Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, November 9, 2016

አትሌት አልማዝ አያና የዓለማችን ምርጧ ሴት አትሌት ለመባል የመጨረሻዎቹ 3 እጩዎች ውስጥ ገባች

በአስደናቂ ውጤት በሪዮ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ከኢትዮጵያ ያመጣችው አትሌት አልማዝ አያና የዓለማችን ምርጧ ሴት አትሌት ለመባል በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከተመረጡ የመጨረሻዎቹ 3 አትሌቶች መካከል አንዷ ሆነች::
almaz


ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ካገኘችው መረጃ ለማመልከት እንደቻለችው አልማዝ ከጃማካዊቷ ኤላኒ ቶምሰን እና ከፖላንዳዊቷ አኒታ ዎድዋርሲክ ጋር የመጨረሻ ፉክክር ይጠብቃታል::


በሪዮ ኦሎምፒክ በተለይ 10 ሺህ ሜትር ሴቶች ክብረ ወሰን ጭምር የሰበረችው አልማዝ በ5 ሺህ ሜትርም የነሃስ ሜዳልያ አምጥታ ነበር::

ጃማካዊቷ ኤላኒ ቶምሰን በሪዩ ኦሎምፒክ በ100 ሜትር እና በ200 ሜትር ሴቶች 2 የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ፣ በ400 ሜትር ዱላ ቅብብል ደግሞ የብር ሜዳልያ ተሸላሚ የነበረች ነች:: በተጨማሪም ፖላንዳዊቷ አኒታ ዎድዋርሲክ በመዶሻ ውርወራ የሪዮ ኦሎምፒክን ክብረ ወሰን በመስበር 2ኛ የኦሎምፒክ ወርቅ ተሸላሚ ነች፡፡


አለትሌት አልማዝ አያና መልካም ዕድል እንመኛለን

No comments:

Post a Comment

wanted officials