Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, June 29, 2015

ሻለቃ አርጋው ካብታሙ ከአገር እንዳይወጡ ተከለከሉ

ሻለቃ አርጋው ካብታሙ ከአገር እንዳይወጡ ተከለከሉ
ሻለቃ አርጋው ካብታሙ የቀድሞውን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተለያዩ እርከኖች ሲያገለግሉና በገዢው ስርዓት አፈና ተፈጽሞባቸው ወህኒ የተወረወሩ ኢትዮጵያዊያንን ዘር፣የሐይማኖትና የፓርቲ አጥር ሳይከልላቸው በመጠየቅና በማጽናናት ይጠቀሳሉ፡፡ሻለቃ በቅርቡ አሜሪካን አገር የሚገኘው ልጃቸው ለሚፈጽመው የሰርግ ሰነ ስርዓት በቦታው ለመገኘት አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተው በበረራቸው ቀን ቦሌ ኤርፖርት እንዳመሩ ስማቸው ከአገር እንዳይወጡ መመሪያ ከተላለፈባቸው ሰዎች አንዱ በመሆናቸው በልጃቸው ሰርግ ለመታደም ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ግኑኝነት አላቸው አልያም ስርዓቱን ይቃወማሉ ተብለው በጥርጣሬ ውስጥ ከሚገኙ ዜጎች መካከል የ500 ሰዎችን የስም ዝርዝር በቦሌ ኤርፖርት ተርሚናል ውስጥ የሚሰሩ የምዝገባ ሰራተኞች መያዛቸውን መረጃዎቸ ይጠቁማሉ፡፡
በዛ ያሉ ወጣቶችም በቦሌ በኩል ከአገር ለመውጣት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ፓስፖርቶቻቸውን ተነጥቀው እንዲመለሱ መደረጋቸውና አንዳንዶቹም በድንበር በኩል በሟቋረጥ ከአገር መውጣታቸው ይታወቃል፡፡
ህገ መንግስቱ የዜጎች የመዘዋወር መብት መከበሩን በወረቀት ደረጃ የሚያትት ቢሆንም መንግስት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ህገ መንግስቱን በመጨፍለቅ የዜጎችን እንቅስቃሴ በመገደብ የበቀል እርምጃ መውሰዱ አምባገነንነቱን ወለል አድርጎ ያሳያል ፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials