ከአርበኞች ግንቦት 7 የጦር አዛዦች አንዱ በሆነው በሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት የለውጥ ደጋፊዎች ሃዘንና
ቁጭታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። በሌላም በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ አሁንም መቀጠሉን የአካባቢው
ምንጮች ገልጸዋል። ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ ኢሳት በሰበር ዜናው ለተያያዘው ምስል ዝግጅት
ክፍሉ የሟቹ ቤተሰቦቹንና ተመልካቾቹን ይቅርታ ጠየቀ።
የቀድሞ የደርግ መንግስት ለመጣል በተደረገው ትግል በብዓዴን/ኢህአዴግ ትግል ተሳታፊ የነበረው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ስልጣን ላይ ያለውን ቡድን በመቃወም ለትምህርት በሄደበት ፈረንሳይ መቅረቱንናበኋላም በስደተኝነት ሉክሰምበርግ መሻገሩን ፣ ከሁለት አመት በፊት በረሃ ላይ ለኢሳት በሰጠው ቃለ-ምልልስ ገልጾ ነበር።
ስርዓቱን መቃወሞ ብቻ ሳይሆን፣ መታገል ያስፈልጋል በሚል የአውሮፓ ኑሮውን በመተው ከቤተቦቹ ተለይቶ ኤርትራ በረሃ የገባው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ፣ መከበቡን ተከትሎ እጅ ላለመስጠት ራሱን ማጥፋቱን የአካባቢ ምንጮችና አርበኞች ግንቦት 7 ገልጸዋል።
ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ከመከበቡና ራሱን ከማጥፋቱ በፊት በቀደሙት ቀናትና በዕለቱ በተካሄዱ ውጊያዎች እርሱ የሚመራው ጦር በደፈጣና በፊት ለፊት ውጊያዎች ጉዳት ማድረሱም ተመልክቷል።
በፈረንሳይ ፖሪስ የሁለት አመታት ወታደራዊ ትምህርቱን አጠናቆ ከስርዓቱ ለመለየት በመወሰን በስደት ሉክሰምበርግ የቆየው የሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት የብዙዎችን ሃዘንና ቁጭት መቀስቀሱ ታውቋል።
በኢሳት የድምፅ መልዕክት ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ የመጡ በርካታ አስተያየቶችም ሻለቃ መሳፍንት በጀግንነቱ ያወደሱ ሲሆን፣ መስዋዕትነቱ ትግሉን ያፋፍማል ሚሊዮኖችን ያፈራል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተያያዘ ዜና ከጦር መሪዎቹ አንዱ የተሰዋበት አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜን ኢትዮጵያ የተጀመረው ውጊያ መቀጠሉን የአካባቢው ምንጮች ሲገልጹ ግንባሩም ይህንኑ አረጋግጧል።
በስርዓቱ ተቆጥተው መሳሪያ ይዘው የሸፈቱ የነጻነት ሃይላትም በተለያዩ የሰሚን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ውጊያ መቀጠላቸውን መረዳት ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ህልፈት ጋር በተያያዘ በሰበር ዜናችን ውስጥ ለተካተተው ምስል ኢሳት የሻለቃ መሳፍንት ቤተሰቦችን እንዲሁም ተመልካቾቹን ይቅርታ ጠይቋል። በአሰራር ላይ በተፈጠረ ግድፈት የአስከሬኑ ምስል በቪዲዮው ዘገባ ውስጥ ማካተቱ ተገቢ ባለመሆኑም፣ ኢሳት ምስሉን በዕለቱ ያስወገደ መሆኑን የኢሳት ዝግጅት ክፍል አስታውቋል።

No comments:
Post a Comment