Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 15, 2016

የኢትዮ ምዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ የአንድ ዓመት እስር እና የገንዘብ መቀጮ ተፈረደበት




አራዳ የሚገኘው 6ኛ የፌደራሉ አንደኛ ደረጃ ወንጀል ችሎት ህዳር 6 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት የኢትዮ ምዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ላይ የአንድ ዓመት እስር እና የ1 ሽህ 500 ብር በግል እና በድርጅቱ ስም ደግሞ የ10 ሽህ ብር መቀጮ እንዲከፍል ሲል ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፎአል።

ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁን ለእስራት እና ቅጣት ያበቃው ምክንያት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን ሕገወጥ አሰራሮችን በመቃወም በጋዜጣው ለሕዝብ በማጋለጥ በእምነት ተቋማት ውስጥ ያለውን ሙስና በማጋለጡ ምክንያት ነው። ከፍርድ ብይን በኋላ ቅጣቱን አስመልክቶ እውነት ትመነምናለች እንጂ አትበጠስም! እውነቱ አንድ ቀን ይወጣል። ይህ ፍርድ የተፈረደብኝ ጋዜጣውን ለመዝጋት ታቅዶ ነው፡፡›› ሲል አስተያየቱን ለፍርድ ቤቱ አሰምቷል። ችሎቱን ለመከታተል በስፍራው የነበሩ ታዛቢዎች ከፍርድ ውሳኔው በኋላ ከሳሽ ካህናት ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ታዛቢዎች እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በእስራት ማሰቃየት እየተለመደ የመጣ ክስተት ሲሆን በተለይ የሃይማኖት ተቋማት የሙስና መስፋፊያ እየሆኑ መምጣቸውን ሳያንስ ከከሳሽነት ተርታ በቀዳሚነት መሰለፋቸው በተደጋጋሚ የሚታይ ክስተት እየሆነ መጥቷል።
ኅዳር ፮ (ስድስትቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-

No comments:

Post a Comment

wanted officials