Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, June 3, 2015

የአይ.ሲ.ስን ግድያ ለማውገዝ ሰልፍ የወጣው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ከሶስት ዓመት በላይ እስር ተፈረደበት



 የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት በሚያዚያ 14/2007 በሊቢያ በአይ.ሲስ አሸባሪ ቡድን በሊቢአ በግፍ የተገደሉ ወገኖች ላይ ተወሰደውን በመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ አደባባይ በመገኘቱ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረሃል በሚል ተይዞ የቆው ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ዛሬ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ የመናገሻ ፍርድ ቤት እንደተፈረደበት ፓርቲው ይፋ አድርጓል።

ከፓርቲው የተገኘው መረጃ እንደሚገልጸው ናትናኤል የኣለም ዘውድ ዛሬ ግንቦት 25ቀን 2007 ዓ.ም የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት የቀረበው ወጣት ናትናኤል የዓለም ዘውድ ላይ የቀረበው ክስ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር›› የሚል ሲሆን አቃቤ ህግ ከፍርዱ በፊት ‹‹ሁከትና ብጥብጡን የፈጠረው ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ የፈፀመውን አይ ኤስ አይ ኤስ ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ላይ በመሆኑ፣ በተፈጠረው ረብሻ በርካታ ሰዎች የተጎዱ በመሆኑ እና ረብሻውን የፈፀመው አምስተኛው አገራዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመሆኑና ይህም አደጋውን ያባብስ የነበር መሆኑን በማገናዘብ›› የሚል የቅጣት ማክበጃ መጨመሩንም ይሄው መረጃ ገልጿል።

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ክስ ተከሰው በዚሁ ፍርድ ቤት የቀረቡት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤና መሳይ የተባለ ሌላ ወጣት መከላከያ ምስክር ለማቅረብ ለሰኔ 4 ተቀጥረዋል፡፡ እነ ማቲያስ ‹‹ሰልፉ ላይ ሀሰተኛ ወሬ በማውራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወር፣ ህዝቡን አትነሳም ወይ በማለት…›› የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ያስታወሰው ይሄው ፓርቲው መረጃ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ይቀርባል ተብሎ የነበረው የቪዲዮ ማስረጃ ባለመቅረቡ በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርብላቸው መጠየቃቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials