Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 6, 2015

የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው ወጣት ስንታየሁ ቸኮል፣ የጤንነቱ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገለጸ





የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው ወጣት ስንታየሁ ቸኮል፣ የጤንነቱ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገለጸ

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ወጣቶች ጉዳይ ኋላፊ የነበረው ወጣት ስንታየሁ ቸኮል፣ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንደሚገኝ ገለፀ።

ከሚያዚያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘውና ‹‹ስብሰባን በማወክ ወንጀል›› ተከሶ ጥፋተኛ ተብሎ የ6 ወር እስራት የተፈረደበት ወጣት ስንታየሁ፣ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዞን አንድ ልዩ ጥበቃ ተብሎ በሚታወቀው ክፍል ውስጥ ታስሮ እንደሚገኝ አስረድቷል። ክፍሉ ጨለማ ከመሆኑ በተጨማሪ ከፍተኛ የቅዝቃዜ መጠን እንዳለውና ይህም በጤናው ላይ እከል ሊፈጥርበት እንደሚችል ገልጿል። ክፍሉ ሁለት በ ሁለት የሆነ ጠባብ ክፍል እንደሆነና ከ አራት ሰው በላይ ሊይዝ እንደማይችል ነገር ግን በአሁኑ ሰአት እሱን ጨምሮ ስድስት ሰዎች በክፍሉ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ጠቁሟል። ከክፍሉ ስንቅ ለመቀበል ብቻ እንደሚወጣና ከቤተሰብም ሆነ ከጓደኛ በቀን ከ30 ደቂቃ ላልበለጠ ጊዜ ብቻ እየተገናኘ እንዳለም ተናግሯል። ከዚህ በተጨማሪ ‹‹በዚህ ዞን ውስጥ የምንገኝ እስረኞች ህክምናም ሆነ የፀሃይ ብርሃን ማግኘት ባለመቻላችን የጤናችን ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል›› ሲል ገልጻል፡፡


በዞን 1 ልዩ ጥበቃ በልዩ ስሙ ‹‹ታንከር›› በሚባለው ክፍል ውስጥ የሚገኘው ስንታየሁ፣ ከ15 ቀናት በላይ ፍራሽ እንዳይገባለት ተደርጎ በቀዝቃዛው ወለል ላይ እንዲተኛ መደረጉን ተናግሯል። ከእሱ ውጪ በክፍል ውስጥ የሚገኙት ሰዎች የእድሜ ልክና የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው እስረኞች መሆናቸውና በዚህ ክፍል ውስጥ አጭር የእስራት ጊዜ የተላለፈበት እስረኛ እንደማይገኝ ጠቁሟል። ‹‹እኔ የ6 ወር እስራት የተላለፈበኝ የፖለቲካ እስረኛ ስለሆንኩ እዚህ ዞን ውስጥ ልመደብ አይገባም›› በማለት ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በማመልከቻ ጥያቄውን ማቅረቡን የገለፀው ስንታየሁ፣ ጥያቄው ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱን አስረድቷል። ከማረሚያ ቤቱ ኋላፊ ዘንድም ‹‹የአንተ ጉዳይ ልዩ ጉዳይ ስለሆነ ምንም ማድረግ አንችልም። ምን አድርገህ እንደገባህ እናውቃለን እንደገባህበት ተወጣው›› የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ገልጿል።

‹‹በአሁኑ ሰዓት በዚህ ዞን አንድ ውስጥ የምንገኝ እስረኞች ሁላ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ የምንገኝ መሆናችን፣ ህክምና መነፈጋችንና ያለንበት ቦታ ህይወታችንን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ሁሉም ሰው ሊረዳው ይገባል›› በማለት አስተያየቱን ሰንዝሯል፡፡ በቃሊቲ ዞን አንድ ውስጥ ስንታየሁን ጨምሮ 18 ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ከስንታየሁና ከሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ከሆነው አህመድ ሙስጠፍ፣ ውጪ የእድሜ ልክና የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው እስረኞች ብቻ በዚህ ዞን ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials