አሁን ያለው የአማራ ህዝብ ትግል የስልጣን ትግል አደለም ትግሉ የጌጥ ወይም እንደዚህ በፊቱ አባቶቻችን ይዋጉት እንደነበረው የደንበር ማስከበር ወይም ከውጭ ወራሪ ጋር የሚደረግ ትግል አደለም ፡፡ ትግላችን የህልውና የማንነት ትግል የመኖር ያለመኖር ትግል ነው፡፡ ትግሉ በሀገር ውስጥ አማራው እንደዜጋ ማንነቱን አስከብሮ ለመኖር የሚደረግ ትግል ነው፡፡ አማራው በዘረኛውና በጎጠኛው የትግሬ ወያኔ ቡድን በሀገሩ ሀብት ንብረት አፍርቶና ተዘዋውሮ እንዳይሰራ አድርጎታል በሚኖርበት በሀገሪቱ አካባቢ እየተገደለ እየተፈናቀለ እየተሰደደ ድፍን 25 ዓመት አስቆጥሯል ፡፡ እሄን በአማራው ህዝብ ላይ የደረሰውን መከራ እና ስቃይ አንድም በኢትዮጵያ አንድነት የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ የስቪክ ማህበራት ትንፍሽ ሲሉ አልሰማንም ነገር ግን ይህን መከራ ስቃይና ግፍ የደረሰብን የአማራ ልጆች ወደ በረሃ በመውረድ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ / አ.ዴ.ሃ.ን/ ሲመሰረት አይዟችሁ ያለ አልነበረም ብዙ ፈተናዎችንም አልፈናል ብዙም ተብለናል እንዴት በአማራ ስም ትደራጃላችሁ ተብለናል በተለይ በአማራ ብሔር ተወላጆች ዘንድ ብዙ ወቀሳ ደርሶብናል ነገር ግን አደረጃጀታችን ስንደራጅ ለስልጣን እንዳልሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያውቅ ይገባል፡፡ በተለይ በአማራ ስም ስንደራጅ እንደዘረኛ እና ጠባብ ያዪን የነበሩት አሁን ባይቀላቀሉንም በሃሳብ እየደገፉን ነው ነገር ግን አሁንም ትልቅ ችግር እንዳለ ይታየኛል ፤ ይህም ችግር ምንድን ነው በረሃ መሬት ላይ ያለን የአማራ ሃይል ከማጠናከር እና ማገዝ ፈንታ በየቀኑ የተለያዩ የአማራ ድርጅቶች እንዳሸን እየፈሉ ነው፡፡ ለዚህ ህዝብ የሚያስፈልገው አንድ የፖለቲካ ድርጅት እና አንድ የስቪክ ማህበር ብቻ ነው ነገር ግን ሁሉም በየጎጡ የስቪክ ማህበር እና የፖለቲካ ድርጅት መመሥረት ላይ ተጠምዷል እሄም ባልከፋ ነበር እርስ በራስ መጠላለፍ እና መተቻቸት ስራ ብለው ይዘውታል እሄ ደግሞ የአማራ ን ህዝብ ችግር ያራዝመዋል ፤ በአንፃሩ ደግሞ ለዘረኛው ትግሬ ወያኔ ቡድን ደግሞ ይጠቅመዋል ይህን ችግር እስካልፈታን ድረስ ትግላችንን ያቀጭጨዋል እንጅ አይጠቅምም፡፡
አማራው ከዚህ በፊት ጎንደር ጎጃም ሸዋና ወሎ በኢኮኖሚና ፖለቲካ ጫና የነበረበት ቢሆንም መፈናቀሉ ሞቱና ስደቱ ይበዛ የነበረው ከነዚህ ከ/ ሀገሮች ዉጭ በሆነው የሀገሪቱ አካባቢ ነበር ፤ አሁን ግን አማራው በጅምላ እየተገደለ አየታሰረ እና እየተፈናቀለ ያለው በነዚህ አካባቢዎች ነው በተለይ በጎንደር እና በጎጃም እየሆነ ያለው ያሳዝናል ፤ ነገር ግን እናውቃለን የምንል ሰዎች አሁንም አልተረዳንለትም አማራው አማራ በመሆኑ ብቻ እየተገደለ ነው እሄን ተገንዝበን ለግል ስምና እውቅና ለማግኘት ከምንሯሯጥ አንድ ሁነን ብንታገል ጥሩ ነው አንላለን፡፡
No comments:
Post a Comment