Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 1, 2016

በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸም ወንጀል ይቁም !!!

በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸም ወንጀል ይቁም !!!
--
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከሁለት አመት በፊት በ68ኛው ጠቅላላ ጉባኤው አንድ አዋጅ አውጥቶ ነበር፡፡ለአባል አገራት የወጣው አዋጅ በአለም አቀፍ ደረጃ በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸም ወንጀል እንዲያበቃ ይረዳል ተብሎለት ነበር ፡፡
ጋዜጠኞች በሰሩት ስራ ምክንያት ለእስር፣ለሞትና ለተለያዩ ኢሰብአዊ ድርጊቶች ተላልፈው እንዳይሰጡ የሚጠይቀው አዋጅ ከጸደቀ ወዲህ ግን በዛ ያሉ ጋዜጠኞች ተገድለዋል፣ለእስርና ለስደት ተዳርገዋል፡፡ድርጅቱ አዋጁን ተከትሎ ኖቬምበር 2 ‘International Day to End Impunity for Crimes against Journalists’ እንዲሆን በመወሰኑ ቀኑ እየተከበረ ይገኛል፡፡በ2013 በማሊ ሁለት ፈረንሳዊያን ጋዜጠኞች በመገደላቸውም ቀኑ እነርሱን ለማሰብ ጭምር ይውላል፡፡
አገራችንም የተባበሩት መንግስታት አባል አገር መሆኗ ይታወቃል፡፡የድርጅቱ ስምምነትንም በህገ መንግስቷ እንደምትቀበለው በማስታወቋ አዋጁን ማክበር ግድ ይላታል፡፡የመንግስት ባለሰልጣናት በጻፈው ጽሁፍ የተነሳ ለእስር የተዳረገ አንድ ጋዜጠኛ የለም የሚል አቋም በማራመድ ላይ የሚገኙ ቢሆኑም ከዚህ ውጪ ተገኝቶ የታሰረ ጋዜጠኛ መኖሩን ሊያረጋግጡ አልቻሉም፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች አስር ጋዜጠኞች እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝና በቅርቡ የፔን ካናዳ የሰብዓዊነት ሽልማት የተበረከተለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በጠያቂዎች እንዳይጎበኙ መደረጋቸው እየተነገረ ነው፡፡ተመስገን ህክምና ከመከልከሉም በላይ ቤተሰቦቹ የሚወስዱለት ምግብ እንዳይገባለት ተደርጓል፡፡
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በኩላሊት በሽታ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡አሳሪዎቹ በበቀል ስሜት ሰክረው ውብሸትን ህክምና ከከለከሉት ረዘም ያሉ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡እነ የሱፍ ከበደ በምርመራ ወቅት ኢሰብአዊ ክብራቸውን በሚነካ ሁኔታ ምርመራ ተደርጎባቸዋል፡፡
ቀጣዩን ሰኞ በአገር ቤት በወህኒ የሚገኙ ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንን በማሰብ የሚደርስባቸውን ህገ ወጥ ድርጊት እየተቃወምን ስለ ነጻነታቸው ድምጻችንን እንድናሰማ እጠይቃለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials