Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, December 22, 2016

ወያኔ እንዲሞት ከወር በፊት ያሟዋረተበት አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ዛሬ አረፈ

በኦሎምፒክ መድረክ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ ታሪክ ሲያነሳው የሚኖረው ማርሽ ቀያሪው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ዛሬ ማረፉ ተሰማ::  
በካናዳ ህክምናውን ሲከታተል የቆየው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በሕይወት እያለ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሞተ ብሎ ዜና አውጆበት ነበር:: ሆኖም ግን አትሌቱ ከልጁ ጋር በመሆን ከካናዳ በለቀቀው ቭዲዮ በሕይወት መኖሩን መናገሩ ይታወሳል::
ምሩጽ ሜይ 15, 1944 በትግራይ አዲግራት ከተማ እንደተወለደ የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል::
ማርሽ ቀያሪው እየተሰኘ የሚወደሰው አትሌት ምሩጽ በሞስኮ ኦሎምፒክ የ5,000 እና የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ነው:: ከዚህ የሞስኮው ኦሎምፒክ ድሉ 8 ዓመታት ቀደም ብሎ እ.አ.አ በ1972 የሙኒክ ኦሎምፒክ ወቅት ግን እጅግ አሳዛኝ ገጠመኝ ነበረው፡፡
በ5,000 ሜትር በ10,000 ሜትርና በሌሎችም ውድድሮች 271 የወርቅ ሜዳልያዎች ባለቤትና በአሁኑ ወቅት የ670 ብር ጡረተኛው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በሙኒክ ኦሎምፒክ ወቅት በ5,000 ሜትር ውድድር 3ኛ ወጥቶ (መቼም ለኢትዮጵያውያን ይሄ ሽንፈት ነውና) በ10,000 ሜትር ውድድር ደግሞ አሰልጣኙ ዘግይተውበት ወደ ሜዳ እንዳይገባ ተከልክሎ….እያለቀሰ ቢመለስም ሀገር ቤት ሲመጣ 8 ወራት መታሰሩ ይታወሳል::
Image may contain: 1 person, outdoor
Image may contain: 3 people, outdoor

No comments:

Post a Comment

wanted officials