Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, November 9, 2016

ህዝቡን ግን በእውነት አዋጁ ገድቦታልን?


ወያኔ ይህን አፋኝ አዋጅ ባወጀ ማግስት በተልቱላ ሚዲያው አዋጁ መታወጁ የህብረተሰቡን ሰላም መልሷል ብሎ ተናግሯል። ግን የህዝቡ ዝምታ አዋጁ ስለገደበው ይሆን? አይደለም።
1. እጅን አጣምሮ መውጣት በአደባባይ ግደለኝ መጥቸልሃለሁ እንደማለት ስለሆነ ይህን የትግል ስልት በሌሎች ስልቶች ለመተካት ሲባል ነው።
2. የትጥቅ መሳሪያዎችን በእጅ ለማስገባት ዝንታው የተሻለ ስለነበር ነው።
3. በጎንደር ሁመራ ሰሊጥ ተሰብስቦ እስኪያልቅ ድረስ መታገስ ስለሚገባ ነው። ይህ ሰሊጥ ለትግላችን አጋዥ የገንዘብ ምን ጭ ስለሆነ ነው።
4. ሁላችን መብታችንን ተጠቅመን የምናደርጋቸው ተቃውሞዎች ለምሳሌ በሰላም ባስ አለመሄድ፣ ዳሽን ቢራን አለመጠጣት፣ ከወያኔ ባንኮች ገንዘብን አለማስቀመጥ ወዘተ ዝምታችንን ጨምረውታል። ሙያ በልብ ነው ይሉ አይደል። በዚህ የዝምታ ተቃውሞ ወያኔ ካዘናው ተሟጦ እርዳታ በመጠየቅ ላይ ሲሆን ዳሽን ቢራ ፋብሪካም ሊዘጋ ጥቂት ነገር ነው የሚቀረው። ስለዚህ ነው ህዝቡ ዝም ያለ ያመሰለው እንጅ አዋጁ አፍኖት አይደለም። አሁን ማንነታችን ሳይታወቅ በወያኔ ተላላኪዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ ትግል ላይ ነን። ይህ ትግል ደግሞ እጅ አጣምረን ከአጋዚ ጋር ግብግብ የምንገጥምበት አይደለም።
13920606_1685064478484194_6501922508429330789_n

No comments:

Post a Comment

wanted officials