Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 20, 2018

ኢሳያስ አፈወርቄ የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት ጋበዙ


(ኢሳት)
 የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት አስመራ ጋበዙ።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብዣ መሰረት ነገ አስመራ ይገባሉ።
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገጻቸው እንደገለጹት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ በቅጽል ስማቸው ፎርማጆ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ነገ ማለዳ አስመራ ይገባሉ።
የኤርትራ መንግስት አልሻባብን ይረዳል በሚል በቀረበበትና በኋላም ምንም ማረጋገጫ እንዳልተገኘበት በይፋ በተገለጸው ወንጀል ሳቢያ ከሶማሊያ መንግስታ ጋር ጤናማ ግንኙነት ሳይኖረው ቆይቷል።
አሁን ላይ ታዲያ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ በሁለቱ ሃገራ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሃገሪቱን ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆን ወደ ኤርትራ እንዲመጡ ግብዣ አቅርበውላቸዋል።
የሃገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገጻቸው  የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አስመራ እንደሚገቡ አስፍረዋል።
ይህ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት በዚህ ሰአት ደግሞ ፎርማጆ ኤርትራ ገብተው ጉብኝታቸውን መጀመራቸው ተሰምቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ኤርትራን ጎብኝተው ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ በይፋ የተባበሩት መንግስታትን መጠየቃቸው ይታወሳል።
ከአካባቢው ሃገራትም ሆነ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ግንኙነቷ በፍጥነት እየተሻሻለ ያለችው ኤርትራ ከጅቡቲም ጋር ውዝግባቸውን ለመፍታት በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ተመልክቷል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያና በዩናይትድ አረብ ኢምሬት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
በዩናይትድ አረብ ኢምሬት ጉብኝታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር የተገናኙ ሲሆን ሁለቱ ላደረጉት የሰላም አስተዋጽኦ የሃገሪቱን ከፍተኛ ሜዳሊያ መሸለማቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials