ጎሳዬ ተስፋዬ፣ ኃይልዬ ታደሰ፣ ማንአልሞሽ ዲቦ፣ ፍቅረአዲስ ነቃጥበብ፣ ታምራት ሞላ፣ መልካሙ ተበጀ፣ አምሳል ምትኬ፣ ማዲንጎ አፈወርቅ፣ ታደሰ ዓለሙ አለሙና ሌሎችም በርካታ ድምጻዊያን ከዚህ ታላቅ የሙዚቃ ሰው ሥራ ተቀብለዋል:: የርሱ ሥራ ስኬት አጎናጽፏቸዋል:: የጎሳዬ “ህልሜን” የኃይልዬ ታደሰ “ይሞታል ወይ?” የሚሉት ዜማዎች ይጠቀሳሉ::
ሙዚቃ አቀናባሪ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ ሙሉጌታ አባተ ባደረበት ሕመም በኮሪያ ሆስፒታል አይሲዩ ውስጥ ሕክምና ሲከታተል ቆይቷል፣ ለሕክምናው ወጪ የሚሆን ገንዘብ በማሰባሰብ ሕዝቡ እንዲረባረብ ቢጠይቀም የታሰበውን ያህል አልተገኘም፡፡
ሙሉጌታ ወደ ሙዚቃው የገባው በለጋ ዕድሜው ሲሆን፣ ለበርካታ ድምፃውያን ግጥምና ዜማ ሰጥቷል፡፡ ሙዚቃም አቀናብሯል፡፡ ከአማርኛ ሙዚቃዎች በተጨማሪ ለኦሮምኛ, ትግርኛና ጉራጊኛ ሙዚቃ ያበረከተው አስተዋጽኦም ቀላል አይደለም፡፡ ከ500 በላይ ሙዚቃዎችን አቀናብሯል:: ሙሉጌታ ያደረበት ሕመም ጠንቶበት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል::
No comments:
Post a Comment