አጭር ጠቃሚ ምክር «ሕወሐት ተነካብን፣ የትግራይ ህዝበ ተደፈረ» እያላችሁ ላላችሁ የትግራይ ተወላጆች በተለይ የአረና ፓርቲ አባላት።
እኔ እናንተን ብሆን ይህን ባገራችን አይተነው ያማናውቅ ዘረኝነት ማን አመጣው ብዬ እጠይቅ ነበር። ወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘርን የፖለቲካ መደራጃ ያደረገ ጊዜና ይህንን ይዞ የበላይነት ለመመስረት ሲሞክር ነው ነገሩ የተበላሸው። የዚህ አደገኛ የጥላቻ ፖለቲካ እናትም አባትም ወያኔና ወያኔ ብቻ መሆኑን መረዳት የመፍትሔው ፍለጋ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። በየትም ቦታ እንዳየነው ማንም ህዝብ በአንድ ሀገር ውስጥ የተለየ ጥቅም ሲያገኝ ሲያይ ወይም ባያገኝም እንኩዋን ሊያገኝ ይችላል የሚል ምክንያት ሲኖረው ይበሽቃል፣ ጥላቻ ያድርበታል። ጥላቻ ደግሞ እንደፍቅርና እንደሌላው ስሜት ሁሉ ሰብዓዊ ስሜት ነው። ሩዋንዳ የተጫረሱት ሰዎች እብዶች ወይም የተለየ ስብዕና ያላቸው ሰዎች አይደሉም። መድሎ ተደረገብን የሚሉ ሰዎች የፈጠሩት ቂምና ጥላቻ ያመጣው አስቀያሚ ጥፋት ነው። ። በኢትዮጵያ ውስጥ ከዘረኝነት ጋር ጠብ ያለው ሁሉ ከወያኔ ራስ ላይ መውረድ አይችልም። አሁን ወያኔ የያዘው አካሄድ ከቀጠለ የበለጠ አደጋ የመጣል ብዬ እፈራለሁ። በተለይ የትግራይ ወገኖቻችን ከባድ ችግር ውስጥ ሲወድቁ ይታየኛል። ይህን ነገር ካሁኑ መፍትሔ ልናበጅለት ይገባል። የትግራይ ተወላጅ የሆነ ሁሉ የወያኔውን መንግስት ከህዝብ አታጣሉን የሚል ዘመቻ መጀመር አለበት።ሌሎቻችንም ማገዝ አለብን።
No comments:
Post a Comment