Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 20, 2018

በምስራቅ ወለጋ ሙት አስነሳለው ብሎ መቃብር አስቆፍሮ ባልተሳካለት ፓስተር ውርደት ምክንያት ብዞዎች ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተመለሱ




**የፓስተሩ ውርደት**

**የምስራቅ ወለጋው አጭበርባሪ ፓስተር እግዚአብሔር በሕዝብ ፊት አዋረደው**

**የፕሮቴስታንት ውርደትና ቅሌት በሊሙ(ምሥራቅ ወለጋ)**


በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖች ጉዞ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አድርገዋል።

ሐምሌ 12/2010 ዓ.ም በሊሙ ተሊላ እንዲህ ሆነ

ሐምሌ 9 ቀን 2010 ዓ.ም በሞተር ሳይክል አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውን አቶ በላይ የተባለውን ሰው ከሞት እንዳስነሳ ጌታ ኢየሱስ ልኮኛል ብሎ ፓስተሩ የሟች ቤተሰቦችና የከተማዋ ነዋሪዎችን አስከትሎ ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሟች ወደ ተቀበረበት ስፍራ በመሄድ መቃብሩን በማስቆፈርና የአስከሬኑን ሳጥን በማስከፈት ይጮሃል፣ ይጣራል ነገርግን ሆማ ኢንጂሩ። ጉሮሮው እስኪነቃ ተነሳ እያለ ቢጮኽም አቶ አየለ አልተነሳም።

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለዘመናት ሲያጭበረብርና ሕዝብ እየዋሸ ገንዘብ ሲሰበስብ የኖረው አጭበርባሪ ፓስተር በከባድ ቅሌት ተሸማቆ ወደ ቤቱ ሄደ በርካቶች ክርስቲያኖች ደግሞ እስከዛሬ የታለልነው ይበቃናል ብለው ወደ እናት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናቸው በፍቅር ተመልሰዋል።እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን።

ፕሮቴስታንት ወገኖች እባካችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል እያሉ ከሚያታልሉ አጭበርባሪ ፓስተሮችና ሐሰተኛ ነቢያት ተለዩ።ወደ እውነተኛዋ እምነት ወደ እናት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችሁ ተመለሱ።

እባካችሁ ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ሐሰተኞችን በማጋለጥ የተሳሳቱ ሰዎችን እንመልስ።



No comments:

Post a Comment

wanted officials