Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 26, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ኮማንደር ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ለትግራዩ መንግስት ጦር እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን ሰዋ

በሰሜን ጎንደር ከአማራ ታጋዮች በተጨማሪ ውጊያ እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 በአርማጭሆ አብደራፊ ባደረገው ውጊያ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ (ገብርዬ) በሕወሓት ወታደሮች በተከበበት ወቅት እጄን አልሰጥም በማለት ራሱን በያዘው ጠመንጃ ማጥፋቱ ተሰማ::
ምንጮች እንዳሉት በሰሜን ጎንደር በተለያዩ ግንባሮች የአማራ ገበሬዎች እና የአርበኞች ግንቦት 7 የሕወሓትን መንግስት እየተዋጉት ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ኮማንደር የነበረው ሻለቃ መሳፍንት በአብራፊ የሄደውን አርበኞች የግንቦት 7 ጦር ሲመራ እንደነበር የዘ-ሐበሻ ምንጮች ያስታወቁ ሲሆን የህወሓት ጦር በሜካናይዝ ደረጃ ቢከበውም ራሱን አጥፍቷል:: ሆኖም ግን እርሱ ይዞት የገባው ጦር ይህ ዜና እስከተሰማበት ጊዜ ድረስ እየተዋጉ ይገኛሉ::
እንደ ምንጮች ገለጻ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ወደ ኤርትራ ሄዶ አርበኞች ግንቦት 7ን የተቀላቀለው የተደላደለ ኑሮውን ከአውሮፓ ሉክዘምበርግ ትቶ ነው::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በሰሜን ጎንደር እያደረኩት ባለሁት ውጊያ የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት ለጊዜው የመሸግኩበትን ቦታ በሄሊኮፕተር ቢደበድብም መክቻቸዋለሁ ሲል መግለጫ ማውጣቱን  አይዘነጋም::
በሌላ ዜና በዚሁ አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዋጉ የሚገኙትን የአማራ ታጋዮችን በርካታ ሕዝብ እየተቀላቀላቸው መሆኑን የደረሰው መረጃ አመልክቷል:: በጎንደር የተለያዩ ግምባሮች ወያኔን እየገጠሙ የሚገኙት የአማራ ታጋዮች በአንድነት ወያኔን ለመውጋት ተስማምተው በጋራ ስር ዓቱን እያርበደበዱት እንደሚገኙም ተሰምቷል::

15109542_10210938344445355_8898449061103277225_n

No comments:

Post a Comment

wanted officials