Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 19, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ፡፡ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡



የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህዳር 07 ቀን 2009 ዓ.ም ከትናነት ወዲያ ቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይ ነብሪ የተባለ ቦታ ለረጅም ሰአት የፈጀ ውጊያ ያደረገ ሲሆን በወያኔ ሰራዊት ላይም ብዛት ያለው ሙትና ቁስለኛ እንዳስቆጠረ ከስፍራው አርበኛ ታጋዩ ሪፖርተራችን ካደረሰን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በትናንትናው ዕለትም ቃፍታ ሁመራ ርዋሳ አካባቢ ልዩ ስሙ ማይጐነጥ የተባለ ቦታ ተመሳሳይ ጥቃት የፈፀመ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰአትም ውጊያው የቀጠለ መሆኑ ሲታወቅ የአርበኞች ግንቦት 7 የተገኘውን ወታደራዊ ድል በአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ በእሁድ ዜና እወጃችን ላይ ዝርዝሩን ይዘን የምንቀርብ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እስከ አሁን ባደረገው እንቅስቃሴ የአካባቢው ነዋሪ ከጐኑ የተሰለፈ መሆኑን ያሳወቀው ሪፖርተራችን፤ በአካባቢው ያለው የወያኔው ሚሊሽያ ኃይልም ከወንድሞቻችን ጋር ውጊያ አንገጥምም በማለት እንዳመፁና ብዛት ያላቸው የሚሊሽያ አባላትም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጐን መሰለፋቸውንም ዘግቧል፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials