Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, November 13, 2016

ሳዑዲዎቹ በተጋቡ በ120 ደቂቃ ተፋቱ





ትዳር ሁለት ጥንዶች በስምምነት በጋራ የሚያቆሙት ውል ነው ።ይህ ውል የሁለቱን ፍላጎት ሳያሟላ ሲቀር ሊፈርስ እንደሚችልም የታወቀ ነው ።
ጋብቻ በውሀ ቀጠነ ሲፈርስ ግን እንዲህ መነጋገሪያ መሆኑ አይቀርም ።የዛሬዎቹ ተፋቺዎች በጋብቻ የቆዮት ለ120 ደቂቃዎች ወይም ለሁለት ሰዓታት ብቻ ነው ።
እርስዎ 120 የሚባለውን የቴቪ የመዝናኛ ፕሮግራም ለማየት በተቀመጡበት ሰዓት ትዳር ተመስርቶ ፈርሷል ቢባሉ ምን ይሰማዎታል ?እንግዲህ ይህ በምንኖርባት አለም እየሆነ ነው ።
ሙሽራው ሙሽራይቱን ከሰርጋቸው በፊት የሰርግ ፎቷቸውን በየትኛውም የማህበረሰብ ሚዲያ እንዳትለቅ አስጠንቅቋት ነበር ።ሙሽሪት በሰርጉ ዕለት የተነሱትን ፎቶ በስናፕ ሾት አማካኝነት በጣም ለሚቀርቧት የሴት ጓደኞቿ ትልካለች ።
አዲሱ ሙሽራ ውላችን ፈርሷል በማለት ፊርማውን ለመቅደድ በቅቷል ።
የወሬው ምንጭ በሳዑዲ ጋብቻ በማህበራዊ ድረገፅ ምክንያት ሲፈርስ ይህ የመጀመሪያው አለመሆኑን በመጥቀስ ከጓደኞችዋ ጋር ቻት የምታደርግበት ሰዓት በመብዛቱ የተማረረ አባወራ ፍቺ ጠይቆ ነበር ብሏል ።
ለማንኛውም በኬንያ ቆይታዬ አንድ ወዳጄ የታደመበትን ሰርግ ሙሽሮች ፎቶ በፌስቡክ በመለጠፉ መልስ ሳይጠራ መቅረቱን አስታውሳለሁ እናም መልካም ዕሁድ ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials