የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳዛና ዙማ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ አስቸኳይ የፖለቲካ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ ጥሪ አስተላለፉ፡፡በአገሪቱ የመጨረሻ መፍትሄ ለማግኘት መነጋገር በጣም ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ወይሮዋ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባር ላይ ሲያውል የዜጎች መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ተቃውሞውን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ዕቀባ መደረጉን የተቃወሙት ዙማ መንግስት አገልግሎቱን እንዲለቅም ጠይቀዋል፡፡
ሊቀመንበሯ አስቸኳይ አዋጁ በስራ ላይ በሚውልበት ወቅት የተረጋጋና ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግ በመጠየቅ መንግስት የዜጎችን መረጃ የማግኘት፣በግኑኝነት ቴክኖሎጂዎች የኢንተርኔት አገልግሎትና የማህበረሰብ ሚዲያዎችን ይጨምራል የመጠቀም መብትን ግምት ውስጥ በማስገባት አለመጓደላቸውን እንዲያረጋግጥ አሳስበዋል፡፡
No comments:
Post a Comment