Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, November 10, 2016

ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፅህፈት ቤቶቻቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ለመቀየር እያሰላሰሉ ነው።

ሕወሓት ለስልጣኑ ሲል ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ የማውደም ሥራ እየሰራ ነው።በዐማራ ክልል ከገጠር እስከ ከተማ ፍፁም ፋሽሽታዊ በሆነ መልኩ በሕዝቡ ላይ ግድያ እና እስር እየተፈፀመ ነው።ይህ በእንዲህ እያለ የኢንተርኔት አገልግሎት በመቆራረጡ እና በአብዛኛው ጊዜ ዝግ በመሆኑ የአፍሪካ ኅብረት፣ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢሮዎቻቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ለመቀየር እያሰላሰሉ ነው።
በኢንተርኔት ምክንያት ሥራ መስራት እንዳልቻሉ የአሜሪካ ኤምባሲ እና የአፍሪካ ኅብረት በተለይ ሁለት ጊዜ መግለጫ አውጥተዋል።የአፍሪካ ኅብረትን ከአዲስ አበባ እንዲቀየር ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ልዩ ልዩ ማባበያ በማቅረብ ድርጅቱን ስያማምሉ የነበሩ መሆኑ ይታወቃል።ሕወሓት ለስልጣኑ ሲል ታሪካዊ የጥፋት ሥራ በኢትዮጵያ ላይ እየሰራ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ።
ከእዚህ በፊት በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢሮዎቻቸውን ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ ለማዞር ያልቻሉበት ምክንያት የኢትዮጵያ ቴሌኮምንኬሽን የኢንተርኔት አገልግሎት ደካማ መሆኑን በግልፅ ሲናገሩ እንደነበር ይታወቃል።ይህ እንግዲህ ቴሌ አገልግሎቱን በሚሰጥበት ወቅት መሆኑ ነው።በአሁኑ የኢንተርኔት መቆም ግን ድርጅቶቹ ዋና መስርያቤቶቻቸውን ለማሳመን በቂ ምክንያት እንደሚሆንላቸው ይታመናል።ሕወሓት ኢትዮጵያን ወደ ጨለማው ዘመን እየመራት ነው።
Bilderesultat for african union office

No comments:

Post a Comment

wanted officials