Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, June 11, 2015

ሰበር ዜና – በሰሚት መድኃኔዓለም የሰንበት ት/ቤት አባላት እስር ወደ ምእመናን ተሸጋገረ፤ በአንድ ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው

  • ‹‹ጉዳዩን በፌስቡክ እያጋጋላችኹ ነው›› የተባሉ 16 የሰንበት ት/ቤት አባላትና ምእመናን ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል

  • በሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ፣ ያለው ፈርሶ በአዲስ ምዝገባ በሚቋቋመው ሰንበት ት/ቤት ዕድሜአቸው ከ30 በላይ የኾኑ ይባረራሉ

  • ‹‹አዲስ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም ያዘዝኹት እኔ ነኝ፤ ዑራኤል ጸሐፊ ኾኜ 700 ሰንበት ተማሪ በትጥቅ ድጋፍ አስበትኛለኹ››/ሥ/አስኪ.የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ/

aba-gebre-sellassie-amare-of-summit
የፖሊስ ጣቢያው እንዳሻቸው የሚያዙበት አለቃው መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ አማረ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመካነ ሰላም ሰሚት መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት አመራር እና አባላት ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ፣ እስር እና እንግልት ወደ አባላቱ ወላጆች ተሸጋገሮ እየከፋ መሔዱ ተገለጸ፡፡
የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ አማረ ዛሬ፣ ግንቦት ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ፣ በአገልግሎት ላይ የነበረውን ሰንበት ት/ቤት በማፍረስ ሌላ እንደሚቋቋም እና የአባላት ምዝገባ እንደሚያካሒዱ ሲገልጹ የሰንበት ት/ቤቱ አባላትና ምእመናኑ በአንድ ድምፅ ተቃውመዋቸዋል፡፡
‹‹ያለው ሰንበት ት/ቤት ምን ኾኖ ነው አዲስ ምዝገባ የሚካሔደው?›› በማለት በአንድ ድምፅ በመጠየቅ ተቃውሟቸውን በብርቱ ካሰሙት መካከል፣ ዘጠኝ ምእመናንና ሰባት የሰንበት ት/ቤት አባላት በስም እየተጠሩ ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎሮ ፖሊስ ጣቢያ በአስተዳዳሪው ትእዛዝ ተይዘው ተወስደዋል፡፡
ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ደብሩ የመጡት አለቃው መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሥላሴ፣ በቃለ ዐዋዲው ለሰንበት ት/ቤቱ የተደነገገውን ወጣቶችንና ሕፃናትን የማደራጀት እና የማቋቋም ሓላፊነት በመጣስ በየአጥቢያው የምእመኑን ልጆች በሀብት መደብ እየከፋፈሉ የሀብታም ልጆችን እናስተምራለን ለሚሉ ግለሰቦች አስተዳደራዊ ድጋፍ በመስጠታቸው የተጀመረው ውዝግብ፣ ለሰንበት ት/ቤቱ አመራሮች እና አባላት መታሰር፣ መከሠሥ እና መታገድ፤ ለጽ/ቤቱና ለአዳራሹም መታሸግ ምክንያት ኾኗል፡፡
ከሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት መታሸግ ወዲኽ የአባላት ወላጆች የኾኑ ምእመናንንም ጭምር በማካተት ዛሬ የተፈጸመው እስር፣ ወከባ እና እንግልት በአንድ ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ የደረሰ ነው፡፡ ትላንት ጠዋት ሰባት አባላት ‹‹ለምን ጥያቄ ትጠይቃላችኹ›› በሚል ታስረው ወዲያው የተለቀቁ ሲኾን ባለፈው ረቡዕ ደግሞ ‹‹የአዲስ ምዝገባውን ማስታወቂያ ገንጥላችኋል›› በሚል አምስት አባላት ከ5፡00 – 8፡00 በጎሮ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው መለቀቃቸው ታውቋል፡፡
ምእመናኑንና የሰንበት ት/ቤት አባላቱን በተደጋጋሚ በማሰር የአለቃው ፈቃድ ፈጻሚ የኾነው የጎሮ ፖሊስ ጣቢያ ለቀረበለት የጣልቃ ገብነት ጥያቄ፣ ‹‹አባ ገብረ ሥላሴ አዝዘውኛል፤ እርሳቸው ያዘዙኝን ብቻ ነው የምፈጽመው›› ቢልም ከቀትር በኋላ ከአቅሜ በላይ ነው በሚል ምእመናኑንና የሰንበት ት/ቤት አባላቱን አምቼ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዳቸው ተገልጧል፡፡

Source:: haratewahido

No comments:

Post a Comment

wanted officials