Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 12, 2018

አብዲ ኢሌ የፓርላማ አባሉን አሰሩ



( ኢሳት ዜና ሃምሌ 5 ቀን 2010 ዓ/ም ) ትናንት በክልሉ ለተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት የቀድሞውን የደህንነት ሚኒስትር ተጠያቂ ያደረጉት የሶማሌው ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ኢሌ፣ አቶ ጌታቸውን በተመለከተ ከአጀንዳ ውጭ በፓርላማ መናገራቸውን በመንቀፍ ለአፈ ጉባኤውና ለሶማሊ ክልል አመራሮች ደብዳቤ የጻፉትን አቶ አብዲ ዴሬን “የጌታቸው ደጋፊ” በሚል ዛሬ አስረዋቸዋል።
የፓርላማ አባሉ አቶ አብዲ ዴሬን በደብዳቤያቸው “የስብሰባው አጀንዳ ከጸደቀ በኋላ ም/ቤቱ ካፀደቀው አጀንዳ ውጪ በሆነ ጉዳይ ሁለት ሰዓት ሙሉ እንድናዳምጥ ተገደናል ብለዋል።
ም/ቤቱ ቀኑን ሙሉ ዶ/ር አቢይ አህመድ ያስተላለፉትን የይቅርታ መልእክትና የክልሉ አመራር አካላት አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተ ያላቸውን ፍራቻ ነው እንድናዳምጥ የተደረግነው ያሉት አቶ አብዲ ዲሬን፣ “ዶ/ር አቢይ ባስተላለፉት የይቅርታ መልእክት ላይ አቶ ጌታቸውን አልተካተቱም ወይ?” ሲሉ ጠይቀዋል።
“ይህን ልጠይቅ የቻልኩበት ዋንኛ ምክንያት እኔን እስከገባኝ ድረስ የይቅርታ መልዕክቱ እኛንም ጨምሮ በአጠቃላይ ለሁሉም ሰው የተላለፈ መልዕክት ስለመሰለኝ ነው”ያሉት የምክር ቤቱ አባል፣ በዚህ ረገድ ም/ቤቱ ለክልሉ ህዝብ እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ከመወያየት ይልቅ ቀኑን ሙሉ ስለ አንድ ከስራ ኃላፊነቱ ስለተነሳ ግለሰብ ላይ ግዜያችንን ማጥፋታችን ከምክር ቤቱ ደንብ ውጪ ከመሆኑም በተጨማሪ የም/ቤቱን ክብር የሚነካ ጉዳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡” ብለዋል።
በዚህ የቅሬታ ደብዳቤ የተቆጡት አቶ አብዲ ኢሌም “የኦጋዴንን ማእከላዊ እስር ቤት ዘግተው መስኪድ እንደሚያደርጉት የገቡት ቃል አንድም ቀን ሳያድር የምክር ቤቱን አባል አስራዋቸዋል
ትናንት “ጌታቸው አሰፋ ጣልቃ እየገባ አላሰራኝ አለ” እያሉ የተናዘዙት አቶ አብዲ፣ ከእርሳቸው ጀርባ ሆነው በክልሉ ህዝብ ላይ ጥፋት ሲያደርሱ ስለነበሩት የመከላከያ ጄኔራሎች ምንም የተናገሩት ነገር የለም።Image may contain: 1 person, sitting

No comments:

Post a Comment

wanted officials