ኢሳት ዜና :-
ኢሳት ያነጋገራቸው በክልሉ ተወልደው ያደረጉ የአማራ ተወላጆች እንደገለጹት ቀደም ብሎ በነበረው መንግስት በሰፈራ ፕሮግራም አማካኝነት አሁን ቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባለ ወደ ሚጠራው አካባቢ ሄደው እንዲሰፍሩ ከተደረገና ልጆችን ወልደው፣ ቤት ንብረት አፍርተው ለአመታት ከኖሩ በሁዋላ፣ የአገዛዙ ሹሞች በተለያዩ ሰበብ አስባቦች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ጫና እየፈጠሩባቸው ነው።
ነዋሪዎቹ ልማት ላይ ያልዋሉ ቦታዎችን ገንዘባቸውን፣ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን አፍስሰው ካለሙ በሁዋላ፣ የክልሉ መንግስት ለልማት ይፈለጋል በማለት ያለምንም ካሳ እየነጠቀ በመውሰዱ አብዛኛው በአሶሳ አካባቢ የሚኖሩ የአማራ ተወላጅ አርሶአደሮች የሚያርሱት መሬት አጥተው እየተሰቃዩ ነው። “ መኖር አልቻልንም፣ አቤቱታችንን የሚሰማልን መንግስት አላገኘንም “ በማለት በምሬት የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ አማራጭ በማጣታቸው መብታቸውን ለማስከበር ወደ ጫካ እየገቡ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ የሚገኙ መሬታቸውን የሚነጠቁ አማራ አርሶአደሮች አማራጭ በማጣት ወደ ከተማ እየተሰደዱ መሆኑን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ መሬታቸው እየተወሰደ ለዘመኑ ባለሃብቶች እየተሰጠ ነው በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። በክልሉ ውስጥ የሚታየው የጸጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሲሆን፣ ራሱን በወታደራዊ እዝ ስር አደራጅቶ አገሪቱን በመግዛት ላይ ያለው የህወሃት/ኢህአዴን መንግስት በርካታ ወጣቶችን ይዞ አስሯል

No comments:
Post a Comment