሩን ለማስወገድ መጀመሪያ ቢያንስ ዋና በሆነው በመሰረታዊ የዜግነት/ኢትዮጵያዊነት ማንነት ላይ መተማመን ከተደረሰ ተቀራርቦ ጸረ ወያኔ ትግሉን በጋራ አድርጎ ወደፊት በህብረት መቀጠሉ እንደሚሻል ማመን እና መቀበል ያስፈልጋል።
ወያኔ ለማጭበርበርም ቢሆን ይህን አድጎ ነው ሃገሪቱን የተቆጣጠረው። የኦሮሞ የአማራ የደቡብ ድርጅቶች ብሎ ምርኮኞችን እና የድል አጥቢያ አርበኞችን ሰባስቦ ነው ኢህአዴግ የሚል ታፔላ ለጥፎ በማስመሰል በአንድ ቡድን ፍጹም የበላይነት የሚታዘዝ ግንባር የመሰረተው።

በአንጻሩ ከዚህ ጋር የተያያዘው እና የዚህ ሃሳብ እና አካሄድ ተቃራኒ ሄሆነ አመለካከት የያዙ ሰዎች ሊያውቁት እና እርማቸውን ሊያወጡበት የሚገባ ጉዳይም አለ።
ይህም ከእንግዲህ ወዲያ ኢትዮጵያ እንደ ድሮው በአሃዳዊ ሥርዐት ከማእከላዊ መንግሥት ብቻ በሚመጣ የአስተዳደር ሥርዐት አትመራም።
ወደፊት ሊሆን የሚችለው ትክክለኛ ፌዴራላዊ ሥርዐት ብቻ ነው። ይህ ሥርዐት ግን እንገነጠላለን ወይንም ይህ የእኛ ሃገር/ክልል ነው ወሳኞቹ እኛ ብቻ ነን የሌሎች ብሄረሰብ አባላት እንደ ዜጋ ሳይሆን እንደ ስደተኛ ወይንም ቱሪስት በእነርሱ ፈቃድና ችሮታ በየአካባቢው መኖር ይችላሉ የሚባልበት ጠባቦች የሚመሩት መሆን የለበትም። በቅድሚያ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን ሃገሪቷም የሁላችንም ነች በየትም ቦታ እና የአሥተዳደር ወሰን ውስጥ ከኖረ ማንኛውም የዛ አካባቢ የአስተዳደር ጉዳይ ይመለከተዋል ጎጥን መሰረት ሳያደርግ ሁሉንም ያገባዋል ብለው በሚያምኑ የሚመራ እንዲሆን ማድረግ ነው መፍትሔው።
ዘውግን መሰረት ሳያደርግ የመኖር የመስራት የመንቀሳቀስ ወዘተ… መብቶች ሁሉም ዜጋ አለው ብለው የሚያምኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች በየአካባቢው እስከተመረጡ ድረስ ችግር አይኖርምና ይህን አይነት ሥርዐት እንደሆነ የሚመጣው መቀበል ይገባል።
3. ወያኔን ለማስወገድ የትግል ስልት እና የሃይል አሰላለፍ ሚዛንን በስሜት ሳይሆን በስሌት ማየት ይገባል።
ወያኔ ለሃገር እና ለህዝብ የማይጠቅም የሚከፋፍል እና የተወሰኑ ወገኖችን ብቻ ለመጥቀም የታቀደ የአሥተዳደር ሥርዐት የመሰረተ ይህንንም ለማስፈጸም ከግለሰብ እስከ ብሄረሰብ ያለርህራሄ የሚጨፈጭፍ ዘር እስከማጥፋት ወንጀል የፈጸመና የሚፈጽም የጥፋት ሃይል ነው። ይህ የጥፋት ሃይል 25 አመት የሃገሪቷን ኢኮኖሚ ወታደራዊ የመረጃ እና የመገናኛ አውታሮችን ሁሉ ተቆጣጥሮ ጡንቻውን ያደለበ እንዲሁም ህዝብ በህብረት ተነስቶ እንዳይመክተው በጎጥ በመከፋፈል በጥቅም በመደለል ብዙ የመለያየት ሥራ ሲሰራ የኖረ በመሆኑ በስሜትና በተናጠል እናስወግደዋለን የሚባለውን ቀልድ ትተን ወደ ሚያዋጣ በትክክል ለውጥ ሊያመጣና ሊያስወግደው ወደሚችለው ስትራተጂ መሄድ ይገባል።
ይህን ለማድረግ ደግሞ ከላይ የተጠቀሱትን ህብረት ቅንጅት እና ግንባር ፈጥሮ እስከ ጉድለታቸው በመቀበል የሃይል ትግል ለማድረግ የግድ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ማሟላት ይገባል።
ወያኔ የትግራይን ገበሬ በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን አሰልጥኖ ጊዜ ወስዶ ከብዙ ሃገራት እና በውጪ ሃገር ከሚኖሩ ደጋፊዎቹ ርዳታ አግኝቶ እንዲሁም የራሱ የገቢ ምንጮች ቤቶች እያከራየ ታክሲዎች እያሰራ ወዘተ…በከፍተኛ የገንዘብና የሰው ሃይል ተደግፎ ነው በ17 አመት ትግል እዚህ የደረሰው።
የትጥቅ ትግል የመደራጃ ቦታ ብዙ መስዋእትነት ብዙ ገንዘብ እና ጊዜ ወዘተ… ይጠይቃል። ይህን አምኖ በመቀበል ነው የሚገባበት።
ይህን እውነታ በመሸፋፈን ህዝቡን ተስፋ ለማስቆረጥና ድጋፍ ለማሳጣት እንደው ብድግ ብሎ ተነስቶ አ. አ. ይደረስ ይመስል አ.ግ7ትን የታል ታዲያ? ለዚሁ ነው? ገበሬው እንጂ አ.ግ.7 የለም እኮ ወዘተ በማለት ትግሉ ቀላልና አጭር እንደሆነ በማስመሰል ሲያስወራ ይሰማል።
አንዳንድ ሰዎችም እንዲሁ አ.ግ7 ነገሮችን ሁሉ በፍጥነት ቀያይሮ የሚፈልጉትን የወያኔን ውድቀት ዛሬ ወይንም ነገ እንዲያሳያቸው የሚፈልጉ የዋሃን ትንሿን ድርሻቸውን እንኳን ሳይወጡ ለእነርሱ ነጻነት ሌላው በገንዘቡ በጉልበቱ በጊዜው በእውቀቱ መስዋእት እንዲሆንላቸው የሚፈልጉ አሉ።
አ.ግ7 ግን ሲጀምር ገና ያለው ህዝቡ ለነፃነቱ እራሱ እንዲታገል ወያኔን በቃኝ እንዲል ሁሉም ባለበትም ሆኖ ይሁን ወደ ትጥቅ ትግል ግንባር በመሄድ በሚችለው እንዲሳተፍና የሚፈልገውን ለውጥ እንዲያመጣ በዋነኝነት ህዝብን ማስተባበርና ማነሳሳት በሂደትም የራሱን የሃይልና የዲፕሎማሲ አቅም እያጠናከረ ወያኔን ማስወገድ አልያም ማስገደድ የሚል ነበር ነው ወደፊትም ይህ ነው አላማው።
ከዚህ አልፎ በአንድና በሁለት አመት ያለብዙሃኑ ህዝብ እገዛ ያለ በቂ የሰው ሃይልና የገንዘብም ሆነ የጦር መሳሪያ ወያኔን ጥዬ ነጻነትን ለኢትዮጵያ ህዝብ አመጣለሁ አላለም። ነጻነቱን ከፈለገ ከማንም በላይና በፊት የራሱ የህዝቡ በየአካባቢው መነሳት ነው ወሳኙ።
በጎንደር በወልቃይት በሁመራም አ.ግ7 ያደረገው ይህንን ነው። ከዚህ በፊት በደቡብ አካባቢም እንዲሁ ነው ያደረገው። ወደፊትም ህዝቡ እምቢ እንዲል ወያኔን በሰልፍና በቃላት ብቻ ሳይሆን ብረት በማንሳትም እንዲታገል ያደረጋል።
ወያኔም ይህ አካሄድ ስለሆነ ለህልውናው የሚያሰጋው ከምንም በላይ የአንድነት ሃይሎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪም ይታገላል።
ከዚህ የተለየው የተበታተነ እና ሁሉም በየራሱ በየዘውጉ የሚያደርገው ነገር እምብዛም አያስጨንቀው። የትም አይደርስምና። የመኖር ህልውናውም በዛ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ይህን በስፋት ያመጣውም እርሱ ስለሆነ 25 አመት ያቆየው መንገድ ስለሆነ ይህን የመከፋፈል አካሄድ በደንብ ይፈልገዋል። ሰሞኑን በየማኅበራዊ ሚዲያው አ.ግ.7ትን እና ኢሳትን የማጥላላት ዘመቻው ምንጩም ይኸው ስለሆነ እኛም ነቅተናል ጉድጓድ ምሰናል ማለት ይገባናል።
ስለሆነም አንድ አይነት አላማ ያላቸውን አ.ግ.7ትን እና የአማራ ታጋዮችን እነርሱ ናቸው እኛ ነን እነርሱ አይደሉም እኛ አይደለንም እያሉ ትግሉን ከወያኔ ጋር ሳይሆን እርስ በእርስ ለማድረግ በወያኔ የተገዙ እና በጉራ የተሞሉ ወይንም ነገሩ ያልገባቸው ሰዎች ራሳቸውን ማረምና ትኩረታቸውን ሁሉ በወያኔ ላይ ሊያደርጉ ይገባል።
በአንድነት በቅንጅት እና በህብረት ካልሆነ ወያኔን ማስወገድ ያስቸግራል። ግንባር መፍጠሩና አብሮ መስራትም ለወደፊቱም ከወያኔ በኋላ ለሚመጣው የሽግግር ሥርዐት ሂደት ይበጃል።
No comments:
Post a Comment