Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, November 16, 2016

የሐዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብ ግብ ጠባቂና የሁለት ልጆቹ ሕይወት በእሳት አደጋ አለፈ

የሐዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብ ግብ ጠባቂና የሁለት ልጆቹ ሕይወት በእሳት አደጋ አለፈ

  • 305
    Share
kibreab-dawit
(ዘ-ሐበሻ) ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ23 ዓመት በታች ያለው; ተሰልፎ የተጫወተውና በአሁኑ ወቅት ለሐዋሳ ከነማ በግብ ጠባቂነት እየተጫወተ የሚገኘው ክብረአብ ዳዊት በመኖሪያ ቤቱ በተነሳ የ እሳት አደጋ የ እርሱና የ2 ልጆቹ ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉ ተሰማ::
ግብ ጠባቂው ክብረአብ ከ3 አመት ሴት እና የወራት እድሜ ካለው ወንድ ልጁ ጋር በተኛበት በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ሕይወቱ እንዳለፈ የተነገረ ሲሆን የ እርሱ እና ልጆቹ አስከሬን በአሁኑ ሰአት ለምርመራ በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን በአካባቢው የተቃጠለው የክብረአብ መኖርያ ቤት ብቻ እንደሆነና ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡
ክብረአብ ዳዊት በሀዋሳ ከተማ ከ2007 ጀምሮ በተጠባባቂ ግብ ጠባቂነት እየተጫወተ የነበረ ሲሆን በ2007 በማርያኖ ባሬቶ በሚመራው የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተካትቶ ሱዳንን በገጠመው ቡድን ቋሚ አካል ነበር::
የክብረአብና የልጆቹ ሕይወት ቢያልፍም ባለቤቱ መተርፏም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials