Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, November 3, 2016

አባ ሰረቀ ከቤተክህነት ፤ እነ ወዲ አድሃኖምም ከቤተመንግሥት ለጊዜውም ቢሆን ገለል ተደርገዋል







አባ ሰረቀ ከቤተክህነት ፤ እነ ወዲ አድሃኖምም ከቤተመንግሥት ለጊዜውም ቢሆን ገለል ተደርገዋል ። ጌታቸው ረዳን የበላ ጅብም አልጮህ ብሏል

 አሁንም ” ምስኪኑ ዐማራ ” ከአሽከርነት የዘለለ አቅም እንደሌለውም ቢሆን ከሚታወቀው የህወሓት ” የቁጩ ” የሥልጣን ማዕድ በርግጫ ተገፍትሮ እንዲባረር ተደርጓል ።


በቅድሚያ ዜና ቤተክህነት ። ቀጥሎም ዜና ቤተመንግሥት ።


ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊውን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጠናቀቋ ይታወሳል ። የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ ሲኖዶሱ ከወትሮው ባልተለመደ መልኩ አስደማሚ መግለጫም ማውጣቱ ይታወሳል ። ከመግለጫዎቹም መሃል መንግስት ከተቋዋሚ ፓርቲዎች ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአስቸኳይ ውይይት ይጀምር ማለታቸውና ” በመላው ዓለም የሚገኙ የስብከተ ወንጌል ሃላፊዎች ስለ ኢትዮጵያዊነት በአዲስ መልኩ ለምእመናን እንዲሰብኩ ይደረግ የምትል ጭንቅ ያላት ዓረፍተ ነገር የያዘች ሀረግ መገኘቷ አግራሞትን ፈጥሯል ። ” የሲኖዶሱ አባላት ተቃዋሚዎች እግር እስኪያወጡ ጠብቄ እቆርጣቸዋለሁ እያለ ህወሓት ሲፎክር እዚያው 4 ኪሎ ቤተመንግሥቱ አጠገብ ቁጭ ብለው ተቃዋሚዎቹ እግር አይደለም ገና ስም ሲያወጡ አየተቀጩ ሲገደሉ ፣ ሲታሰሩ ፣ ሲሰደዱ ዐላየንም አልሰማንም ሲሉ ከርመው አሁን ተቃዋሚዎች ከምድረ ኢትዮጵያ ድራሻቸው ከጠፋ በኋላ በ11 ኛው ሰዓት ቅዱስ ሲኖዶሱ ህወሓት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ቢሮ ከሌላቸው ተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ ማለታቸው አስገራሚም አስቂኝም ሆኗል ። በሌላም በኩል ይሰበክ የተባለው ኢትዮጵያዊነትም ቢሆን እስከዛሬ እንዲቀበርና እንዳይነገር የመከላከያ አጥር ሲበጅለት የከረመ ጉዳይ ሲሆን በመግለጫው ውስጥ የተሰነቀረችዋ ” ከአንዳንድ ቦታዎች የተፈናቀሉ ወገኖች ስላሉ ” የቀድሞው የመረዳዳትና የመከባበር መንፈስ የነበረበት ኢትዮጵያዊነት በደንብ ይሰበክ ሲሉ የስጋታቸው ምንጭ ከወዴት እንደሆነ ጠቁመዋል ። ወይ መፈናቀል አለ ዐማራ ።





በሌላ ዜናም ” አባ ሰላማ ” የተባለውን የክህደት ማስተላለፊያ ብሎግ በዋናነት ከቂርቆሱ መምህር ሰሎሞን ጋር በማዘጋጀት ቅድስት ቤተክርስቲያንን ሲያደሙ የነበሩት መናፍቁ ” አባ ” ሰረቀብርሃን ወልደ ሳሙኤል ከተመደቡበት የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ፀሐፊነት ወንበር መወገዳቸው ታውቋል ። ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ አባ ሰረቀ የአስተዳደር ብቻ ሳይሆን ” እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት ” የሚል መጽሐፍ እስከማሳተም የደረሰ የሃይማኖት ችግርም ያለባቸው ሰው በመሆናቸው በየትኛውም የቤተክርስቲያኒቱ የአመራር ቦታ መቀመጥ የለባቸውም በሚል በብዙ ብንሞግትም ሰሚ አለማግኘታችን ይታወቃል ። የዘር ፖለቲካው ጉዳይ ልክ እንደ ቤተመንግስቱ ሁሉ ቤተክህነቱንም ከእግር ጥፍሩ እሰከ ራስ ፀጉሩ ድረስ የተቆጣጠረው በመሆኑ ሰሚ ጠፍቶ ከላይ እስከታች እስከ አሁን ድረስ ዘረኞች መቅደሱንም ቢሮውንም ተቆጣጥረው ቤተክርስቲያኒቱን የፊጥኝ አስረው በቁሟ አጥንቷ እስኪቀር እየጋጧት መሆኑ ይታወቃል ።


አባ ሰረቀ አሁን ከቦታቸው ለመወገዳቸው የተሰጠው ምክንያት የአቅም ማነስ፣ አለመታዘዝና ችኩልነታቸው እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ፤ ምንፍቅናቸውና ሌብነታቸው ግን ሳይጠቀስ ታልፈዋል ። እንግዲህ ልብ በሉ አባ ሰረቀ በዚህ ሁኔታም ቢሆን ለጊዜው ከዚህ የኃላፊነት ስፍራ መነሳታቸውን የሰማን ቢሆንም ፤ ይህን ዜና በሰማን ማግስት ግን ሰሞኑን ይህንኑ የአቅም ማነስ፣ አለመታዘዝና ችኩልነታቸውን እንደተሸከሙና እሽኮኮ እንዳሉ ከጥቂት ቀን በኋላ በሌላ ከፍተኛ የቤተክርስቲያኒቱ የስልጣን እርከን ላይ መሾማቸውን እንሰማለን ። ቱ ምን አለ በሉኝ ደግሞ ይሄ ባይደረግ ታዘቡኝ ።


በሌላም በኩል ደግሞ ከገደል አፋፍ የቆመው የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስትም በዛሬው ዕለት ወጥ የማያጣፍጠውን ጉልቻ መቀያየሩን በይፋ አውጇል ። 6 አቶዎችን አንድ ወይዘሮና 12 ደክተሮችን 2ፕሮፌሰሮችና 1 ኢንጅነር “አዲሱ የህወሓት ጉልቻዎች” በመሆን እንዲያገለግሉ በዛሬው ዕለት ተመርጠዋል ። ህወሓቶች ከዚህ ቀደም የፓርቲውን ትእዛዛት እስከፈፀመ ድረስ ተሿሚው ለምን ዘበኛ አይሆንም ችግር የለውም በማለት ብዙ ሺህ ሱፍ የለበሱ መሃይሞችን በመሾም ዜጎች በጠራራ ፀሐይ እንዲጨፈጨፉ ማድረጋቸው ይታወሳል ። እናም አሁን ከዚህ ቀደም የተማረ ሰው አለርጂካቸው የሆኑት ህወሓቶች የአራዳ ልጆች “የተማረ ይግደለኝ ” ሲሉ በመስማታቸው እነሆ ይኸው አሁን ዛሬ የእስከአሁኖቹን ዘበኞች ከመጠሪያ ስማቸው በፊት ፕሮፌሰር ፣ ደክተሮችና ኢንጅነሮች የሚል የቅጥያ ማእረግ የተሰጣቸውን ” የተማሩ አዳዲስ ገዳይ” ግለሰቦችን ወደ ስልጣን በማምጣት ስልጣኑን በሙሉ በዶክተሮችና ኢንጅነሮች አጥለቅልቃ ጉድ አስብላናለች ። አዲሶቹ ምሑራን ተሿሚዎች ” በየተማረ ይግደለኝ ” መርህ አሟሟታችንን ለማሳመር ይጥራሉ ተብሎም ይጠበቃል ። ባልተማሩ መሃይሞች እጅ ከመሞት እስቲ በተማሩ ፕሮፌሰሮች እጅ መሞት ምንሸምን እንደሚል በጥቂት ቀናት ውስጥ የምናየው እንደሚሆን እንጠብቃለን ። እንደሚገመተው እነዚህ ምሑራን የቀደሙ መሃይማን ” የጀመሩትን የሚጨርሱ ” ይሆናሉ ተብሎም ይጠብቃል ። የተማረ ይግድለን ይሏችኋል ይኸው ነው ። ታድለን ።


በዚህ አዲስ ካቢኔ ውስጥ አንድ ዓመት ሙሉ የዘለቀ ተቃውሞ በማድረግ በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሐን የኦሮሞ ተወላጆች በግፍ የተጨፈጨፉባቸው የኦሮሞ ልጆችን አፋቸውን ለማስያዝ በሚመስል መልኩ በዛ ያለውን የስልጣን እርከን ኦሮሞ የሆኑም ሆነ የኦሮምኛ ስም ለያዙ ፎርጅድ ኦሮሞ ለሆኑ ግለሰቦች እንዲሰጥ ተደርጓል ። የፈረደበት ዐማራ አሁንም በደሙ በመሠረታት ሀገር ከስልጣኑ ማዕድ ተገፍቶና ተገፍትሮ የበይ ተመልካች እንዲሆን ተፈርዶበታል ። ለዓመታት የዘለቀውና በሺህዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን የኦሮምኛ ተናጋሪዎችን ሲያስፈጅ ደማቸውንም በከንቱ ሲያሰፈስስ የከረመውን ውጤት አላባ የነበረውን የኦሮሞውን የለውጥ እንቅስቃሴ ፤ በጥቂት ወራት ትግል የህወሓትን ጥርስ የነቀነቁት ዐማራዎች ገዢውን ፓርቲ አስደንግጠውና ” ሱሪያቸውንም አስረጥበው ” ለይስሙላም ቢሆን አሁን ይኸው ኦሮሞዎቹን ወንድሞቻቸውን ምንም እንኳን በሙሉ ኃይል የማያዙበት ሹመት ፤ ወደ አርቴፍሻሉና ” የዛፍ ላይ እንቅልፍ ” ወደ ሆነው የህወሓት የኃይል ሚዛን ማስጠበቂያ ወደሆነው የስልጣን ዙፋን አስጠግተዋቸዋል ። ከ21ዱ አዳዲስ ጉልቻዎች ውስጥ 3 ጉልቻዎች ብቻ የዐማራው ብሔር ወኪል ተደርገው የተሾሙ ቢሆንም ፤ እነዚህ ዐማራ ናቸው ተብለው ከተሾሙት ውስጥም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተብለው የተሾሙት ” ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ ” የተባሉት ግለሰብ ከወዲሁ ዐማራ አይደሉም ” ብርሃነ ” ብሎ ዐማራ የለም ትግሬ እንጂ የሚል ተቃውሞ እየቀረበባቸው ነው ። ህወሓት በህይወት እስካለች ድረስና በመርፌም ሆነ በኪኒን የዐማራውን ብሔር ከኢትዮጵያ ምድር እስክታመናምን ድረስ በዋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስትርነቱን ስፍራ እንደማትለቅና ለሌላ ብሔር አሳልፋ እንደማትሰጥም እየተነገረ ነው ። ሌላው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ ሚንስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ከበደ ጫኔም ቢሆኑ ለዐመል ታህልም ቢሆን ይህችንም ስልጣን ያገኙት ” በግፍ ” ከዐማራ ክልል የተፈናቀሉ የተባሉ የትግራይ ተወላጆችን መቀሌ ድረስ በመሄድ በዐማራ ስም ድንጋይ ተሸክመው ይቅርታ በመጠየቃቸው ለውለታቸው የተሰጣቸው ስፍራ እንጂ በችሎታም ሆነ ብሔረሰቡን ወክለው እንዳልሆነ እየተነገረ ነው ። ለዚህ ነው አብዛኛው የመንግስቱ ደጋፊዎች ” ዐመት ሙሉ እየሞተ የሚጮኸው የኦሮሞው ጥያቄ ህጋዊና ትክክልም ነበር ” ። ሲገሉኝ ዝም ብዬ እንደ ኦሮሚያ ልጆች አልሞትም ፤ ስትገድሉኝም እገድላለሁ ፣ ስትተኩሱም እተኩሳለሁ ብሎ የትግሉን አቅጣጫ በፍጥነት ዙሩ ከርሮ ህወሓት የመቃብር አፋፍ ላይ ቆሞ ግብአተ መሬቱን እንዲጠባበቅ ያደረገው አማራው ግን ህገወጥ ድርጊት ነው የፈጸመው ። ለምን ዝም ብሎ እንደኦሮሞ ልጆች አልሞተም ተብሎ ተከሳሽ መሆኑ ይታወቃል ። ከዚህም የተነሳ የዐማራ ልጆች ትምህርት ሚኒስቴር እንዳይማሩ ፣ ሌሎቹም ባለስልጣን እንዳይሆኑ ተፈርዶበታል ።


አሁንም ቢሆን ህወሓት ቁልፍ የሆኑ ቦታዎችን ጠርቅማ እንደያዘች ነው ። የውጭ ጉዳዩን ዘርፍ እና የደም ስር የሆነውን የገንዘቡንና የፈረንካውን ደግሞም የቀርሺና የጨላውን ስፍራም አልለቀቀችም ። ከወራት በፊት የአያታቸውን ስም” ነገዎ” አድርጋ ለኦሮሞ ህዝብ ልትሾምበት የነበረውን አቶ ወርቅነህ ገበየሁን አሁን የጭንቁ ጊዜ ሲመጣ ያለምንም እፍረት ” ነገዎ ” የነበረውን የአያቱን ስም ወደ ቀድሞው ገብረኪዳንነት መልሳ በመቀየር ብሔሩን ” ትግሬ ― ኦሮሞ ” በማድረግ ኦሮሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነትን ስልጣን አገኘ ለማስባልና ” የኦሮሞዎቹን ” አፍ ለማስዘጋት ቀሽም ድራማ በመሥራት በአዲስ ምእራፍ ብቅ ብላለች ። ሌላው የትምህርት ሚኒስቴር አሁንም ትውልድ እየገደለ እንዲቀጥል የተፈረደበት ይመስላል ። የጠቅላይ ሚኒስትርነትና የፕሬዝዳንትነቱ ቦታ ብቻ ሲቀራቸው በዘመነ ኢህአዴግ እንደ ” ማያ ” ራሳቸውን በመቀያየር በብዙ የኢህአዲግ “የሺ ― ሞት ” እርካብ ላይ በማንጠላጠል እንደ ፔንዱለም ስታወዛውዛቸው የከረመችውን ዶ/ር ሺፈራውን አሁን ደግሞ ቀድሞም የሞተውን የትምህርት ዘርፍ በደንብ እንዲገድለው በማሰብ የትምህርት ሚኒስቴርን አሁንም በአፈር መልሰውበት መቃብሩን በደንብ እንዲሠሩ አዲስ ስልጣን ሰጥታ ሹማቸዋለች ። ለየት የሚለው ነገር የባህል ሚኒስቴር ስፍራውን ከሙስሊሞችና ከፕሮቴስታንቶች በቀር እንዲመሩት የማትፈቅደዋ ህወሓት አሁን ለእምነታቸው ኦርቶዶክሳዊ መሆን ማረጋገጫ ባይገኝለትም ብቻ ስማቸው ኦርቶዶክስ የሚሸት ሴት ሚኒስትር ተሹመዋል ብዬ ፈገግ ከማለቴ ፤ ተሿሚዋ አዲሷ ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት ወ/ ማርያም በአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ በሥነ ልሣን ትምህርት ክፍል ውስጥ መምህር የነበረች እና በዩኒቨርሲቲው የፀረ ሙስና ኮምሽን መኮንን በነበረች ጊዜም ስልጣኗን ተጠቅማ ዶር ግርማ አውግቸውን ያሳሳረችው ሴት እንደነበረች ፣ በዚህ ትጋቷም ምክትል ፕሬዘዳንት ሆና ተሹማ እንደነበር ፡፡ ምክትል ፕሬዘዳንት በነበረች ጊዜም ብዙ ክፉ ሥራዎችን አንደሠራች ፣ በዚህ የተናደዱ ሠዎች የዶሯን ኢሜል ሃክ አድርገው ከትዳሯ ውጭ ከሦስት የዩኒቨርሲቲ ምህራን ጋር የነበራትን የወሲብ ግኑኝነት ይፋ አውጥተውባት ልታብድ ትንሽ ቀርቷት እንደነበር፡፡ በዚያን ወቅት ከተማሪ ጀምሮ የወሲብ ቅሌቷን አንብቦ ሁሉም ይስቅባት እንደነበር ፤ በዚያም ኢሜል የተነሳ ሁለቱ አፍቃሪዎቿ ከትዳራቸው እንደተፋቱ ፣ አሁን የደረሰችበት ባይታወቅ እርሷም ወደ ፍቺ ሄዳ እንደበርና በየኒቨርሲቲው ውስጥ ብዙ መምህራንን ለኢህአዴግ አባልነት ትመለምል የነበረች ሴት መሆኗን የሚያሳዩ መረጃዎች መውጣት ጀምረዋል ። እናም ለትዳሯ ያልታመነች ሴት እንዴት ለኢትዮጵያ ሀገሯ የሚታመን ሥራን ትሠራለች ተብሎ ህወሓት እንደመረጣት ከህወሓት በቀር የሚያውቅ ማንም የለም ።


የሆነው ሆኖ የዱሮውም ሆነ አዲሱ ካቢኔ ያው ዞሮ ዞሮ ከኋላው እጅ ጠምዛዡ ህወሓት ናት የሚሉ ተከራካሪዎች እንዳሉት ሁሉ ፤ አይ ምን ሲደረግ በአሁኑ ካቢኔ ላይ እንኳን የምንታማበት አንዳችም ምክንያት የለም ። ከቢኔው ኦሮሞ 9 ፣ አማራ 3 ፣ ደቡብ 5 ፣ ትግራይ 2 ፣ አፋር 1፣ ሶማሌ 1 ነው አድርጎ ነው መርጦ የሾመው ። እናም አሁን የምንወቀስበት አንዳችም አይነት ምንም ምክንያት የለም ይላሉ ። እንዲያውም ይላሉ ህወሓቶች በፊት ከነበሩት 4 የዐማራ ባለስልጣናት ላይ አሁን አንድ ኦሮሞም 9 ተጨምሯል ይሉና በዚህም መሰረት አጠቃላይ የሚኒስትሮች ስብጥር ሲታይ ኦሮሞ 9 ፣ አማራ 7+1 ፣ ደቡብ 6+1 ፣ ትግራይ 4 ፣ አፋር 1እና ሱማሌ 1 ቦታ አግኝተው መንግሥት ከሚፈልገው 30 የሚንስትርነት ስፍራዎች ውስጥ ሕወሓት ያገኘው 4 ቦታዎችን ብቻ ነው ። እናም ህወሓት እጅግ ተፈላጊ የሆነውን የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ስፍራ ለደቡቡ ሰው ለፕሮቴስታንቱ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ የምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነቱን ስፍራም ለሙስሊሙ ለዐማራው ተወላጅ ደመቀ መኮንን ፣ መከላከያ ሚንስትርንም የስልጤው ተወላጅ ሲራጅ ፈርጌሳ እንዲመሩት አድርገን ባዶ እጃችንን ቀርተናል። እናም ከእንግዲህ ወዲህ የህወሓት የበላይነት አለን? አገሪትዋን የሚመራትስ ህወሓት ነውን? ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለ እውነት እነዚህ 4ቱ የህወሓት ተወካዮች የተቀሩትን 26 ሚኒስትሮች ላይ በምን አቅማቸው ጫና ያሳርፋሉ ? በማለት በሳቅ የሚያፈርስ ኮሜዲያቸውን ሊለቁብን ሲሞክሩ ይታያሉ ። እውነታው ግን የሌላ ብሄር ባለስልጣናት ገሚሶቹ የብሔሩ ስም የተሰጣቸው የትግራይ ሰዎች ሲሆኑ እንደ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አይነቶቹ ባለስልጣናት ደግሞ ለላንቲካ የተቀመጡና አዛዦቹ በአማካሪና በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማእረግ በዙሪያው ሰንገው የያዙት እነ ደብረጽዮን መሆናቸው ይታወቃል ። እንዲያው ማን ይሙት በ ” ዶር ጀነራል ሰሞራ የኑስ የሚመራውን መከላከያና 60ዎቹን የመከላከያ የትግራይ ጀነራሎች ስልጤው ሲራጅ ፈርጌሳ ነው የሚያዛቸው ሲባል እንዴት አድርገን ነው ለማመን የምንገደደው ። ” ቀልዱን ተይ ” አለ አዝማሪ ።


በሌላ በኩል አሁንም ቤተክህነቱም ሆነ ቤተመንግስቱ በአንድ ብሔር የበላይነት እየተመራ መሆኑ ግልጽ መሆን አለበት ። ከሚንስትርነት እስከ ተላላኪነት ድረስ ማለት ነው ። በቤተክህነቱ አንድ አባ ሰረቀን ብቻ በማስወገድ ለማስተንፈስ መሞከሩ ጊዜው ያለፈበት ቲያትር ነው ። አሁን የተሾሞት ወደ ስልጣን ሲመጡ የተነገረን የቀድሞዎቹ የአቅም ማነስና የአፈጻጸም ችግር ስላለባቸው ነው ተብሎ በግልፅ መነገሩ ይታወቃል ። ሆኖም ግን እነዚህ በደካማነታቸው ተከሰስው ከስልጣን የተባረሩት በሙሉ በሌላ ሹመት በጓሮ በኩል ሙሉ ስልጣን ይዘው ቤተመንግስት ነው የገቡት ። ኤርትራዊውና ነገር ግን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን የገለግሉ የነበሩት የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ቴዎድርሶ አድሃኖም ምንም እንኳን በትግራይ ተወላጁ የኦሮሞ ቅብ በሆኑት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ቢቀየሩም ፤ እኚህ “ትንሿ ኢትዮጵያ” በደካማ አመራራቸው ምክንያት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያስወገደቻቸው ግለሰብ ፍጥጥ ብለው ዐይናቸውን በጨው በመታጠብ ለዓለም ጤና ድርጅት ጄኔራል ዳይሬክተርነት እየተወዳደሩ መገኘታቸውን ባሰብኩ ጊዜ ስለእሳቸው እኔ ተሸማቅቄ ማለቄ ያሳዝነኛል ። በሳቅ !!


ቤተክርስቲያንም አባ ሰረቀን እንዲህ አሸማቅቃ በደብዳቤ ከማይመጥናቸው ስፍራ ማንሳቷን ብትነግረንም በቅርብ ቀን ልክ እንደ ህወሓት ሁሉ የአባ ማትያስ አገዛዝም እኚህኑ ሰው በሌላ ከፍ ያለ ሹመት መልሶ በሚገርም ደብዳቤ ሥልጣን እንደሚሰጧቸው ይጠበቃል ። እስከዚያው በየአድባራቱ የተሾሙት ሌቦች ለጊዜው ከስልጣናቸው ገሸሽ የሚያደርግ ደብዳቤ እስኪደርሳቸው ድረስ ዘረፋውን አጧጡፈው እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል ።


ሻሎም ! ሰላም !


ዘመድኩን በቀለ ነኝ

ጥቅምት 22 /2009 ዓም

ከራየን ወንዝ ማዶ

No comments:

Post a Comment

wanted officials