Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 19, 2016

10.000 ዶላርና 3ኪግ ወርቅ የያዘች ኢትዮጵያዊት ለሁለተኛ ጊዜ በህንድ ተያዘች


=============
ከዚህ በፊት 650ግራም ይዛ በዋስ ተፈትታ ነበር
=============
ከሁለት ወራት በፊት ከአዲስ አበባ ተነስታ ህንድ የደረሰችው ስሟ ያልተጠቀሰ ኢትዮጵያዊት 650ግራም ወርቅ ይዛ በመገኘቷ ታስራ በዋስ ተለቅቃ ነበር ፡፡አሁን በድጋሚ ከአዲስ አበባ ወደ ህንድ በገባችበት ወቅት በተደረገባት ፍተሻ 10.000 የአሜሪካ ዶላርና 3ኪሎ ግራም ወርቅ የተገኘባት መሆኑን የህንድ የገቢዎች ባለስልጣን ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡ 
በደልሂ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በተደረገ የኤሌክትሮኒክስ ፍተሻ በያዘችው ቦርሳ ውስጥ አምስት የወርቅ ጥፍጥፎችና ብዛት ያላቸው የወርቅ ጌጣጌጦች ተገኝተዋል፡፡
የአሜሪካና የህንድ የብር ኖቶች ከሴትየዋ መያዙን የጠቀሱት ባለስልጣናቱ በህንድ ህግ መሰረት ንብረቶቹ ለህንድ መንግስት ገቢ ተደርገው ሴትየዋ በቁጥጥር ስር መዋሏን ጋዜጦች ለንባብ አብቅተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials