Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 19, 2016

በሚችጋን ኢትዮጵያዊው በትራምፕ ደጋፊ ድብደባ ደረሰበት




===================
በአሜሪካ ሚችጋን የሚኖር ኢትዮጵያዊ የታክሲ አሽከርካሪ በዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ ድብደባ የደረሰበት መሆኑን ኤም ላይቭ ዶት ኮም ለንባብ አብቅቷል፡፡
የማጅ አደም የተባለው ኢትዮጵያዊው ስደተኛ በኋላ ላይ ስሙ ጃኮብ ዴቪድ እንደሚሰኝ በተደረሰበት ዘረኛ ስለተፈጸመበት ሲያወራ ወደማሽከረክራት ታክሲ አምስት ሴቶች መጡ ግለሰቡ ከእነርሱ ጋር የመጣ መስሎኝም ነበር ብሏል፡፡
የታክሲው ሹፌር ግለሰቡ ጠጥቶ እንደነበር በመግለጽ በታክሲው እንዲወስደው ለጠየቀው ቦታ 10 ዶላር እንደማይበቃ ለማስረዳት ሲሞክር ግለሰቡ በብስጭት ተሞልቶ በቡክስ እንደነረተው ተናግሯል፡፡
‹‹እውነቱን ለመናገር በሰነዘረብኝ የመጀመሪያ ቡጢ ተገርሚያለሁ ፣ከተሳፋሪዎቼ እንዲህ አይነት ነገር አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ነገር ግን ግለሰቡ የትራምፕ ስምን ሲጠራ ነገሩ የተለየ መሆኑን ተረድቻለሁ››ብሏል፡፡
አደም ከተሰነዘረበት ቡጢ በኋላ ከመኪናው ዘሎ በመውጣት እግሬ አውጪኝ በማለቱ ራሱን አትርፏል፡፡ፖሊሶች በአካባቢው በመድረስም ተጠርጣሪውን የነጭ ዘረኛ በቁጥጥር ስር አውለውታል፡፡
አደም ‹‹በጥላቻ ስብከት አእምሯቸው የተበከሉ ጥቂት ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ ነገር ግን በዚህ ሰው ምክንያት ሁሉንም ሰው አልፈርጅም ››ማለቱ ተዘግቧል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials