የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ አጎራባች ድንበር ለይ ሰፍሮ የነበረውን ጦሩን ከአካባቢው እንዲነሱ ማድረጉን ሮይተርስ ዘገበ ።
በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሰፈረው የኤርትራ ጦር ከአካባቢው እንዲነሳ የተደረገው በሁለቱ ሀገራት መካከል የተወሰደውን የእርቅ እርምጃ መነሻ በማድረግ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ኢትዮጵያ ከግጭቱ ወዲህ የመጀመሪያ የተባሉትን አምባሳደር አቶ ሬድዋን ሁሴን በአስመራ መመደቧ ታውቋል ።

No comments:
Post a Comment