- 120
(ዘ-ሐበሻ) በምዕራብ ወለጋ ነጆ ከተማ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ ተማሪዎች እየታፈሱ መሆኑ ተሰማ:: በኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በትምህርት ቤቶች እንደ አዲስ መጀመራቸውን ተከትሎ የመለስተኛና የ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በነጆ ከነዩኒፎርማቸው በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ሲታፈሱ ውለዋል::
እንዳንድ ተማሪዎች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በተለይም ሴት ተማሪዎች የወሲብ ትንኮሳ ከሕወሓት ወታደሮች እንደተፈጸመባቸው አስረድተዋል::
በም ዕራብ ወለጋ ነጆ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች::
No comments:
Post a Comment