Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 31, 2018

አርበኞች ግንቦት ሰባት ወደ ሀገር ቤት ሊገባ ነው


 አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሩ ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ቤት እንደሚገባ አስታወቀ።
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የንቅናቄው አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት መደረጉን የጠቀሰው ንቅናቄው የተጀመረውን ለውጥ ወደ ግቡ እንዲደርስ ለማድረግ ወደ ሀገር ቤት መግባቱ አማራጭ የሌለው እንደሆነ በማመን ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውቋል።

ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ


 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከ 27 ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ  ትናንት ጉዟቸውን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር  ላደረገው ልኡል እግዚአብሔር ምስጋና አቅርበዋል።እንዲሁም ይህ እርቅ ኣንዲወርድ አስተዋጻኦ ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ምስጋናቸውን  አቅረበዋል።
መጠለያ ሆና ላቆየቻቸው አሜሪካም ሰላሟን እና በጎውን ሁሉ ተመኝተውላታል።
ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከ 27 ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተጓዙ።ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ  ትናንት ጉዟቸውን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር  ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምስጋና  አቅረበዋል። መጠለያ ሆና ላቆየቻቸው አሜሪካም ሰላሟን እና ብጎወን ሁሉ ተመኝተውላታል።
“በሃዘን እና በለቅሶ ከሃገራችን ተሰደን ነበር።ነገር ግን የእግዜብሄር ግዜ ሰለደረሰ ወደ አገራችን እንመለስ ዘንድ እነሆ የእግዜብሄር ፈቃድ ሆኗል”  በማለት ለመመለስ መወሰናቸውን እና ቀን መቁረጣቸውን ትናንት ሃምሌ 23 /2010 ያስታወቁት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ሃምሌ 19 ቀን 2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት የተካሄደው ሥምምነት ለዚህ ወሳኔ እንዳበቃቸው አመልክተዋል።
በተለይም ቅዳሜ ሃምሌ 21 /2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ ያቀረቡላቸው ጥያቄ  ለአፋጣኙ ርምጃ ምክንያት መሆኑንም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ  አመልክተዋል።
ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ  ትናንት ጉዟቸውን በተመለከተ በሰጡት  በዚሁ መግለጫ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር  ከፍተኛ ግፊት እና አስተዋጾ ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምስጋና  አቅረበዋል። መጠለያ ሆና ላቆየቻቸው አሜሪካም ሰላሟን እና በጎወን ሁሉ ተመኝተውላታል።
ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ  እና አብረዋቸው ዛሬ ከዋሺንገተን  ዲሲ የተነሱት አባቶች ነገ ረቡዕ አዲስ አበባ ይገባሉ። ከፍተኛ የአቀባበል መርሃ ግብርም ተዘጋጅቷል። 6ኛው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ዛሬ አዲስ አበባ  ላይ በሰጡት መግለጫ የቤተክርስቲያኒቱ አንድነት በመመለሱ  ደስታዬ ወሰን የለውም ብለዋል።

Monday, July 30, 2018

ሰመጉ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከ700 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ


ሰመጉ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከ700 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ
የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ)፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመረጃ አስደግፎ በ144ኛ ልዩ መግለጫው በዝርዝር ሪፖርቱ ከ735 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።
ከጥር 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 2010 ዓ.ም የተፈፀሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚያጣሩ ባለሙያዎቹን ጥቃቱ ወደተፈፀመባቸው አካባቢዎች በመላክ የማጣራት ሥራውን ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ አከናውኖ፣ 258 የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች በሶማሊ ልዩ ሃይል ሲገደሉ፣ በኦሮምያ ክልል የነበሩ 451 ሰላማዊ የሶማሊ ብሄር ተወላጆች መገደላቸውን ገልጿል።
ኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ሐረርጌ ባቢሌ፣ ሐረር፣ አማሬሳ፣ ሀሮማያ፣ አወዳይ፣ ሜታ (ጨለንቆ)፣ ድሬደዋ፣ ፈዲስ፣ ኮምቦልቻ፣ ጉርሱም፣ ጃርሶ። በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ፣ ሚኤሶ፣ ቦርደዴ፣ መሰላ፣ ጡሎ። በምሥራቅ ጉጂ ሊበን እና ጉሚ ኤልደሎ። በምዕራብ ጉጂ ቡሌ ሆራ። በምስራቅ ሸዋ አዳማ አጣሪ ቡድኑ በመዘዋወር ምርመራዎችን አድርጓል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ማኔጅመንትንት፤ ኮሌጅ 1 እና ኮሌጅ 2፣ በባቢሌ፣ ሞምባስና ዱከቱ ሪፖርቱን አጠናቅሯል።
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከክልላችን ይውጡልን በሚል በተፈፀሙ ጥቃቶች እና ግጭቶች ምክንያት ከጳጉሜ 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ ወር 2010 ዓ.ም. ድረስ ብቻ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ባደረገው ምርመራ የበርካታ ንጹሃን ሕይወት መጥፋቱን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ዜጎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸውን እንዲሁም የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ሰመጉ አረጋግጧል። በመሆኑም በተጠቀሰው ግዜ ውስጥ ብቻ ከ344 ሺህ በላይ ዜጎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸውን በምርመራ ስራው ለማረጋገጥ ችሏል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በሶማሌ ልዩ ኃይል በተፈፀመው ጥቃት 160 ሰላማዊ የኦሮሞ ብሄር ተውላጅ የሆኑ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በተመሳሳይ በባሌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በሶማሌ ክልል አዋሳኝ በተፈፀሙ የጅምላ ግድያዎች 98 ንፁሃን ዜጎች ተጨፍጭፈዋል። ከልዩ ኃይል በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በመከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት 88 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዞኑ ከግድያ በተጨማሪም በሦስት ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀልም ተፈፅሟል። አድራሻቸው የማይታወቁም መኖራቸውን ሰመጉ ዜጎችን በስም ዝርዝርና በምስል አስደግፎ አውጥቷል።
በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚኖሩ የሶማሌ ብሄር ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ የመብት ጥሰት ጥቃቶች መፈፀማቸውን ሰመጉ በሪፖርቱ አካቷል።
ሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተገኘ ሪፖርትና የሰመጉ ባለሙያዎች ቦታው ድረስ በመሄድ ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦችና ከዐይን እማኞችን በማግኘት ማጣራት አድርጓል። ይህን ዋቢ በማድረግ በኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ውስጥ በተነሱ ግጭትና ጥቃቶች ምክንያት 451 ሰላማዊ የሶማሌ ብሄር ተወላጅ ዜጎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል። በተጨማሪም ቁጥራቸው 256 በሚሆኑት ላይ ከባድና ቀላል አካላዊ ጥቃቶች ተፈፅመውባቸዋል። ከነዚህ ውስጥ በአስር ሴቶች ላይ ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል። ከሰላሳ በላይ ዜጎች እስካሁን ያሉበት አድራሻ አይታወቅም።
ሰመጉ በ144ኛው ልዩ መግለጫው እንዳለው በሁለቱም ክልሎች ውስጥ ለዘመናት በኖሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ፣ አካል ማጉደል፣ በጅምላ ማፈናቀልና የወሲብ ጥቃቶች ተፈፅመዋል። ይህን በገለልተኛ አካል በማጣራት ወንጀለኞቹን ለፍትህ አካል ማቅረብ ይገባል ሲል ሪፖርቱን አጠቃሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጨረሻ ጉብኝታቸውን በሚኒሶታ አካሄዱ


 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአሜሪካ የመጨረሻ ጉብኝታቸውን በሚኒሶታ አካሄዱ።

ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ጋር በመሆን በሚኒያፖሊስና ሴንት ፖል ከተሞች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር የተገናኙት ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ኢትዮጵያውያን ልዩነታቸውን ወደ ጎን አድርገው ለሀገራችን ለውጥ በአንድነት እንዲነሱ ጥሪ አድርገዋል።
አቶ ለማ መገርሳም ሀገራችን ኢትዮጵያ ለሁላችን የምትበቃ በመሆኑ ለእድገቷ በጋራ እንስራ ሲሉ ጠይቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማምሻውንም በሚኒሶታ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሰጡበት መድረክ መካሄዱን ለማወቅ ተችሏል።

Sunday, July 29, 2018

በአማሮ ወረዳ እና በጉጂ መካከል እንደገና ግጭት በማገርሸቱ የሰዎች ሕይወት አለፈ


በአማሮ ወረዳ እና በጉጂ መካከል እንደገና ግጭት በማገርሸቱ የሰዎች ሕይወት አለፈ
 በድንበር በማካለል ስም የተነሳውና ለአንድ አመት ያክል የዘለቀው በአማሮ ወረዳ በሚኖሩ የኮሬ ብሄረሰብና በጉጂ ኦሮሞ መካከል የተከሰተው ግጭት ዛሬ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ ዛሬ ከዲላ ወደ አማሮ ኤፍ.ኤስ.አር የጭነት መኪና ሲያሽከረክር የነበረ፣ በጀሎ ቀበሌ ቅዱስ ዮሃንስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት የታጠቁ ሃይሎች ተኩስ በመክፈት ሹፈሩን ጨምሮ ሌላ አንድ ተሳፋሪ ወዲያዉ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል። ይህንን ተከትሎም ተኩስ በሁለቱ ወገን ተከፍቶ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የተኩስ ልዉወጥ እየተደረገ እንዳለና እስከ አሁን ሰዓት በኮሬ በኩል ብሻሮ ዘለቀ የሚባል አርሶአደር እንደተገደለ፣ ሌሎች ሶስት ደግሞ ቆስለዉ ኬሌ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአካባቢዉ የመከላከያ አባላት ቢኖሩም፣ ግጭቱን ማስቆም እንዳልቻሉ በተለይ መከላከል ያልቻሉት ደግሞ መኖሪያቸዉ ከተማ ላይ ስለሆነ ከግጭት ከአካባቢዉ 20 ኪሜ ርቀት ላይ እንደሚኖሩ በህብረተሰቡም ቅሬታ እየፈጠረ እንዳለ ግጭቱ ላይ ዘግይቶ በአካባቢዉ ከደረሱት መከላከያዎች መሃልም አንዱ በጥይት ተመትቶ እንደቆሰለ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ከቡሌ ሆራና ከወረዳዉ ቆላማ ቀበሌዎች በተለይ ከዶርባዴና ጀሎ፣ የተፈናቀሉ ከ 21 ሺ 800 በላይ ዜጎችም ጉዳይ በኢሳት በተደጋጋሚ መዘገቡን ተከትሎ፣ የሃገር ዉስጥ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ለመስጠት ቢሞክሩም፣ አስከ ዛሬ በቂ እገዛ በማጣት ለከፋ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ። ከሃምሌ 16 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ የሞቱት ዜጎች ቁጥር ከአማሮ ብቻ 60 የቆሰሉት ደግሞ 114 መድረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

Saturday, July 28, 2018

Rival Ethiopian Orthodox church synods agree to merge


The two synods of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church have agreed to resolve their differences and reconcile ending 27 years of acrimonious relationship.
Image result for abune merkorios
The split started in 1991 when Patriarch Abune Merkorios was forced to abdicate his position and forced into exile. He was replaced by the late Abune Paulos who was hand picked by the Tigray People’s Liberation Front.
In a reconciliation process kick-started by Prime Minister Abiy Ahmed, the exiled synod and its rival in Ethiopia headed by Abune Matias have agreed to merge. According to reliable sources, Abune Merkorios will return to Ethiopia to be reinstated as the patriarch. The current patriarch, Abune Matias, will abdicate his seat and will become head of administration.
Ethiopians on social media have been expressing excitement over the reconciliation that are referring to it a miracle.    

Friday, July 27, 2018

በሃረር ወጣቶችን እርስ በርስ ለማጋጨት የተደረገው ሴራ ከሸፈ


በሃረር ወጣቶችን እርስ በርስ ለማጋጨት የተደረገው ሴራ ከሸፈ
ወኪላችን እንደገለጸው ጠ/ሚ አብይ አህመድን ለመደገፍ፣ በኢንጂኒየር ስመኛው ሞት ሃዘናቸውን ለመግልጽ እንዲሁም የአሟሟታቸው ሁኔታ በፍጥነት ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ለመጠየቅና ጄ/ል አብርሃ የምስራቅ እዥ አዛዥ በነበሩበት ወቅት ታፍነው የተወሰዱትን የአቤል ፈቃዱ ወይም አቤል ኩባ እና የደረጀ ሙሉጌታ ሁኔታ ለህዝብ እንዲገለጽ ለመጠየቅ የወጡ ፋኖና ዘርማን የሚወክሉ ወጣቶችን ከቄሮዎች ጋር ለማጋጨት የተጠነሰሰው ሴራ ከሽፏል።
ወጣቶቹ ጠዋት ላይ ኮከብ የሌለበትን ሰንደቃላማ ይዘው ሲወጡ፣ ለቄሮዎች “የእናንተን ትግል ለመቃወም ፋኖዎችና ዘርማዎች የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ነውና ተቃወሙዋቸው” የሚል መልዕክት እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን፣ የቄሮ አባላትም ወደ ወጣቶች ሄደው ከፋኖና የዘርማ አባላት ጋር ውይይት ሲያደርጉ፣ የተሰጣቸው መረጃ ሆን ተብሎ በህዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር መሆኑን ሲረዱ፣ “ በሚቀጥለው ጊዜ አብረን ሰልፍ እናደርጋለን” በማለት ሴራውን አክሽፈው ተለያይተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን በቄሮ ስም የተወሰኑ ብሄሮችን እየለዩ ቤታቸውን እንዲለቁ ሲያስፈራሩ ከሹፌሮች በጉልበት ገንዘብ ሲቀበሉና ህዝቡን እያሰቃዩ ሲዘርፉ የነበሩ 6 ወጣቶች፣ በቄሮዎች ትብብር እሁድ ሃምሌ 21 ቀን 2010 ዓም ከያዙዋቸው የእጅ ቦንቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በሌላ በኩል ከህወሃት አመራሮች ጋር በመሆን ለአመታት ወጣቶችን ሲያስገድልና ሲያሳፍን የነበረ አንድ ግለሰብ ማምነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ ተገኝቷል። በሶፊ ወረዳ ቄሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተገደለው ይህ ግለሰብ፣ በአካባቢው ቄሮዎችን በማስተባበር ይመራ የነበረን ወጣት እንዲገደል ማድረጉን፣ በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወረ መንግስትን የሚቃወሙትን እየጠቆመ ሲያሳስር መቆየቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ግድያውን ማን እንደፈጸመው እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም።

Ethiopians shocked over sudden death of mega dam project chief


ESAT News 
 The chief engineer and head of the the Grand Ethiopia Renaissance Dam (GERD) was found dead in his Land Cruiser at Meskel Square in the capital. The passing of the engineer has sent shockwave across Ethiopia.
GERD was said to become Africa’s largest hydropower dam with a capacity of 6,450 MW when completed. However, the
project has been dogged by controversies. According to reports , there has been massive embezzlement by top TPLF officials undermining the progress of the project.
Bekele headed GERD since its launch in April 2011. The engineer reported to Debretsion Gebremichael the Board Chair of Ethiopian Electric Power Corporation until recently.
Prime Minister Abiy Ahmed had expressed concern over the progress of the project. He reportedly said  that with the current pace the dam was unlikely to be completed in 10 years.

Thursday, July 26, 2018

የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ


የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ
 ግድቡን በዋና ሃላፊነት ሲመሩ የነበሩት ኢንጂነር ስመኛው በቀለ መስቀል አደባባይ ከዋናው መንገድ ገባ ብሎ በቪ 8 መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ መገኘቱን የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ ዘይኑ፣ ኢንጂነር ስመኛው ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው እንደነበረ፣ በቀኝ እጃቸው በኩል ኮልት ሽጉጥ መገኘቱን ገልጸዋል። ፖሊስ የአይን እማኞችንና ማስረጃ ይሰጣሉ የተባሉትን ሰዎች ይዞ ምርመራ እያደረገ መሆኑን፣ ቢሮአቸውንም ፈትሾ መረጃ ማሰባሰቡን ተናግረዋል።
የኢንጂነሩ አሟሟት በርካታ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል። በዜናው የተደናገጡ ወጣቶች በድንገት ተሰባስበው ወደ ኢቲቪ ቢሮ በመሄድ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። እንዲሁ በርካታ የመዲናቅዋ ወጣቶች ኢንጂነሩ ሞተው በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በጎንደር ከተማም እንዲሁ ሞቱ ያስደነገጣቸው ወጣቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ቁጣቸውን ገልፀዋል።
ኢንጂነሩ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስራውን በበላይነት በመቆጣጠር ግድቡ አሁን ላለበት ደረጃ አድርሰውታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ሞት እንደሰሙ መደንገጣቸውንና ሀዘናቸውን መግለጻቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል።
እንደ ኃላፊው አቶ ፍጹም አረጋ ገለጻ ዶክተር አብይ ይህን አስደንጋጭና ልብ ሰባረኢ ዜና የሰሙት አሜሪካ ሲደርሱ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ለኢንጂነር ስመኘው በቀለ ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማስተላለፋቸውንም ከአቶ ፍጹም ገለጻ ለመረዳት ተችሽሏል።

Wednesday, July 25, 2018

የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ።

ላለፉት 12 አመታት በህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ በኃይል ተዘግተው ከነበሩት የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ።

ላለፉት 12 አመታት በህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ በኃይል ተዘግተው ከነበሩት የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ።
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ካለፉት ስድስት ዓመታት እስር በኋላ በቅርቡ ከእስር የተፈታው ጋዜጠኛ እስክንድር በአጭር ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የሚዲያ ውጤቶች ከህዝቡ ጋር ለመገናኘት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል.።
የእስክንድ ቢሮ ከ12 ዓመታት በኋላ ሲከፈት ጋዜጠኞች እና የዞን ዘጠን ጦማርያን ተሰባስበውም ኬክ በመቁረስ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል.።
በስደት አሜሪካ የምትገኘው የሰርካለም አሳታሚ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ባለቤቱ ሠርካለም ፋሲል ጉዳዩን አስመልክታ በሰጠችው አስተያዬት፦“.ነፃው ፕሬስ ታፍኖ አይቀርም….የህዝብ አደራ አለብን!”ብላለች።
ትናንት በሆላንድ -ደንሀግ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመቀበል በተሰናዳው ዝግጅት ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ባደረገው ንግግር ከእስክንድር ነጋና ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር አንድ ላይ በመሆን በቴሌቬዥንና በጋዜጣ ወደ ጋዜጠኝነት ሥራው ለመቀላቀል ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አስታውቆ ነበር።

Tuesday, July 24, 2018

የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ግድያ በአስቸኳይ እንዲጣራ ተጠየቀ


 የኢንጅነር ስመኘው በቀለ ግድያ በአስቸኳይ ተጣርቶ ፍትህ እንዲሰጥ በጎንደር ፣ ማክሰኝትና በባህርዳር ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች ጠየቁ።
በጎንደር በነበረው ህዝባዊ ቁጣ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ግጭት ተፈጥሮ አንድ ወጣትና አንድ ታዳጊ በጥይት ተመተው ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ትላንት ጠዋት አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተገድለው የተገኙት የአባይ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ጉዳይ በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ብርቱ ሀዝን ፈጥሯል።
በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር  እንደተገለጸውም ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በጥይት ተመትው ህይወታቸው አልፏል።
ምርመራው ገና በሂደት ላይ ቢሆንም ድርጊቱ የግድያ እርምጃ መሆኑን በመጥቀስ በተለያዩ አከባቢዎች ቁጣ ተቀስቅሷል።
ቁጣው ወደ ሰላም መደፍረስ እንዳያመራ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ከየአቅጣጫው መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።
ዜናው እንደተሰማ በተለይ በአዲስ አበባ ና ጎንደር ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን በኢንጅነር ስመኘው የትውልድ ቦታ ማክሰኝትም ህዝቡ አስቸኳይ ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ ይገልጽ ሲል ጥያቄ አቅርቧል።
ወጣቶች ተሰባስበው ፍትህ እንዲሰጣቸውና ገዳዩች እንዲያዙ በመጠየቅ መሪር ሀዘናቸውን አሰምተዋል።
ዛሬ ማንነቱ ባልታወቀ አካል በጎንደር የተጠራ ተቃውሞ ግጭት አስከትሎ አንድ ወጣት በጥይት መመታቱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በትላንትናው ዕለት በጎንደር የሰላም ባስ አውቶብስ መቃጠልና ሁሌታውን ወደ ለየለት ትርምስ ለመለወጥ የሚንቀሳቀስ ሃይል በመኖሩ ህዝቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እየተጠየቀ ነው።
በጎንደር ወደ አደባባይ የወጣው ህዝብ ወደ ግጭት እንዳይገባ በሀገር ሽማግሌዎች በተላለፈ መልዕክት ሁሉም ወደ ቤቱ እንዲበተን መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።
ወጣቱ በዚህ ቁጭት ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይሄድ በተለይም እየታየ ያለውን የለውጥ ሂደት የሚቀለብስ እርምጃ እንዳይወስድ ስሜቱን እንዲቆጣጠር መልዕክቶች ከተለያዩ አከባቢዎች እየተላለፉ ነው።
በባህርዳር ወጣቶች በቀበሌ 04 ድንኳን ጥለው ሀዘናቸውን እየገለፁ ሲሆን ፍትህ ለኢንጅነር  ስመኘው በቀለ የሚል መልዕክት በማሰማት ምርመራው በአፋጣኝ ተጠናቆ ውጤቱ እንዲታወቅ ጠይቀዋል።
በአዲስ አበባም በኢንጅነር ስመኘው መኖሪያ ቤት የሀዘን ፕሮግራም በመካሄድ ላይ መሆኑ ታውቋል። የኢንጅነር ስመኘው ወላጅ አባት ከጎንደር አዲስ አበባ መግባታቸም ተገልጿል።
በሌላ በኩል የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን እሁድ እንደሚፈጸም ለማወቅ ተችሏል።
በመንግስት በኩል የቀብር ስነስርዓቱን ለታላላቅ ሰዎች በሚሰጥ ተገቢ ክብር እንደሚፈጸምም ታውቋል።
በአዲስ አበባ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጽም የወጣው መረሃ ግብር ያሳያል።

Saturday, July 21, 2018

Menafiqan Addiss netelaa zemaa leqequu








Osoo hin dubbisiin bira hin darbiinaa.

G/W/B/A/Limmuu magaalaa galiilaa irraa Qillensa irraa akkaan olchuuf karaa fb naaf ergame

======= =======
Share gochuun waliif dabarsu hin dagatiina.


guyyaa 9,11,2010 guyyaa keessaa sa'atii 6:30 G/W/B/A/Limmuu magaalaa galiilaatti balaa motoraatiin nama maqaan isaa ...... ( Maqaa isaanii natu bekaa hanbiisee) .... lubbuun isaa darbee gaafa guyyaa 10,11,2010 immoo awwalchi isaa waldaa mulu wangeelii kan jedhamutti rawwate......
harra jechuun 12,11,2010 immoo amana warra Protestantii kan tahe tokko guyyaa keessaa naannoo saati 8;00 bakka maatiin isaa fi haatii mana isaa jirtu deemuun yesuusitti natti mullatte deema awwala diiga inni Hin duune jechuun....
kan dhagahuun ummanni magaalitti utuu Hin hafiin buqqaye ilaaluuf deemani turani kanaan booda gaafa deemanii awwaalcha irraa diiganii,saanduqaa reeffa banaan hundumtu naasuu of wallaalee yegguus hedduuwwan amantoota kana afuurtu nurraa buhe jechuun yeroon lafa jeeqanitti raajiin ani ammaaf maqaasa adda baafachuu Hin dandeenye kun.....
huccuu reeffa kanatti marame jiru gaafanni irraa saaquu homaa waanti haaraa gaafa dhibu itti jedhe iyyuu jalqabee maqaa yesuusiin kahi jechuun gaafa dadhabuu ani Hin dandeenye ittiin jechuun firaaf maatii akkasumas namoonni ilaaluu deeman hundinuu booyichan of wallaalan hedduu wwan immoo foolli reffichan kan gaggaban illee ni jiru yeroo amma kana obbo Abdisaa kan jedhaman haala rakkisa keessatti argamuu hedduwwaniins kan raajeffachise ture.maaloo sitti toleef warreen sagalee raajota sobduu dhagahuun karaa irraa kaha jiraniifi hanga isaa du'erra illee awwala diiganitti kanneen gaha kanaaf barumsa haa tahu ifoomsi galatoomi!!
seenaa dhugaa amanuuf kana namaa rakkisuuf ajaa'ibaa addaati waanti kan raawwate bakka geggeessitoonni,barsiiatonni wangeela,raajonni waldichaafi waldalee aanicha biroo argamanitti ture.

Barbbaachiisa ta'e yoo argame Maqaa isaaniis ta'e suraa fi Vidi'oon kan degaraamee waan jiruf gadhiisu dandda'ama.

Raajootii sobduu irraa of qusadha.

Friday, July 20, 2018

የኤርትራ መንግስት ድንበር ላይ ሰፍሮ የነበረውን ጦሩን እንዲነሳ አደረገ


 የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ አጎራባች ድንበር ለይ ሰፍሮ የነበረውን ጦሩን ከአካባቢው እንዲነሱ ማድረጉን ሮይተርስ ዘገበ ።
በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሰፈረው የኤርትራ ጦር ከአካባቢው እንዲነሳ የተደረገው በሁለቱ ሀገራት መካከል የተወሰደውን የእርቅ እርምጃ መነሻ በማድረግ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ኢትዮጵያ ከግጭቱ ወዲህ የመጀመሪያ የተባሉትን አምባሳደር አቶ ሬድዋን ሁሴን በአስመራ መመደቧ ታውቋል ።
Image may contain: one or more people, sky, outdoor and nature

ኢሳያስ አፈወርቄ የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት ጋበዙ


(ኢሳት)
 የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት አስመራ ጋበዙ።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብዣ መሰረት ነገ አስመራ ይገባሉ።
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገጻቸው እንደገለጹት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ በቅጽል ስማቸው ፎርማጆ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ነገ ማለዳ አስመራ ይገባሉ።
የኤርትራ መንግስት አልሻባብን ይረዳል በሚል በቀረበበትና በኋላም ምንም ማረጋገጫ እንዳልተገኘበት በይፋ በተገለጸው ወንጀል ሳቢያ ከሶማሊያ መንግስታ ጋር ጤናማ ግንኙነት ሳይኖረው ቆይቷል።
አሁን ላይ ታዲያ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ በሁለቱ ሃገራ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሃገሪቱን ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆን ወደ ኤርትራ እንዲመጡ ግብዣ አቅርበውላቸዋል።
የሃገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገጻቸው  የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አስመራ እንደሚገቡ አስፍረዋል።
ይህ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት በዚህ ሰአት ደግሞ ፎርማጆ ኤርትራ ገብተው ጉብኝታቸውን መጀመራቸው ተሰምቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ኤርትራን ጎብኝተው ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ በይፋ የተባበሩት መንግስታትን መጠየቃቸው ይታወሳል።
ከአካባቢው ሃገራትም ሆነ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ግንኙነቷ በፍጥነት እየተሻሻለ ያለችው ኤርትራ ከጅቡቲም ጋር ውዝግባቸውን ለመፍታት በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ተመልክቷል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያና በዩናይትድ አረብ ኢምሬት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
በዩናይትድ አረብ ኢምሬት ጉብኝታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር የተገናኙ ሲሆን ሁለቱ ላደረጉት የሰላም አስተዋጽኦ የሃገሪቱን ከፍተኛ ሜዳሊያ መሸለማቸው ይታወሳል።

Celebrity worship አምልኮተ -ስመጥር- አልበርት አይንስታይንና ቻርሊ ቻፕሊን

Image may contain: 5 people, people smiling, text and closeup


(Celebrity Worship)

(ግሩም ተበጀ)

ክፍል አንድ 

✍️ City Lights የተሰኘውን የቻርሊ ቻፕሊንን ፊልም ለመመረቅ አልበርት አይንስታይንና ቻርሊ ቻፕሊን ሎስ አንጀለስ እንደገቡ፣ የሎስ አንጀለስ ነዋሪ ግልብጥ ብሎ ነበር የተቀበላቸው። 

✍️ የህዝቡ እንዲህ በነቂስ ወጥቶ እነሱን መቀበል፣ የሚዲያው ወከባ ሁሉ፣ ለአይንስታይን ፍፁም ግራ የሚያጋባ ነበር የሆነበት። በዚህ ወከባ መሃል፣ ቻርሊ ቻፕሊን ወደ አይንስታይን ጆሮ ጠጋ ይልና እንዲህ ይለዋል፣ 

✍️ “ይሄ ሁሉ የሰዉ ግርግር ለምን ይመስልሃል…እኔ ስለገባኋቸው ነው - አንተ ደግሞ ስላልገባሃቸው !” 

✍️ የሆነው ሆኖ አይንስታይን እግሩ የአሜሪካን አፈር ከረገጠበት ጊዜ አንስቶ ባስተዋለው የአሜሪካ ህዝብና ሚዲያ ለስመ-ጥሮች ባለው ከልክ ያለፈ አምልኮ እንደተገረመ ነበር። 

✍️ በየሄደበት ቦታ ሁሉ፣ እንደልዩ ፍጡር የሚከበውን የሰው አጀብ ባየ ቁጥር፣ አጠገቡ ያሉትን የሚጠይቀው ጥያቄ፣ “ለመሆኑ ይሄ ሁሉ ሰው ስራዬን አንብቦ ተረድቶ ነው?” የሚል ነበር፡፡

👉 ፈፅሞ…!

✍️ እንዲያውም፣ የአይንስታይንን አጠቃላይ የአንፃራዊነት ንድፈ-ሃሳብን በተመለከተ የምትጠቀስ አንዲት ቀልድ አለች። 

✍️ የአይንስታይንን አጠቃላይ የአንፃራዊነት ንድፈ-ሃሳብን በእንግሊዝኛ ተናጋሪው ዓለም እንዲታወቅ ያስቻለውን እንግሊዛዊውን ሳይንቲስት ኤዲንግተንን አንድ ጋዜጠኛ እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል፡፡

✍️ “ለመሆኑ፣ አጠቃላዩን የአንፃራዊነት ንድፈ-ሃሳብ የሚረዱ ሰዎች ሦስት ብቻ ናቸው ይባላል፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ትላለህ?” “በእውነት…?” ይላል ኤዲንግተን ተገርሞ፣ “ለመሆኑ ሦስተኛው ሰው ማን ይሆን?” (እንግዲህ ሁለቱ ሰዎች፣ ራሱ ኤዲንግተንና አይንስታይን መሆናቸው ነው።) 

✍️ አይንስታይን በደንብ በሚያውቃት አውሮፓ ውስጥ በአሜሪካ ያየው ዓይነት የተደራጀ ህዝባዊ የዝነኞች አምልኮ (Celebrity Worship) የለም። ስራውን ያነበቡ ሊያናግሩት ይመጣሉ፤ በታላቅ ሳይንቲስትነቱ አክራሪ የናዚ ወጣቶች እንኳ ያከብሩታል፡፡ 

✍️ ከዚህ አልፎ ግን፣ የአሜሪካው ዓይነት ፍፁም ያበደና ከልክ ያለፈ፣ ወደ አምልኮ ያዘነበለ ህዝባዊ አድናቆት ግን የትም አላጋጠመውም። “ስራዬን አንብቦ ያልተረዳ ሰው እንዴት ያደንቀኛል…” ሲል የሚሞግተው አይንስታይን፣ ስራውን ሳያነቡና ሳይረዱ የሚያደንቁትን ሰዎች ጉዳይ እንደ ስድብ ነው የሚቆጥረው።

✍️ ኋላ ላይ ግን፣ አይንስታይን፣ የአሜሪካን ህዝብና የሚዲያ ባህል ይበልጥ እየገባው ሲመጣ፣ ጭራሽ በጉዳዩ ላይ ምክር ለጋሽ ሆኖ አረፈው። 

✍️ ለዓለም ሰላም የሚታገለውን አንድ የሂሳብ ፕሮፌሰር፣ አይንስታይን እንዲህ ነበር ያለው፣ “የዓለም ሰላም የምትለውን ኃሳብ እርሳው። ይልቅ ዝም ብለህ ሂሳብህን ስራ…ከዛ ታወቅ…ያኔ የፈለግከውን ብትላቸው ይሰሙሃል። አሁን ግን አንዲህ ታዋቂ ሳትሆን፣ ምን ሃሳብህ ድንቅ ቢሆን፣ ማንም የሚያዳምጥህ የለም።”

✍️ እንግዲህ የዛሬ 60 ዓመት ገደማ አሜሪካ እንዲህ ነበረች። የአሁኑ ደግሞ ጨርሶ ብሶባት ምሁራኖቿ ወደ አንዳች ታላቅ ባህላዊ ክስረት እያመራን ነው እያሉ ነው።

✍️ በአሜሪካ የባህል ግዛት ውስጥ ሆነን፣ ከምዕራቡ ዓለም የተገኘውን ቁሳዊም ሆነ ባህላዊ ኮተት በመሰብሰብ የተጠመድነው እኛም ብንሆን፣ ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ሀገር በቀል ችግሮቻችን ባሻገር፣ ይሄን አደገኛ ርካሽ ባህላዊ ክስተት እያራገብን ስለሆነ እጅጉን የሚመለከተን ጉዳይ ነው። 

✍️ አሜሪካ ውስጥ በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት፣ ከሦስት አሜሪካውያን አንዱ፣ ስመጥርና ዝነኛ ሰዎችን በማምለክ ስነ-ልቦናዊ አባዜ (Celebrity Worship Syndrome) ተጠምደዋል ሲል ይጠቁማል።

✍️ ጥናቱ፣ ይህ ስነ-ልቦናዊ ጣጣ የተለያዩ ደረጃዎች እንዳሉት ጠቅሶ፣ አንዳንድ የዚህ ስነ-ልቦናዊ አባዜ ተጠቂዎች ከሚያመልኩት ዝነኛ ሰው ጋር አንዳች የነፍስ ጥምረት አለን ብለው እንደሚያምኑ ይጠቅሳል። 

✍️ ይህ ዓይነት ስነ-ልቦናዊ ክስተት ደግሞ በፋንታው ወሰን ለለቀቀ የቀን ህልምና እሱን ተከትሎ ለሚመጣው ለማህበራዊ ህይወት ውጥንቅጥ እንደሚዳርግ ግልፅ ነው። 

✍️ ሌሎች የዚህ ስነ-ልቦናዊ ጣጣ ሰለባዎችም ቢሆኑ፣ የሚያመልኩትን ስመ-ጥር ሰው ህይወት አሳዶ በመከታተል አባዜ በመጠመድ፣ የራሳቸውን የኑሮ ኃላፊነት ሲዘነጉ ተሰተውሏል። 

✍️ ብስጩነትና፣ ተለዋዋጭ ባህሪም ቢሆን በዚህ ስነ-ልቦናዊ ጣጣ ተጠቂዎች ላይ ተደጋግሞ የሚስተዋል ክስተት ነው። የችግሩ አስፈሪ ጎን ያለው ግን፣ የአንዳንድ የጥናቱ ተሳታፊዎች የዝነኛ አምልኮ ደረጃ እዚህ ድረስ የመድረሱ ጉዳይ ነው፤ “ምንም ያህል ጉዳዩ ህገወጥ ቢሆን፣ የማደንቀው ሰው አድርግልኝ ቢለኝ የማላደርገው ነገር የለም!”

✍️ እዚህ ድረስ የሚደርስ ነው እንግዲህ የዝነኞች አምልኮ ጣጣ ጉዳይ። በዚህ ጉዳይ ላይ የፃፈችው ካርሊን ፍሎራ፣ የአንድ ወቅት የዝነኛ ገጠመኟን (Celebrity Encounter) እንዲህ ስትል ትገልፀዋለች

✍️ “ከጥቂት ዓመታት በፊት ነው፣ ብሪትኒ ስፒርስ ከነአጀቧ በአለቃዬ ቢሮ በኩል ስታልፍ አየኋት። ኮራ ዘና ባለ አረማመድ በአጠገቤ ስታልፍ…በድንጋጤ ፊቴ ሲግል ይታወቀኛል። እንደምንም የሞት ሞቴን በጠረጴዛዬ ላይ አሻግሬ ልጨብጣት እጄን ዘረጋሁ። ብሪትኒ በቀጥታ ዓይኔ ውስጥ እየተመለከተች፣ ያን ገዳይ ፈገግታዋን ፈገግ ሰትል፣ እውነቴን ነው የምላችሁ ደንዝዤ ቀረሁ። 

✍️ ከዛ በኋላ ወዲያውኑ ለጓደኞቼ እየደወልኩ አስደናቂውን የዝነኛ ገጠመኜን ማብሰር ጀመርኩ። ‘እንዴት አምሮባታል መሰላችሁ…እስከ ወለሉ የሚደርሰው ነጭ የሃር ኮቷ…ቆዳዋ ደግሞ…’ እያልኩ”

✍️ “ግን አንድ ነገር ልብ ልትሉ ይገባል…” የምትለው ፀሐፊዋ፣ “እኔኮ ፈፅሞ የብሪትኒ አድናቂ አልነበርኩም። ታዲያ ለምንድነው ብሪትኒን ማግኘቴ ይሄን ያህል አቅሌን እስካጣ ያደነባበረኝ” ስትል ትጠይቃለች። 

✍️ መልሱ ግን፣ በአብዛኛው በምዕራቡ ዓለም፣ በተለይም በአሜሪካ ስር እየሰደደ ከመጣው ልቅ የሆነ የዝነኛ አምልኮ (Celebrity Worship) ጣጣ የሚዘል አይደለም። 

✍️ የዚህ ባህላዊ ውዥንብር ዋንኛ መጠንሰሻ ደግሞ፣ በሆሊዉድ የሚመራው የምዕራቡ ዓለም የፊልም፣ የሙዚቃና የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ነው። “ከዚህ ሁኔታ ጀርባ ምንም ዓይነት የተለየ ድብቅ አጀንዳ የለም…” የሚሉት የኒውዮርክ ታይምሱ ሃያሲ ማርቲን ሜየር፣ “ብዙ ታላላቅ የሰው ልጅን ፈተናዎች በአሸናፊነት የተወጣው የምዕራቡ ዓለም ስልጣኔ፣ በስተመጨረሻ፣ ከመሰላቸትና ከድብርት ጋር ታላቅ ትንቅንቅ ገጥሟል” ይላሉ።

✍️ በዕርግጥም የመዝናኛው ኢንዱስትሪ በማኅበረሰቡ ሁለንተና ፊት የሚያዛጋውን ታላቅ የድብርትና የመሰላቸት ዓዚም ለመግፈፍ ብዙ አዳዲስ ድርጊቶችን መዘገብ፣ ጀግኖችን ፈልፍሎ ማውጣት ይጠበቅበታል። 

✍️ በዚህ ተግባር የምዕራቡ ዓለም የመገናኛ ብዙሃንና የመዝናኛ ኢንዱስትሪው አልሰነፉም የሚሉት የናሽናል ሪቪው ፀሐፊ ፖል ሆላንደር፣ “ችግሩ የፍላጎትና የአቅርቦት አለመመጣጠን ነው” ባይ ናቸው። 

✍️ “የህዝቡ የአዲስ ነገር አምሮት አጅጉን ስለበረታ ከዚህ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የአዝናኝና አስደናቂ ክስተት አቅርቦት ሊኖር አልቻለም። 

✍️ ሰዉ፣ በሚዲያው፣ ብዙ አዳዲስና አስደናቂ ክስተት፣ ብዙ ብዙ ጀግኖች ማየት ይፈልጋል” የሚሉት ሆላንደር፣ “እውነተኛ አስደናቂ ክስተቶችና የምር ጀግኖች ደግሞ ከስንት አንዴ የሚከሰቱና አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉ በመሆናቸው፣ የስልቹውንና ማለቂያ በሌለው የአዳዲስ ነገሮች አምሮት የተለከፈውን ህዝብ ፍላጎት ለማሟላት፣ ሚዲያው አዳዲስ ዝነኞችን ከየትም እያነሳ ወደ መፈብረክ አምርቷል” ይላሉ። 

*****************************************************************************
👉 ውድ የኢንፎ ቶሎ ቤተሰቦች ጽሁፉን ስላነበባችሁልን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ክፍል ሁለትን ነገ የምናቀርብላችሁ ይሆናል፡፡ እስከዚያው በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያላችሁን አስተያየት አጋሩን፡፡ መልካም ቀን፡፡

በምስራቅ ወለጋ ሙት አስነሳለው ብሎ መቃብር አስቆፍሮ ባልተሳካለት ፓስተር ውርደት ምክንያት ብዞዎች ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተመለሱ




**የፓስተሩ ውርደት**

**የምስራቅ ወለጋው አጭበርባሪ ፓስተር እግዚአብሔር በሕዝብ ፊት አዋረደው**

**የፕሮቴስታንት ውርደትና ቅሌት በሊሙ(ምሥራቅ ወለጋ)**


በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖች ጉዞ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አድርገዋል።

ሐምሌ 12/2010 ዓ.ም በሊሙ ተሊላ እንዲህ ሆነ

ሐምሌ 9 ቀን 2010 ዓ.ም በሞተር ሳይክል አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውን አቶ በላይ የተባለውን ሰው ከሞት እንዳስነሳ ጌታ ኢየሱስ ልኮኛል ብሎ ፓስተሩ የሟች ቤተሰቦችና የከተማዋ ነዋሪዎችን አስከትሎ ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሟች ወደ ተቀበረበት ስፍራ በመሄድ መቃብሩን በማስቆፈርና የአስከሬኑን ሳጥን በማስከፈት ይጮሃል፣ ይጣራል ነገርግን ሆማ ኢንጂሩ። ጉሮሮው እስኪነቃ ተነሳ እያለ ቢጮኽም አቶ አየለ አልተነሳም።

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለዘመናት ሲያጭበረብርና ሕዝብ እየዋሸ ገንዘብ ሲሰበስብ የኖረው አጭበርባሪ ፓስተር በከባድ ቅሌት ተሸማቆ ወደ ቤቱ ሄደ በርካቶች ክርስቲያኖች ደግሞ እስከዛሬ የታለልነው ይበቃናል ብለው ወደ እናት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናቸው በፍቅር ተመልሰዋል።እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን።

ፕሮቴስታንት ወገኖች እባካችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል እያሉ ከሚያታልሉ አጭበርባሪ ፓስተሮችና ሐሰተኛ ነቢያት ተለዩ።ወደ እውነተኛዋ እምነት ወደ እናት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችሁ ተመለሱ።

እባካችሁ ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ሐሰተኞችን በማጋለጥ የተሳሳቱ ሰዎችን እንመልስ።



Monday, July 16, 2018

ጠ/ሚኒስትሩ: የዋሽንግተን ዲሲው ሲኖዶሳዊ ዕርቀ ሰላም፣ ሒደቱ የሚፈጸምበት እንጅ የሚራዘምበት እንዳይኾን አደራ አሉ፤ ልኡካን አባቶችና የሰላም ኮሚቴ አባላት ተሸኙ፤ ዛሬ ምሽት ይጓዛሉ



c3d7f0e1288b03e1578ddc5d56b07506_XL
  • ተስማምታችሁ ብትችሉ ይዛችሁ ኑ! ቤታችሁ ነው፤ አገራችሁ ነው፤ ኑ በሏቸው፤
  • “በሥነ ሥርዐት ጨርሳችሁ ከተመለሳችሁ፣ በሚሌኒየም አዳራሽ ዕውቅና እንሰጣለን፤”
/ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ/
†††
  • “ተልእኳችሁ፣ የአገርም ጉዳይ ነው፤ መልካም ነገር ሠርታችሁ በውጤት እንደምትመለሱ ተስፋ እናደርጋለን፤” /የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዴኤታዋ/ 
  • “ቤተ ክርስቲያን የሰላምና የዕርቅ ቤት ናት፤ መከፋፈል የቤተ ክርስቲያን መገለጫ አይደለም፤ እግዚአብሔር ያሳካላችሁ፤”/ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ/ 
  • “ዘመኑ፥ የሰላም፣ የፍቅርና የዕርቅ ነው፤ ቤተ ክርስቲያንም አርኣያ ኾና የበለጠ መሥራት አለባት፤”/የቋሚ ሲኖዶስ አባላት/
†††
የቤተ ክርስቲያናችንና የአገራችንን ሰላምና አንድነት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተስፋ የተጣለበት የዋሽንግተን ዲሲው ሲኖዶሳዊ የዕርቀ ሰላም ውይይት፣ ሒደቱ የሚፈጸምበት እንጅ በመደራደር ብዛት የሚራዘምበት እንዳይኾን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአደራ መልእክታቸውን አስተላለፉ፡፡
FB_IMG_1531915511698
የሀገር ቤቱን ቅዱስ ሲኖዶስ በመወከል የተሠየሙት ሦስቱ ልኡካን አባቶች እንዲሁም የሰላምና አንድነት ዓለም አቀፍ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ስምንት አባላት፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ማምሻውን ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ ሲኾን፤ ረፋዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ካነጋገሯቸው በኋላ አበረታተው ሸኝተዋቸዋል፡፡
“ተስማምታችሁ ጨርሳችሁ፣ ብትችሉ ይዛችኋቸው መምጣት እንጅ በመደራደር ብዛት እንዳይራዘም፣ ለሰላም የሚከፈል ማንኛውንም ዋጋ ከፍላችሁ የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲመለስ ጥረት እንድታደርጉ አደራ እላለሁ፤” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላምና አንድነት የአገርም ሰላም አንድነት መኾኑን ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ልኡካን አባቶችም አርኣያ እንዲኾኑ አማጥነዋቸዋል፡፡ በመደራደር ብዛት ጊዜ መግደል እንደማይገባና አስፈላጊ ከኾነም ከዕርቅ በኋላ በውጭ ያሉት ወደ አገር ተመልሰው በአንድነት ሊቀጥል እንደሚችል በመጠቆም የሰላሙን ቀዳሚነት በአጽንዖት ጠቁመዋል – “ድርድር አታብዙ፤ የተለየ ንግግር ካስፈለገ ከዕርቅ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ይቀጥል፤ አንድ ላይ እዚህ መጥቶ መነጋገሩ ይሻላል፤” ብለዋል፡፡
ሲኖዶሳዊው አንድነት፣“ትልቅ ጉዳይ ስለኾነ ነው በዚህ መልኩ የምንሸኛችሁ፤” እንዳሏቸው የጠቀሱት የሰላም ኮሚቴው አባላት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “ወደ ቤታችሁ ኑ፤ አገራችሁ ነው፤ ኑ በሏቸው፤” በማለት ለሒደቱ ሰላማዊ ፍጻሜ ትኩረት በመስጠት ያስተላለፉት መልእክት፣ ልዩ የሓላፊነት ስሜት እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል፡፡ ለዓመታት የተደከመበት የዕርቀ ሰላሙ ጉዞ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሷል ብለው እንደሚያምኑና በዋሽንግተን ዲሲው ውይይትም ሒደቱ ፍጻሜ እንዲያገኝ የተቻላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ የኮሚቴው አባላት አስታውቀዋል፡፡
አክለውም፣“በሥነ ሥርዐት ጨርሳችሁ ከተመለሳችሁ፣ በሚሌኒየም አዳራሽ 25ሺሕ ታዳሚዎች ባሉበት ዕውቅና እንሰጣለን፤ ሰላም ግቡ፤ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይኹን፤ እዚያ ስመጣ እንገናኛለን፤” በማለት ዶ/ር ዐቢይ በከፍተኛ ደረጃ አበረታተው እንደሸኟቸው ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከሐምሌ 21 እስከ 23 ቀን በአሜሪካ ሦስት ከተሞች(ዋሽንግተን ዲሲ፣ ሎሳንጀለስና ሜኒሶታ)ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ጋራ የሚያካሒዱት ውይይት አመቻች ኮሚቴ ሰብሳቢ የኾኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋም፣ በትላንትናው ዕለት ለልኡካኑ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡ ተልእኳቸው፣ የአገርና የሕዝብ ሰላምና አንድነት ጉዳይም እንደኾነ ጠቅሰው፣ “በውጤት እንደምትመለሱ ተስፋ እናደርጋለን፤” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡
በተመሳሳይ ኹኔታ፣ ትላንት ከቀትር በኋላ በመንበረ ፓትርያርኩ ለልኡካን አባቶችና ለሰላምና አንድነት ኮሚቴው አባላት ጸሎትና አሸኛኘት የተደረገላቸው ሲኾን፣ “ፈጽማችሁ እንድትመጡ” የሚለው መልእክት አጽንዖት እንደተሰጠው ተመልክቷል፡፡
የወቅቱ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በዚሁ የሽኝት መርሐ ግብር፣ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰላምና የዕርቅ ቤት በመኾኗ፣ “ስለ ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት መሥራት አለብን፤” ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ መከፋፈል የቤተ ክርስቲያን መገለጫ እንዳልኾነና ልኡካኑ ለተጀመረው የዕርቀ ሰላም ሒደት ፍጻሜ የተቻላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ እግዚአብሔር ያሳካላችሁ፤ ሲሉም ጉዟቸውን ባርከዋል፡፡
የዕርቀ ሰላም ሒደቱ፣ ቅዱስነታቸው የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ እያሉ የጀመሩት እንደነበር ያወሱት በአሸኛኘቱ ሥነ ሥርዐት ላይ የተገኙ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በበኩላቸው፣ አሁንም በቅዱስነታቸው ዘመነ ክህነት መፈጸሙ፣ “መልካም አጋጣሚና ዕድል ነው፤” ብለዋል፡፡ ዘመኑ፥ የፍቅር፣ የሰላምና የዕርቅ እንደኾነ ገልጸው፣ የዕርቀ ሰላም ሒደቱ፣ ቤተ ክርስቲያን በአርኣያነትና በምሳሌነት የምትጠቀስበት በመኾኑ ልኡካኑ የበለጠ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
በኢትዮጵያም ኾነ በአሜሪካ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች፣ ላደረጉላቸው ትብብርና ለሰጧቸው ቀና ምላሽ ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ኹለተኛው ዙር የሰላምና አንድነት ዓለም አቀፍ ኮሚቴ አባላት፣ “በኹለቱም በኩል ያሉ አባቶችን በማስማማት በቅርቡ የሰላምና የፍቅር ብሥራት ለኢትዮጵያ ይኾናል፤” ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ምሽት ወደ አሜሪካ የሚያቀኑት ሦስቱ ልኡካን አባቶች፡- ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ እና ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው፡፡ ከእነርሱም ጋራ አብረው ከሚጓዙት መካከል የሰላምና አንድነት ዐቢይ ኮሚቴው አባላት ዶ/ር ንጉሡ ለገሰ እና ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ፣ ከአዲስ አበባው ቅርንጫፍ ደግሞ ዶ/ር አብርሃም አስናቀ፣ ዶ/ር ደምሴ፣ አቶ ብርሃን ተድላ፣ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴና አቶ ግርማ ዋቄ የሚገኙበት ሲኾን፣ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም በዚያው በአሜሪካ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

Saturday, July 14, 2018

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ትህዴን) ወይም ዴምህት የትጥቅ ትግል ማቆሙን አስታወቀ:

የእንፈታ ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ሲተኮስ በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ ደረሰ

በእስር ቤቱ የእንፈታ ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ሲተኮስ እንደነበርና  የቦምብ ፍንዳታም መሰማቱ ተነግሯል።
እስረኞቹን ለመጠየቅ የመጡ ሰዎች በፖሊስ እንደተደበደቡ ለማወቅ ተችሏል።
በቂሊንጦ እስር ቤት እስረኞች የእንፈታ ጥያቄ አቅርበው ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል።
እስረኞቹ የኦነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት በሚል ታስረው ከነበሩት መካከል መሆናቸውም ታውቋል።
ድሃ በመሆናችንና ታዋቂ ባለመሆናችን ከእስር አለመፈታታችን አግባብ አይደለም ሲሉ ታራሚዎቹ ተቃውሞ አሰምተዋል።
የእስረኞቹን ተቃውሞ ተከትሎ በግቢው ውስጥ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱንና የእሳት ቃጠሎ መከሰቱ ተነግሯል።
በቂሊንጦ የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች መሰማራታቸውም ነው የተገለጸው።
በእስርቤቱ የቦምብ ፍንዳታ ድምጽ እንደተሰማ ቢነገርም ስለደረሰው ጉዳት ግን የታወቀ ነገር የለም።
የእስረኞቹን ጩኽት የሰሙት የታሳሪ ቤተሰቦች በአካባቢው ጋዜጠኞችም ሲዋከቡ የሚያሳዩ በምስል የተደገፉ ማስረጃዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ተለቀዋል።
በቂሊንጦ እስር ቤት ከዚህ ቀደም በተነሳ የእስረኞች አመጽ ሳቢያ ከ20 በላይ ታራሚዎች በእሳትና በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው ይታወሳል።
በዚሁም ምክንያት 38 እስረኞች በግድያና በእሳት ቃጠሎ ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ሲመላላሱ እንደነበርም ይታወሳል።
በኋላም ከእስረኞቹ ብዙዎቹ ሲለቀቁ 4 ታራሚዎች ብቻ ፍርዱ እንዲጸናባቸው ተደርጓል።
በሙስና ሰበብ ታስረው የነበሩት የልብ ሃኪሙ ዶክተር ፍቅሩ ማሩም የቃጠሎውን ሴራና ግድያውን አቀነባብረዋል ተብለው ተጨማሪ ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር አይዘነጋም።
ዶክተር ፍቅሩ ማሩ በመጨረሻ ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል።

በግብጽ በሰው አካል ንግድ ላይ ተሰማርተው ተገኝተዋል ባላቸው 37 ግለሰቦች ላይ የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተሰማ


