ኢትዮጵያዊው አባት ሁለት ህጻናት ልጆቹን በመግደል ተጠርጥሮ ታሰረ
(አድማስ ሬዲዮ) ነገሩ የሆነው በርሚንግሃም እንግሊዝ ነው። ባለፈው ኦክቶበር 28 ቀን በሚኖሩበት ቤት ተነሳ በተባለ እሳት የ 8 ህጻን የሆነችው ሳሮስ ኢድሪስ እና የ6 ዓመት ዕድሜ ያለው ወንድሟ ሊያኖር ኢድሪስ በ እሳቱ ተቃጥለው ህይወታቸው ሲያልፍ፣ አባት ፣ ራሱን ለመግደልም ሞክሮ መኪናው ውስጥ እሳት ከለቀቀ በኋላ ተርፎ ሆስፒታል ሊወሰድ ችሏል። እናት ጴንኤል ተክለሃይማኖት ግን ተርፋለች :: ቢሆንም፣ ባሁኑ ወቅት የእዕምሮ ችግር ገጥሟት በሰው ድጋፍ እንዳለች ለአድማስ ሬዲዮ የደረሰው ዜና ያስረዳል።
Eight-year-old Saros Endris and his sister Leanor Endris, six, died following the “suspicious” fire at a home in Holland Road, Hamstead. The father, Mohammed Endris, 46, was arrested on Thursday morning. Preliminary investigation shows that the childeren died NOT because of the fire related injury.
Mr Endris was found with life-threatening injuries in a fire-damaged car in Staffordshire several hours later. The children’s mother Penil Teklehaimamot, 36, was uninjured. She is being treated as a witness. ፖሊስ እስካሁን ባለኝ ምርመራ አረጋገጥኩ እንዳለው፣ ህጻናቱ ህይወታቸው ያለፈው ከ እሳቱ በፊት ነው። በመሆኑም በወቅቱ አብሯቸው የነበረው አባት፣ ሆስፒታልም ቢሆን፣ ልጆቹን ገድሎ ከዚያ በ እሳት አደጋ እንደሞቱ ለማስመሰል ሳይሞክር አልቀረም በሚል ጥርጣሬ መታሰሩ ተነግሯል። ከዚያም ተያይዞ ራሱን ለማጥፋት ሳይሞክር አልቀረም በተባለ ሁኔታ ከቤቱ ርቆ መኪናው ውስጥ በ እሳት ተቃጥሎ ግን ከነህይወቱ ፖሊስ ደርሶ ሆስፒታል ወስዶታል።
በበርሚግሃም እንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ አሳዛኝ አደጋ ማዘናቸውን ለአድማስ ሬዲዮ ገልጸዋል። አያይዘውም፣ ምርመራው ተጠናቆ አሁን ህጻናቱ ይቀበሩ ስለተባለ፣ ለቀብር ማስፈጸሚያ እርዳታ እያሰባሰቡ መሆኑን የባንክ ቁጥር አያይዘው ልከውልናል። ዲሴምበር 3 ቀንም የገቢ ማስገኛ ዝግጅት ማዘጋጀታቸውን እንግሊዝ የምትኖሩ ኢትይጵያውያን እወቁልንና ተባበሩን ብለዋል። Ethiopians who live in Birmingham, England asks for your help for the funeral cost of the two children.
BARCLAYS BANK
KASSIM SENDUKIE
SORT CODE: 20-70-70.
ACC. NO. 10075485
KASSIM SENDUKIE
SORT CODE: 20-70-70.
ACC. NO. 10075485
ለበለጠ መረጃ 07932786622 ቃሲም ወይም 07852131171 ተስፋዬ ብለው ሊደውሉ ይችላሉ።
No comments:
Post a Comment