Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, November 13, 2016

ማሪ በፍቃዱ ሀይሉ በድጋሚ ታሰረ



ከተለያዩ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ከዞን፱ ጦማሪያን ስብስብ ጋር በመሆን ሽልማቶችን ያገኘው ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉ ዛሬ ህዳር 02/2009ዓ.ም ጠዋት ከቤቱ በፀጥታ ሀይሎች ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወስዷል።(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)


ጦማሪ በፍቃዱ በ2006ዓ.ም ሚያዝያ17 ከሌሎች የዞን፱ ጦማሪያን እና ሶስት ጋዜጠኖች ጋር በመሆን በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሲሆን ከአንድ አመት ከስድስት ወር የእስር ቆይታ በኋላ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የተከሰሰበትን የሽብር ወንጀል ወደ አመፅ ማነሳሳት ቀይሮ በ20ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ ፈቅዶለት ነበር። በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ያልተደሰተው አቃቤ ህግ በበፍቃዱ ላይና ሌሎች ፍርድ በቤቱ ነፃ የለቀቃቸው የዞን፱ ጦማሪያን (ሶልያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔና አቤል ዋበላ) ላይ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን የፊታችን ማክሰኞ ህዳር 06/2009 ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በጠየቀው ይጋባኝ ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉ ከእስር ከተፈታ አንድ አመት በኋላ ዛሬ ጠዋት ላይ በመኖሪያ ቤቱ እያለ “ኮማንድ ፖስቱ ሊያናግርህ ይፈልጋል” በሚል በፀጥታ ሀይሎች ሊወሰድ ችሏል።

ጦማሪ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በፍቃዱ ሀይሉ ከእስር ከተፈታ በኋላ በአጭር ጊዜ ተወዳጅ በሆነችውና ከ10 እትም በኋላ ከገበያ በወጣችው ውይይት መፅሄት ላይ በዋና አዘጋጅነት ይሰራ እንደነበር ይታወቃል።

ምንጭ: የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት

No comments:

Post a Comment

wanted officials