 የግብጽ ፍርድ ቤት በሰው አካል ንግድ ላይ ተሰማርተው ተገኝተዋል ባላቸው 37 ግለሰቦች ላይ የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተሰማ።
በሃገሪቱ የሚታተም አንድ ጋዜጣ ለንባብ እንዳበቃው የካይሮ ፍርድ ቤት በወንጀሉ ተሳትፈዋል ባላቸው ግለሰቦች ላይ ከ 7- 15 አመት ቅጣት ማስተላለፉን አስነብቧል።
ከተከሳሾቹ መካከል በህገወጥ የአካል ዝውውሩ ላይ የጤና ባለሙያዎችም እንደሚገኙበት ታውቋል።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ግብጻውያን በህገወጥ መንገድ አካላቸውን በመሸጥ ገንዘብ እንደሚያገኙም ጋዜጣው አስነብቧል።

ሰማያዊ ፓርቲ ከአርበኞች_ግንቦት7ጋር አብሮ ከመስራት እስከ ውህደት ድረስ ለመስራት ፈቃደኛ ነው

ሰማያዊ ፓርቲ በተለይ በሕብረብሔራዊ አስተሳሰብና በሰላማዊ ትግል የሚታገሉ ድርጅቶች ጋር አብሮ ከመስራት ጀምሮ እስከ መዋሃድ የሚደርስ እርምጃ ለማከናወን ፈቃደኛ እንደሆነ ከዚህ ቀደም በስራ አስፈጻሚና በምክር ቤት ደረጃ በተሰጡ ተደጋጋሚ መግለጫዎች ላይ አቋሙን ግልጽ አድርጓል፡፡ አሁንም #ከአርበኞች_ግንቦት7ጋር አብሮ ከመስራት እስከ ውህደት ድረስ ለመስራት ፓርቲያችን ፈቃደኛ በመሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት አመራሮች ጋር በመገናኘት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ፡-
1ኛ. በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና ተቋማትን ነጻና ገለልተኛ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ህዝብ እና ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሚመራው መንግስት ጋርመነጋገር በሚቻልበት መንገድ ላይ፤
2ኛ. ሁሉም በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ የተለያዩ ድርጅቶች ሰራዊቶቻቸውን ሳይበትኑ ሃገርን መጥቀም የሚችሉ ዜጎች የሚሆኑበትን እና እንደፍላጎታቸው የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል ሆነው በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ ፤
3ኛ. የዜጎች ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በእኩልነትና በተቋም ታግዞ ማስከበር የሚችል፣ የህዝብን አብሮ የመኖርና የመተማመን መንፈስ የሚያጎለብት እና ከጎረቤት አገራት ጋር በመተሳሰብ በጉርብትና መንፈስ ሊያኖረን የሚችል የዜጎች ተሳትፎ በነጻነት የሚያሳትፍ ህገ መንግስት ተዘጋጅቶ እውን በሚሆንበት ሁኔታ ላይ በዋነኝነት እንዲወያይ የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ወስኗል፡፡ via Yidnekachew Kebede

ልብወለድ የሚመስለው የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ገድል !!

ልብወለድ የሚመስለው የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ገድል !!
* * * * *
ለሀገራችን ሉዓላዊነት ለማስከበር በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈው ታላቅ ገድል ከፈፀሙ በርካታ ጀግኖች መሀል አንዱ ነው፡፡ በፈፀመው ወደር የሌለው ጀግንነት ሊታወስ የሚገባ የሀገር ኩራት። ነገር ግን ጀግንነቱ በወጉ ያልተነገረለት፡፡
ጀግናው ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ዘላለማዊ ኩራት ከሆኑ ድንቅና ብርቅዬ ተዋጊዎች መሃል በጀግንነቱ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፡ ፡
.
በ1944 ዓም የተወለደው ይህ ብርቅዬ ጀግና ታላቅ ገድል ከፈፀመባቸው የውጊያ ውሎዎቹ መሃል የሐምሌ 27 ቀን 1969 ዓ.ምህረቱ ይቀድማል፡፡ በዚያ ወቅት ትምክህተኛው የዚያድ ባሬ መንግስት በምስራቅ ኢትዮጵያ ግዙፍ ወታደራዊ ወረራ ይፈፅሞ ነበር፡፡ ይህንን ወረራ ለመመከት ከተሰማሩት የአየር ኃይል (አሜሪካ ሰራሽ ኤፍ 5 ኢ) ተዋጊ ጀቶች መሃል አንዱን የያዘው ይህ ጀግና ነበር።
እናም በኦጋዴን ሐረዋ፣ አይሻ፣ በእነኖ ሜጢ እና በሌሎችም ቦታዎች የሮኬት ናዳ በማውረድ ወራሪውን የሶማሊያ ጦር ባለበት እንዲገታ ከማድረግ ባሻገር፣ 8 የጠላት ታንኮችን ከእነምድብተኛው ረመረመ፡፡ ይህንን ታላቅ ጀግንነት ባስመዘገበ በ10 ሰዓት ልዩነት እንደገና ወደ ምስራቅ ጦር ግንባር በመብረር የኢትዮጵያን አየር ኃይል ብቃት ያስመሰከረም ነው፡-
ይህ ጀግና።ገድሉ ይቀጥላል፡-…..
.
ጥቅምት 7 ቀን 1970 ዓም፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት በጅጅጋ ካራማራ ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ ይገኛል፡፡ ያኔ እሱ ከላይ ከሰማይ በሚያወረደው ቦንብ የሶማሊያን ወራሪ ጦር ብትንትኑን ማውጣት ተያያዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ከጠላት ወገን በተተኮሰ አየር ቃወሚያ የሚያበረው ኤፍ 5 ኢ ተዋጊጀት ተመታ፡፡ ይኼኔ እሱ በዥንጥላ ወርዶ ህይወቱን ማትረፍ ነበረበት፡፡ ነገርግን የሚያበረውንም ጀት ጭምር እንጂ የራሱን ህይወት ብቻ ማትረፍ አልፈቀደም፡፡ እናም የሚያበረውን ጀት በቆራጥነት እየቀዘፈ ወደ ቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ገስግሶ በሰላም አረፈ፡፡ የተመታውም ጀት ተጠግኖ እንደገና ለግዳጅ ተሰማራ፡፡
.
ሐምሌ 30 ቀን 1969 ዓ.ም በነገሌ ቦረና ግንባር የተሰማራውን የሶማሊያ ጦር የቦንብ ናዳ በማውረድ ጠላትን ብትንትኑን ማውጣቱን ቀጠለ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ሁለት የሶማሊያ ጦር ጀቶችን በአየር ላይ አጋይቶ ጣለ፡፡ የሚገርመው አንዱን የሶማሊያ ጦር ጀት ያጋየው ሶማሊያ ግዛት ውስጥ ዘልቆ ገብቶ መሆኑ ነው፡፡
አሁንም የጀግናው ገድል ይቀጥላል፡-
.
ጥቅምት ወር 1970 ዓ.ም፡- የሶማሊያ ጦር ጀቶች ድሬደዋ ከተማ ላይ ጥቃት ፈፀሙ፡፡ ይኼኔ ለጥቃቱ የአፀፋ መልስ እንዲሰጡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተዋጊዎች ታዘዙ፡፡ ከታዘዙት ተዋጊዎች መሃል አንዱ ይህ ጀግና ነበር፡፡እናም ጀቱን እየቀዘፈ የአየር ላይ ትርዒት ጭምር በማሳየት ጀግናው ገድሉን ቀጠለ፡፡ እናም የሶማሊያን ሚግ 21ተዋጊ ጀት ከነአብራሪው በአየርላይ አጋይቶ በሰላም ወደ ቢሾፍቱ ተመለሰ፡፡ እነሆ ይህ ጀግና እንዲህ ያለ አኩሪ ገድል የፈፀመ ነው፡፡
ማነው?
.
ይህ ጀግና ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ይባላል፡፡ (በነገራችን ላይ ኮሎኔል በዛብህ፤የፕር በየነ ጴጥሮስ ወንድም ነው፡፡)ከላይ የጠቀስነውን ጀግንነት በፈፀመ ጊዜ የሻለቅነት ወታደራዊ ማዕረግ ነው የነበረው፡፡ የሆነ ሆኖ የጀግናችንን አኩሪገድል መተረካችንን እንቀጥል፡፡
.
ሕዳር 3 ቀን 1970 ዓ.ም፡፡የሶማሊያ ተዋጊ አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ጥቃት ፈፅመው ተመለሱ፡፡ ይኼኔ ሁለት የኢትዮጵያ ተዋጊዎች (ሻለቃ በዛብህ ጴጥሮስ እና ኮሎኔል ለገሰ ተፈራ) ተከትለዋቸው ገሰገሱ፡- እስከ ሞቃዲሾ ድረስ፡፡ የሶማሊያ አውሮፕላኖች ሞቃድሾ አየር ማረፊያ ደርሰው ለማረፍ ዝቅ ሲሉ፤ ጀግኖቹ ሻለቃ በዛብህና ኮሎኔል ለገሰ ተፈራ እዚያው ደፍቀው አጋዩአቸው፡፡ እናም በሰላም (እየሸለሉ) ወደ ቢሾፍቱ ተመለሱ፡፡ ይህ የጀግኖቻችን ተግባር ለሶማሊያውያን ዘላለማዊ ውርደት ያከናነነበ እንደ ነበር ታሪክ ይመሰክራል፡፡
.
የጀግናው በዛብህ ጴጥሮስ ገድል ይቀጥላል፡-
ታህሳስ 13 ቀን 1970 ዓም በዛብህ፤ ቶጎ ውጫሌ በሚባል ቦታ ላይ የሚገኝን የሶማሊያ ጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት እና መካናይዝድ ክፍለ ጦር መምሪያ በቦንብ እያጋየ ሳለ ከጠላት ወገን በተተኮሰበት አየር መቃወሚያ ጥይትየሚያበረው አውሮፕላን ሞተር ክፍል ተመታበት፡፡በዛብህ ጴጥሮስ አውሮፕላኑ ክፉኛ ቢመታም አልተደናገጠም፡፡ የተመታውን
አውሮፕላን መልሶ ደብረዘይት ለማሳረፍ ታላቅ ጥረት አደረገ፡፡
ሆኖም ጥረቱ አልተሳካም የአውሮፕላኑ ነዳጅ አለቀበት፡፡ በዚህ የተነሳ ቢሾፍቱ እና ሞጆ መሃል በሚገኝ ገላጣ ሜዳ ላይ አውሮፕላኑን አሳርፎ ድርብ ጀግንነቱን አስመሰከረ፡፡ጀግናው በዛብህ ጴጥሮስ፤ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር ተፈሪ በር በተባለ የጦር መንደር ላይ የሚገኘውን (በጥር ወር 1970) የከባድ መሳራያ ግምጃ ቤት እና የጠላት ጦርም ድባቅ መታ፡፡ በዚህ ወቅት 5 የጠላት ታንኮችን ከነምድብተኛቸው ደመሰሰ፡፡
ይሁን እንጂ አሁንም ከጠላት በተተኮሰ ፀረ አውሮፕላን ጥይት ተመቶ የሚያበረው አውሮፕላን በእሳት ተያያዘ፡፡ ጀግናው ይህም ጥቃት አላሸበረውም፡፡ እሳቱን በመከላከያ በማጥፋት ወደመጣበት ተመለሰ፡፡ አሁን ግን ቢሾፍተቱ መድረስ አልቻለም፡፡
አውሮፕላኑን ድሬደዋ አየርማረፊያ አሳረፈው፡፡አውሮፕላኑም ተጠግኖ እንደገና ለግዳጅ በቃ፡፡ይህ ጀግና ፤ ከሚያዝያ ወር 1970 ጀምሮ ኤርትራ ወደ ሚገኘው 2ኛው አየር ምድብ እንዲዛወር ተደረገ፡፡ ሻለቃ በዛብህ ጴጥሮስ የሶማሊያን ወረራ ለመቀልበስ ከሐምሌ ወር 1969 እስከ የካቲት ወር 1970 በተደረገ የመከላከልም ሆነ የማጥቃት
ውጊያ 191 ጊዜ ወደ ጠላት ወረዳ በርሯል፡፡
በዚህ የላቀ እና ታላቅ ሀገራዊ ተጋድሎ ላበረከተው አስተዋፅኦ በወቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት
መስከረም 3 ቀን 1972 ዓ.ም “የላቀ የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይ” ሸልሞታል፡፡
.
እዚህ ላይ ሻለቃ በዛብህ ጴጥሮስ ህዳር 21 ቀን 1972 ዓም ለንባብ በበቃው “ታጠቅ” የተሰኘ የሰራዊቱ ጋዜጣ ላይ ከሰጠው ቃለምልልስ የሚከተለውን መጥቀስ ይገባል፡፡ እነሆ፡-
“… እኛ ብንሞት ሌላ ሰው ይተካናል፤ መተኪያ የሌላት ሀገር ከሞተች ግን ተተኪው ትውልድ ስለሚሞት ዋጋ አይኖረውም፡፡ የሀገርን ሉአላዊነት በአስተማማኝነት መጠበቅ ቆራጥነት እና ልበ ሙሉነት ይጠይቃል፡፡ እኛ በሕይወት ቆመን እያየን ጠላት አንዲት ስንዝር መሬት ቆርሶ መሄድ ቀርቶ በአንድ እግሩ እንኳ ሊቆምባት አይችልም፡፡ ከሀገር ወዲያ ሌላ መኖሪያ ዋሻ ስለሌለ በሃገርና በነፃነት ጉዳይ ምንም ቀልድ ሊኖር አይችልም፡፡…”
.
ይህ ጀግናችን የተናገረውን ካለማወላወል በተግባር የፈፀመ ብርቅዬ ልጅ ነው፡፡ ከሶማሊያ ወረራ በኋላ ወደ ኤርትራ ዘምቶ እስከ 1977 ድረስ ግዳጁን በአግባቡ የተወጣ አርበኛ ነው፡፡ በ1977 ዓም ግን ከሻዕቢያ ጋር በናቅፋ ግንባር እየተዋጋ ሳለ አውሮፕላኑ ተመታ፡፡ አሁን ግን ወደ ተነሳበት ቦታ መመለስ አልቻለም፤በሻዕቢያ እጅ ወደቀ ጀግናችን እስረኛ ሆነ፡፡
በ1983 ዓም ከእስር ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀልም ችሎ ነበር፡፡ከሰባት ዓመት በኋላ በ1990 ዓም የኢህአዴግ ወዳጅ የነበረው ሻዕቢያ ጠላት ሆኖ መጣ ተባለ፡፡ ባድመን ወረረም ተባለ የሦሥት ወንዶች እና የሁለት ሴቶች አባት የሆነው ኮሎኔል በዛብህ የሀገሩን ክብር ለማስመለስ እና ሻዕቢያን ለመደምሰስ ዳግም ዘመተ፡፡
እንደ ልማዱ ተዋጊ አውሮፕላኑን እየሰገረ የሻዕቢያን ጦር አከርካሪ መሰባበሩን ቀጠለ፡፡ግንቦት 5 ቀን 1990 ዓም ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ወደ ኤርትራ ምድር ዘልቀው ከገቡ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተዋጊዎች አንዱነበር፡፡ የሚያበረውን አውሮፕላን ዝቅ፤….እጅግ ዝቅ….. አድርጎ የሻዕቢያን ጦር “አፈር ድሜ እያስጋጠ “ ሳለ ተመታ፤ እንደገና በሻዕቢያ እጅ ወደቀ፡፡ የሻዕቢያ እስረኛ ሆነ፡፡
እነሆ ይህ የሀገር ፈርጥ፤ ይህ ብርቅዬ ጀግናችን እስካሁን በሕይወት ይኑር አይኑር በይፋ የታወቀ ወይም የተነገረ ነገር የለም፡፡ “አውራምባታይምስ” ድረ ገፅ ኦክቶበር 16፤2013 ከሕውሐት መሪ ስብሃት ነጋ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ጀግናችን ሳይገደል እንዳልቀረ ጠቁሟል፡፡
ያሳዝናል፡፡ እንዲያም ተባለ እንዲህ ጀግናችን በልባችን ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል፡፡ እኛ ገድሉን እንዘክራለን፡፡ በታሪካችን ውስጥ ከፍ ከፍ እያደረግን እናወሳዋለን፡፡ የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ታሪክ እና ገድል ከመቃብር በላይ ነውና....
.
.
ምንጭ፡- (የአናብስት ምድር – መጽሀፍ) Wossen Ayehu አሳጥሮ እንዳቀረበው።

Friday, July 13, 2018

የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ ነው፡፡


(ኢሳት ዲሲ–ሃምሌ 5/2010)
ዩኒቨርሲቲው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው እና ለመሃመድ አህመድ ቆጴ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥም ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት መረጃ ሰጥቷል፡፡
ሃሮማያ ዪኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ከመጀመሪያ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ 7900 በላይ ተማሪዎች ሐምሌ 07/2010 ዓ.ም እንደሚያስመርቅ ታዉቋል፡፡
በዕለቱም ለርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው እና ለመሃመድ አህመድ ቆጴ የክብር ዶክትሬት ይሰጣቸዋል፡፡
የሃሮማያ ዩንቨርስቲ ለአማራ ክልል ርእሰመስተዳድር አቶ ገዱ አንድአርጋቸው የክብር ዶክትሬት ለመስጠት የወሰነው በኢትዮጵያ እየተደረገ ባለው የለውጥ እንቅስቃሴ እያደርጉ ላለው አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ነው።
መሃመድ አህመድ ቆጴ የመጀመሪያው የኦሮምኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ ሆነው በሃረር ከተማ ይሰሩ እንደነበረም ከዩኒቨርሲቲው ካገኘነው መረጃ አረጋግጠናል፡፡
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት ለሁለት ሰዎች ብቻ ነው የክብር ዶክትሬት የሰጠዉ፡፡
በማሽላ ላይ ታዋቂ ተመራማሪ እና የምግብ እና የእርሻ ድርጅት/FAO/ አማካሪው ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ እና የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ  በዩኒቨርሲቲው የእስካሁን ታሪክ የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸዉ ናቸው፡፡
በቅርቡም የጅማ ዩንቨርስቲ ለኦሮሚያው ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት መስጠቱ ይታወሳል።

wanted officials