Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, November 13, 2016

(ሰበር ዜና) ዛሬ ሌሊት የአማራ ታጋዮች በሳንጃ የወያኔ ካምፕን ገንጥለው በመግባት እርምጃ ወሰዱ – በርካቶች ወታደሮችን ገድለው የጦር መሳሪያ ወስደው ተሰወሩ



በጎንደር የአማራ ተጋድሎ ታጋዮች ከትግራዩ ነጻ አውጪ ወታደሮች ጋር የሚያደርጉትን ትንቅንቅ አሁንም እንደቀጠሉ ባሉበት በዚህ ሰዓት ዛሬ ለሊት ለእሁድ አጥቢያ (ሕዳር 4, 2016) የአማራ ተጋድሎ ታጋዮች ሰሜን ጎንደር ሳንጃ የሚገኘው የወያኔ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሰው በርካታ የወያኔ ወታደሮች መግደላቸው ተሰማ::

13925404_701627863308854_2282274968808861391_n
ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ (ሕዳር 4, 2016) ሌሊት ታጋዮቹ ሳንጃ የሚገኘውን የትግራይ ነጻ አውጪ ካምፕ ወረው በወታደሮች ላይ እርምጃ የወሰዱ ሲሆን በዚሁ ካምፕ ውስጥ የነበሩ የጦር መሳሪያዎችን ወስደው መስወራቸው ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ ጠቁሟል::

በዚህ ጥቃት የሞቱ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ቁጥር ለጊዜው ባይታወቅም በርካታ እንደሆኑ ምንጮቻችን ተናግረዋል::

በሳንጃ የአማራ ተጋድሎ ታጋይዮች መሳሪያዎችን ይዘው መሰወራቸው ያስደነገጠው መንግስት በአሁኑ ወቅት ከነርሱ ጋር ተፋጦ ይገኛል:: እንደ ምንጮች ገለጻ የአማራው ሕዝብ ተከዜ የሚገኘው የአማራ ድንበር ድረስ እስካልደረስንና ማንነታችንን ካልስከበርን አንመለስም በሚል ቆርጦ ለትግል ተነስቷል::

 

No comments:

Post a Comment

wanted officials