ሰማያዊ ፓርቲ በተለይ በሕብረብሔራዊ አስተሳሰብና በሰላማዊ ትግል የሚታገሉ ድርጅቶች ጋር አብሮ ከመስራት ጀምሮ እስከ መዋሃድ የሚደርስ እርምጃ ለማከናወን ፈቃደኛ እንደሆነ ከዚህ ቀደም በስራ አስፈጻሚና በምክር ቤት ደረጃ በተሰጡ ተደጋጋሚ መግለጫዎች ላይ አቋሙን ግልጽ አድርጓል፡፡ አሁንም #ከአርበኞች_ግንቦት7ጋር አብሮ ከመስራት እስከ ውህደት ድረስ ለመስራት ፓርቲያችን ፈቃደኛ በመሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት አመራሮች ጋር በመገናኘት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ፡-
1ኛ. በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና ተቋማትን ነጻና ገለልተኛ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ህዝብ እና ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሚመራው መንግስት ጋርመነጋገር በሚቻልበት መንገድ ላይ፤
1ኛ. በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና ተቋማትን ነጻና ገለልተኛ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ህዝብ እና ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሚመራው መንግስት ጋርመነጋገር በሚቻልበት መንገድ ላይ፤
2ኛ. ሁሉም በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ የተለያዩ ድርጅቶች ሰራዊቶቻቸውን ሳይበትኑ ሃገርን መጥቀም የሚችሉ ዜጎች የሚሆኑበትን እና እንደፍላጎታቸው የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል ሆነው በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ ፤
3ኛ. የዜጎች ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በእኩልነትና በተቋም ታግዞ ማስከበር የሚችል፣ የህዝብን አብሮ የመኖርና የመተማመን መንፈስ የሚያጎለብት እና ከጎረቤት አገራት ጋር በመተሳሰብ በጉርብትና መንፈስ ሊያኖረን የሚችል የዜጎች ተሳትፎ በነጻነት የሚያሳትፍ ህገ መንግስት ተዘጋጅቶ እውን በሚሆንበት ሁኔታ ላይ በዋነኝነት እንዲወያይ የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ወስኗል፡፡ via Yidnekachew Kebede
No comments:
Post a Comment