Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 19, 2016

ሰበር ዜና: ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አናንያ ሶሪ ታሰሩ – ከ15 ሺህ ሰው በላይ በኮማንድ ፖስቱ ታስሯል


(ዘ-ሐበሻ) በሶሻል ሚድያ ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትና በተደጋጋሚ በትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ሲጎሳቆሉ የቆዩት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ መታሰራቸው ተሰማ:: የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ከሳምንት በፊት የዞን 9ና የውይይት መጽሔት ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ በኮማንድ ፖስቱ ትፈለጋለህ ተብሎ መያዙ የሚታወስ ሲሆን አናንያ እና ኤልያስም እንዲሁ በተመሳሳይ ተይዘዋል::
ሁለቱ ጋዜጠኞች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ማ ዕከላዊ ታስረው ይገኛሉ::
ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ በቅርቡ በትግራይ ነጻ አውጪው የፕሮፓጋንዳ ራድዮ ፋና ቀርቦ ስር ዓቱን ሲሞግት የነበረ ጋዜጠኛ እንደነበር ይታወሳል::

በተመሳሳይም የቀድሞው የአንድነት አመራር የነበረውዳንኤል ሺበሺም በኮማንድ ፖስቱ እየተፈለገ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል::

መንግስት በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩት ወገኖች ቁጥር 11 ሺህ ነው ብሎ ይናገር እንጂ የታሰሩት ቁጥር ከ15 ሺህ እንደሚበልጥ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አረጋግጠዋል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials