Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 1, 2016

ንቅናቄው ይፋ ሆነ – “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ መመስረት ጠንክረን እንሠራለን” ሌንጮ ለታ – “ሕዝባችንን እና ሀገራችንን አስቀድመን እንታገላለን” – ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ



ሕዝባዊው ስብሰባ እየተደረገበት ያለበት ሁኔታን የሚያሳይ ፎቶ
ሕዝባዊው ስብሰባ እየተደረገበት ያለበት ሁኔታን የሚያሳይ ፎቶ
screen-shot-2016-10-30-at-4-40-47-pm
(ዘ-ሐበሻ) አራት ድርጅቶች በጋራ የመሰረቱት “የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ” ዛሬ በዋሽንተን ዲሲ የድርጅቶቹ መሪዎች ሌንጮ ለታ እና ምክትላቸው ዲማ ነገዎ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ (በስካይፕ)፣ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳና አቶ በቀለ ዋዩ በተገኙበት ይፋ ሆነ:: በአሁኑ ወቅት ሕዝባዊ ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድ እየተደረገ መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::
“የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ”ን የመሰረቱት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲና የሲዳማ ሕዝብ ዴሞራሲያዊ ንቅናቄ ሲሆኑ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ንግግር ያደረጉት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር መሪ ኦቦ ሌንጮ ለታ ““ወረቀት መፈራረም ቀላል ነው፤ እዚህ ንግግር ማድረግ ቀላል ነው። ከባዱ ነገር ሀገር ቤት እያለቁ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ጠንክረን መሥራቱ ነው። እጅግ ብዙ ሂደት አልፈን ነው እዚህ የደረስነው። ከፊታችን ብዙ ከባድ ፈተናዎች አሉ።ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገናል። በህዝቦቿ መፈቃቀድ ለምትመሰረት አዲሲቷ ኢትዮጵያ ጠንክረን እንሠራለን!” ሲሉ ቃል ገብተዋል::
በተጨማሪም የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው ”ጨቋኙን አገዛዝ ለማስወገድና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ስምምነት ለተፈራረምንበት ለዚህ ታሪካዊ ቀን በመብቃታችሁ ሁላችሁም እንኳን ደስ ያላችሁ! ንቅናቄው በአራት ፓርቲዎች ይመስረት እንጂ ሌሎች ድርጅቶችንም ወደ ህብረቱ ለማምጣት ተግተን የምንሠራበት ነው። ከራሳችንንና ከድርጅታችን ይልቅ ሕዝባችንን እና ሀገራችንን አስቀድመን ልንታገል ቃል ገብተናል።” ብለዋል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials