Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 31, 2018

ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ


 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከ 27 ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተሸኙ።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ  ትናንት ጉዟቸውን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር  ላደረገው ልኡል እግዚአብሔር ምስጋና አቅርበዋል።እንዲሁም ይህ እርቅ ኣንዲወርድ አስተዋጻኦ ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ምስጋናቸውን  አቅረበዋል።
መጠለያ ሆና ላቆየቻቸው አሜሪካም ሰላሟን እና በጎውን ሁሉ ተመኝተውላታል።
ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ከ 27 ዓመታት ስደት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተጓዙ።ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ  ትናንት ጉዟቸውን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር  ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምስጋና  አቅረበዋል። መጠለያ ሆና ላቆየቻቸው አሜሪካም ሰላሟን እና ብጎወን ሁሉ ተመኝተውላታል።
“በሃዘን እና በለቅሶ ከሃገራችን ተሰደን ነበር።ነገር ግን የእግዜብሄር ግዜ ሰለደረሰ ወደ አገራችን እንመለስ ዘንድ እነሆ የእግዜብሄር ፈቃድ ሆኗል”  በማለት ለመመለስ መወሰናቸውን እና ቀን መቁረጣቸውን ትናንት ሃምሌ 23 /2010 ያስታወቁት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ሃምሌ 19 ቀን 2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት የተካሄደው ሥምምነት ለዚህ ወሳኔ እንዳበቃቸው አመልክተዋል።
በተለይም ቅዳሜ ሃምሌ 21 /2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ ያቀረቡላቸው ጥያቄ  ለአፋጣኙ ርምጃ ምክንያት መሆኑንም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ  አመልክተዋል።
ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ  ትናንት ጉዟቸውን በተመለከተ በሰጡት  በዚሁ መግለጫ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር  ከፍተኛ ግፊት እና አስተዋጾ ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምስጋና  አቅረበዋል። መጠለያ ሆና ላቆየቻቸው አሜሪካም ሰላሟን እና በጎወን ሁሉ ተመኝተውላታል።
ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ  እና አብረዋቸው ዛሬ ከዋሺንገተን  ዲሲ የተነሱት አባቶች ነገ ረቡዕ አዲስ አበባ ይገባሉ። ከፍተኛ የአቀባበል መርሃ ግብርም ተዘጋጅቷል። 6ኛው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ዛሬ አዲስ አበባ  ላይ በሰጡት መግለጫ የቤተክርስቲያኒቱ አንድነት በመመለሱ  ደስታዬ ወሰን የለውም ብለዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials