Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 15, 2016

ኢትዮጵያውያን በስዊዲን ፓርላማ ፊት ለፊት የረሃብ አድማ አደረጉ ።

#HUNGER_STRIKE_FOR_JUSTICE
አምባገነኑ የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን የጅምላ ጭፍጨፋ፣ እስራት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማውገዝ በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ለሁለት ቀናት የሚቆይ የርሃብ አድማ እያደረጉ ነው።
ቁጥራቸው ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በስዊድን ፓርላማ ፊት ለፊት ቀዝቃዛው በረማው የአየርንብረት ሳይበግራቸው ለወገኖቻቸው አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ከተለያዩ የሲቪክ ማኅበረሰቦች የተውጣጡት እነዚህ የርሃብ አድማ አድራጊዎች የስዊድን መንግስት አምባገነኑን የህወሃት ኢህአዲግ መንግስት መርዳቱን እንዲያቆም እና የውጭ ፖሊሲውን ዳግም እንዲይፈትሽ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የስዊድን ፓርላማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ተወካይ የፓርላማ አባላት ወኪሎች በበኩላቸው በስፍራው በመገኘት የርሃብ አድማ አድራጊዎቹን ኢትዮጵያዊያን ጥያቄዎች አድምጠዋል። የስዊድን መንግስት የኢትዮጵያን ውስጥ ያለውን ጉዳይ አንክሮት ሰጥቶት እየተከታተለው መሆኑን  መሆኑን እና የርሃብ አድማውን በሚመለከት ለፓርላማው በማቅረብ እንደሚወያዩበትም ተወካዮቹ ተናግረዋል። የአስተባባሪ ኮሚቴው አባል የሆኑት አቶ ዘለሌ ጸጋስላሴ የርሃብ አድማውን  ዓላማ አስመልክቶ አጠር ያለ መግለጫ ሰጥተዋል።
የርሃብ አድማ አድራጊዎቹ አክለውም በተለይ በባሕር ማዶ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ያሉባቸውን ችግሮች ተወያይተው በመፍታት የጎንዮሽ መሳሳቡን በመተው አገር ውስጥ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ፣ እስርና ሰቆቃ በማውገዝ በአንድ ላይ ቆመን ርብርብ ማድረግ ይገባል ሲሉ ከሕዝባቸው ጋር በመሰለፍ የወያኔን መንግስት እንዲታገሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials