Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, November 23, 2016

‹‹ያለመንግሥትና ያለፖለቲካ ድርጅት ጣልቃገብነት ሕዝቡ የራሱን ሸንጎ በየደረጃው መሥርቶ ችግሩን ተወያይቶ ሊፈታ ይገባል›› አያልነህ ሙላቱ

‹‹ያለመንግሥትና ያለፖለቲካ ድርጅት ጣልቃገብነት ሕዝቡ የራሱን ሸንጎ በየደረጃው መሥርቶ ችግሩን ተወያይቶ ሊፈታ ይገባል›› አያልነህ ሙላቱ

  • 227
    Share
270-kumneger-cover-copy-640x915
ግዕዝ ካማርኛ አስተባብሮ ሲያውቅ?
ከውጭ ሐገር ቋንቋ ያን ጊዜ ይንጠቅ፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
በ1941 ዓ.ም በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሀገር አገው ምድር የተወለዱት ደራሲ፤ገጣሚና ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ በስነ ፅሑፍና በጋዜጠኝነት የትምህርት መስክ ከሞስኮ ዩኒቨርሲቲ የማስትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡ ፡ ሃያ ያህል የሙሉ ጊዜ ቴአትሮችን የፃፉና ለመድረክ ያበቁት አቶ አያልነህ ስድስት የሥነ ግጥም መድብል መፅሐፍና ከሩሲያ ቋንቋ የተተረጎሙ በርካታ የስነ ግጥም ስራዎች አላቸው፡፡ ከፃፏቸው ቴአትሮች መሀከል በሩሲያ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተርጎመው ለዕይታ ያበቁት አቶ አያልነህ ሰሞኑን በሀገራችን ከተከሰተው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ‹‹ዳር ቆሞ መመልከት ዋጋ የለውም ›› በሚል ስሜት የራሳቸውን ዕይታና የመፍትሔ አማራጭ ሀሳብ ያሉትን አቅርበዋል፡፡
የሀገራችን የዘመናት ችግርና ያለመደማመጥ መጥፎ ባህል ላይ የሀገሪቱ ምሑራን ረብ የለሽ አስተዋፅኦ መታከሉን የሚተቹት አቶ አያልነህ ለፖለቲካዊ ፤ ለማህበራዊም ሆነ ለአኮኖሚያዊ ችግሮቻችን መፍትሔው በራሳችን ባህልና ትውፊት ውስጥ መኖሩን በመናቅ ሥርዓተ ትምህርታችንን ከፈረንጆች ቀድተን ማስተማር መጀመራችንና አይናችንን ወደ ፈረንጆች ማማተራችን ከአዙሪቱ እንዳንወጣ አድርጎናል ባይ ናቸው፡፡ አቶ አያልነህ ከቁም ነገር መፅሔት አዘጋጅ ፍስሃ ጌትነት ጋር በዚሁ ችግር ዙሪያ ያደረጉት ቃለ ምልልስ በገጽ 8 ላይ የተስተናገደ ሲሆን ‹‹ ግጭት አብራጅ ዘመናዊ ምሁራን አሉን?›› በሚል ርዕስ ያቀረቡትን ፅሑፍ ለዓምዱ በሚመች መልኩ ጨምቀን አቅርበነዋል፡፡
‹‹እኔ በፖለቲካ ምሕዋር ውስጥ ብኖርም ዐይን ያወጣሁ ፖለቲከኛ ግን አይደለሁም፡፡›› በማለት ይጀምራሉ አቶ አያልነህ፤ ‹‹ መፃፍ ብችልም ጥሩ ተመራማሪ ምሁር ነኝ አልልም፡፡መናገር ብችልም ለሚገባው ተገቢ ቃላት መርጨ መናገር አልችልም፡፡ኤዲያ!እኔ ማን ነኝ? እራሴን የሥነ ጽሑፍ ሰው አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ ይምረርም-ይጣፍጥ.. ይወደድም-ይጠላ..ይከበርም-ይናቅ.. ዘመን ተሻጋሪም ይባል ወቅታዊ..ዕድሜየን በሙሉ ያገባደድሁት በዚህ ሙያ ላይ ተሰማርቼ ነው፡፡ ››
አቶ አያልነህ የሀገራችንን ምሑራን ሚና በተቹበት ፅሑፋቸው ሥነ መሰረቱ የሀገራችን የትምህርት አሰጣጥ ከውጪ ሀገር የተገለበጠ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ትምህርት‹‹ልዩ-ልዩ የዕውቀት መፃሕፍትን ከአስተማሪው መማር.. መቅሰም..መቅዳት.. መገልበጥ ›› ነው ይላል የከሣቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት(2002 እትም ፣ገጽ 559)እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባ ነጥብ አለ፡፡ይኸውምልዩ-ልዩ የዕውቀት መፃሕፍትን ከአስተማሪው መማር.. መቅሰም..መቅዳት.. መገልበጥ በማለት ለትምህርት የተሰጠውን ትርጉም ነው፡፡ የዚህን ጽሑፍ ዐላማ በሚገባ የሚያንፀባርቀውም ይህ ነጥብ ነው፡፡ የአገሪቱ ዘመናዊ ትምህርት መነሻ ወደሆነው ሥርዐተ-ትምህርትየሚያመራኝም ይህ ለትምህርት የተሰጠው ስያሜ ነው፡ ፡ የእኛ ዘመናዊሥርዐተ-ትምህርት የተቀዳው.. የተቀሰመው.. የተገለበጠው.. ከውጭ መሆኑን ለማንም ዘመናዊ ምሁር ግልጽ ነው፡፡
‹‹የዘመናዊው ትምህርታችን ከመነሻው ጀምሮ የእኛን ነባር ባህል መሠረት ያላደረገ፣ የውጭ አገር ሥርዐተ ትምህርት ነው፡፡ ሁለተኛው የዚህ ሥርዐተ ትምህርት አስፈፃሚዎች የውጭ አገር መምህራን መሆናቸው ነው፡፡›› የሚሉት አቶ አያልነህ ‹‹በዘመናችን ደግሞ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አስተማሪዎቻችን የሥርዐተ ትምህርቱ ባለቤቶች ወይም ፈጣሪዎች የሆኑት ፈረንጆች ነበሩ ፡፡ የከተማችን ዕውቅተማሪ ቤቶች ባለሐብቶች የውጭ ኢምባሲዎች ወይም ዜጎች ናቸው፡፡ እኛ በዘመናዊ ትምህርት ያለፍነው ምሁራን‹‹ልዩ- ልዩ የዕውቀት መፃሕፍትን›› የቀዳነው.. የተማርነው.. የገለበጥነው ከየትኛው አስተማሪ ይሆን? አስተማሪው የሚያስተምርባቸው የዕውቀት መፃሕፍቱስ በማንና በምን ቋንቋ የተዘጋጁ ናቸው? ሥርዐተ ትምህርቱየነጭ ከሆነ ዘንዳ..አስተማሪውይጥቆር-ይቅላበዚህ በነጭ ሥርዐተ ትምህርት ተሞርዶ የተሳለ ነው› ይላሉ፡፡
ይህ በዚህ ሥርዐተ ትምሕርት የተቀረጸ ምሁር ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ነጭ አገር ድረስ ዘልቆየሥርዐተ ትምህርቱ ባለቤት የሆነውን ነጩን ዜጋእራሱን ማስተማር የሚችል ነው፡፡ ፈረንጅ የፈጠረውሥርዐተ ትምህርትደግሞ የትም-ይሁን-የት.. ትምህርቱን በተቀበሉት አገሮች ሁሉ ይሠራል፡፡ እኒህ ነጭ በቀረፀው ሥርዐተ ትምህርት ABCD ብቻ ብለው የተማሩት.. ለሥርዐተ ትምህርቱ ተብለው በተደረሱ የዕውቀት መፃሕፍት የተቀረጹ.. በሥርዐተ ትምህርቱ በተካኑ መምህራን ዕውቀት የቀሰሙ ምሁራንየዛሬዋንእናትአገራቸውንበሚገባ ያውቋታል ማለት ይቻላል ወይ? ልብ በሉ.. ይወዷታል ወይ? ብዬ አልጠየቅሁም፡፡
የእናት አገር ፍቅር ከትምህርት ብቻ አይመነጭም፡፡ ጥያቄዬ ዘመናዊው ምሁር በየሕብረተቡ ጓዳ ውስጥ ያለውን እምቅ ጥበብ.. ብርቅዬ ዕውቀት.. ዕንቁ ባህል..ትውፊት..ችግር.. ደስታ ወዘተ የማወቅ ክህሎቱን ከዘመናዊው ትምህርት ጋር ተመግቦታል ወይ? የገዳን.. የአፋርን..የሶማሌን..የአማራን.. የትግሬን.. የጋምቤላን ወዘተየዕርቅ.. የፍትህሥርዐት ያውቀዋል ወይ? ሬቻ የምስጋናና የዕርቅ ማእድ ሆኖ ከስድስት መቶ ዐመታትጀምሮ የሚከበር ሕዝባዊ ሥርዐት ነው፡፡ ሰዎች ወደሬቻ ከመምጣታቸው በፊት ከተጣሉት ሰው ጋር ዕርቀ-ሠላም ማውረድ አለባቸው፡፡ ቂም ቋጥሮ ሬቻ መምጣት ኃጢያት ነው፡፡ ይህን ካወቅን ዘንዳ ለምን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በእያመቱ እንደመስቀልና እንደ አረፋ.. ወይም እንደ ሜይ ዴይና እንደ ዘመን መለወጫ ወይም እንደ ግንቦት ሃያ እንዲያከብረው በሕግ አልደነገግንለትም፡፡ እንወያይበት፡፡
ት ም ህ ር ት ማህበራዊ ዕውነታን በትክክል የሚያንጸባርቅ፣ ለሕዝባዊ ሥርዐት ግንባታ ህሊናዊ ሁኔታዎችን የሚያመቻች፣ ሕብረተሰቡን ከጎታችና ኋላቀር አመለካከትም ሆነ እምነት የሚያላቅቅና ከተፈጥሮ አደጋዎች ጋር በቁርጠኝነት እንዲታገል የሚያነሳሳ፣ ድህነትን የሚያስወግድ.. ርሀብን የሚያጠፋ.. ፍትህን የሚያሰፍን.. የሕዝቦች አብሮነትን የሚፈጥርነው፡፡ በነባሩ ባህል ላይ መሰረቱን ያደረገ ትምህርት በጋራ- ጥረት ለጋራ-ብልጽግና መሥራትን ያበረታታል፡፡ ስነምግባርንም ያሰርጻል፡፡ የአገር ፍቅርንና አርበኝነትን ይገነባል፡፡ ዓለም አቀፋዊነትን ያጠናክራል፡፡ የውጭ የባህል ወረራንና ለዘመናት በሕዝቡ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ሰርጾ በመግባት ጠንቅ የሆነውን ጎታች ልማድን ይዋጋል፡፡ በምትኩም የሕዝቡን እሴት..ነባር ዕውቀትያዳብራል፡፡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አዲስ ስብዕና ያለው ባህላዊ ሰው ይፈጥራል፡፡
ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ዕድገት መፋጠን ጥርጊያ ጎዳናን መቀየስ እንዲቻል፣ ነባር ክህሎቶች ሰርጸው ገብተው እንዲያብቡና እንዲዳብሩ፣ ዘመናዊ ትምህርት በህብረተሰባችን ውስጥ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና ጠጋ ብሎ መገምገምና ቀጥተኛ ፈር የሚያስይዝ ሥርዐተ ትምህርት መዘርጋት አስፈላጊ ነው፡፡ ለማበልጸግ የምንፈልገው ትምህርት መሠረቱ ምን መሆን አለበት? የሚለው ጥያቄ አፋጣኝ መልስ የሚያሻው ጉዳይ ነው፡፡
የሰውን ልጅ ሙሉ-በሙሉ ነፃ የሚያወጣው ትምህርት ብቻ ነው፡፡ ምሁራን በተማረ ሰውና ባልተማረ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት በጨለማና በብርሃን.. በሞትና በሕይወት መካል ካለ ልዩነት ጋር ያነፃጽሩታል፡፡ በትምህርት የምንገነባው የሰውን ጭንቅላቱን ወይም አካሉን ነጥለን ሳይሆን እራሱን ሰውን ነው፡፡ የእናት እቅፍ.. ቤተሰብ.. ሕብረተሰብ.. ትምርት ቤት ሁሉም የዕውቀት መቅሰሚያ መድረኮች ናቸው፡፡ የተማረን ሕዝብ በአግባቡ መምራት እንጅ ወደፈለጉት መንዳት አይቻልም፡፡ማስተዳደር እንጅ መግዛትም አስቸጋሪ ነው፡፡ ባልተማረ ሕብረተሰብ ውስጥ የዲሞክራሲን ጽንሰ ሀሳብ ማስረጽም በእጅጉ አስቸጋሪ ነው፡፡ትምህርት የሰውን ልጅ መጀመሪያ
ማ ን ኛ ው ም ዐይነት ጥናትም ሆነ ምርምር ደግሞ ተቀባይነት አ ይ ኖ ረ ው ም ፡ ፡ ኢትዩጵያዊው ዘመናዊ ምሁር ሰ ለ ኢ ት ዮ ጵ ያ ቋንቋዎች ሲያጠና ነጭ የፃፈውን መጽሐፍ በዋቢነት ወይም በአስረጅነት መ ጥ ቀ ስ በግድያስፈልገዋል፡ ፡ ስለአገሩም ብሔረሰቦችሲጽፍ የፈረንጅ ቡራኪ ያሻዋል፡፡ በታሪኩ.. በ ፖ ለ ቲ ካ ው . . በ ኢ ኮ ኖ ሚ ው . . በ ሕ ክ ም ና ው ም . . በ ም ሕን ድ ስ ና ው . . በባህሉ.. በኪጥበብ ዘርፎች ሲጽፍ ፈረንጅ ካልጠቀሰ ምርምሩም ሆነ ጥናቱ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ ወደአገሩ ዘወር ብሎ ነባር ምሁራን ላስታውሳቸው ቢል እንኳ፣ አንድም በሥርዐተ ትምህርቱ ተካተው በአግባቡ ስላልተማራቸው አያውቃቸውም፡፡ ሁለትም ዐይኑን-በጨው አጥቦ የአገሪቱን ሊቃውንት ደፍሮ ቢጠጋቸው፣በቋንቋ ስለማይግባቡ ዋቢ አድርጎ ሊልጥቀሳቸው አይችልም፡፡ ይህን ሁሉ አልፎ ሊጠቅሳቸው ቢችልም ነጭ አስተማሪው ጥቅሱን ሳይንሳዊ አይደለም ብሎ አይቀበለውም፡፡ የጥንታውያን አበሾችሊቀ- ሊቃውንት ድርሳናት በዐለም ላይ ተቀባይነት እንዲያገኙየፈረንጅ ቡራኪያስፈልጋቸዋል፡፡ ፈረንጅካልባረካቸውበራሳችን ዘመናዊነጭ- አምላኪ ምሁራን ጭምር አፈታሪክ ወይም አሉቧልታ ተብለው ይፈረጃሉ፡፡ በመሠረቱ ሳይንቲስቱም ፈረንጅ.. ስለአበሻ ሲጽፍ ምንጩን በአግባቡ ሳያሰፍርእያለፈውእንጅ.. ማጣቀሻውንም ሆነ ምርምሩን የሚያገኘው ከእነዚህ አበው የአበሻ ሊቀ-ሊቃውንትአንደበት ወይም ድርሳን ነው፡ ፡ አበሾች ሲጥፉት አፈታሪክ የተባለው ድርሳን.. የፈረንጅ ቡራኪ ሲጨመርበት ሳይንሳዊ ይሆናል፡ ፡
እንደ አፋሩ ገበሬ ፍየል ማለት ነው፡ ፡ ያሳደጋትን ፍየል ክርስቲያኖች ገዝተው አርደው ሲበሉ አፋሩን እንብላ ሳይሉት ይቀራሉ፡ ፡ የሰጡትም ምክንያት‹‹አንተ ሙስሊም ነህ ››የሚል ነው፡፡ አፋሩም በምክንያታቸው ተገርሞ እንዲህ አላቸው፡፡ ‹‹ፍየሏ ያደገችው ከእኔ ጋር ነው፡፡ እናንተ ስላረዳችኋት ብቻ እንዴት ክርስቲያን ትሆናለች?ካልነፈጋችሁኝ

No comments:

Post a Comment

wanted officials