Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 26, 2018

የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ


የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ
 ግድቡን በዋና ሃላፊነት ሲመሩ የነበሩት ኢንጂነር ስመኛው በቀለ መስቀል አደባባይ ከዋናው መንገድ ገባ ብሎ በቪ 8 መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ መገኘቱን የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ ዘይኑ፣ ኢንጂነር ስመኛው ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው እንደነበረ፣ በቀኝ እጃቸው በኩል ኮልት ሽጉጥ መገኘቱን ገልጸዋል። ፖሊስ የአይን እማኞችንና ማስረጃ ይሰጣሉ የተባሉትን ሰዎች ይዞ ምርመራ እያደረገ መሆኑን፣ ቢሮአቸውንም ፈትሾ መረጃ ማሰባሰቡን ተናግረዋል።
የኢንጂነሩ አሟሟት በርካታ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል። በዜናው የተደናገጡ ወጣቶች በድንገት ተሰባስበው ወደ ኢቲቪ ቢሮ በመሄድ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። እንዲሁ በርካታ የመዲናቅዋ ወጣቶች ኢንጂነሩ ሞተው በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በጎንደር ከተማም እንዲሁ ሞቱ ያስደነገጣቸው ወጣቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ቁጣቸውን ገልፀዋል።
ኢንጂነሩ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስራውን በበላይነት በመቆጣጠር ግድቡ አሁን ላለበት ደረጃ አድርሰውታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ሞት እንደሰሙ መደንገጣቸውንና ሀዘናቸውን መግለጻቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል።
እንደ ኃላፊው አቶ ፍጹም አረጋ ገለጻ ዶክተር አብይ ይህን አስደንጋጭና ልብ ሰባረኢ ዜና የሰሙት አሜሪካ ሲደርሱ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ለኢንጂነር ስመኘው በቀለ ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማስተላለፋቸውንም ከአቶ ፍጹም ገለጻ ለመረዳት ተችሽሏል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials