Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 11, 2018

በደርግ ወቅት ኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ደራሲ አረፋ -<> ለደራሲና ገጣሚ ይስማዕከ እንድረስለት

ሲሆን ለሁለት አመታት ያህል የቤተክህነት ትምህርት ከተከታተለ በኋላ ወደB.V ስዊድሽ ሚስዮን ተዘዋውረው ለሌላ ሁለት አመታት ቀጥሎ በጄኔራል ውንጌት ተምሯል።በስዊድሽ ሚስዮን በሚማሩበት ወቅት አንደኛው መምህሩ ቄስ ገ/አምላክ ሩፋኤል ሲሆኑ የታዋቂው ደራሲ የበእምነት ገ/አምላክ አባት ናቸው።በጄኔራል ዊንጌት ቆይታው ስነፅሁፍ እና ቴአትር አካባቢ ከብርሃኑ ባዬ እና ከጥበቡ ጋር ይንቀሳቀስ የነበረ ሲሆን ከ4ኛ ክፍል ጀምሮ ለ8 አመታት ያህል ዩልዮስ ቄሳርን ተርጉሞ ለምርቃት ያዘጋጅ የነበር ቢሆንም በወቅቱ የከበደ ሚካኤል ሮምዮና ዡልየት በመታተሙ ሊቀር ችሏል።
የ12 ኛ ክፍል ትምህርቱን በሚገባ አጠናቆ ለብሪትሽ G.C.E የተቀመጠ ሲሆን ሁሉንም የኦ ደረጃ ፈተናዎች አልፎ ትምህርቱን በችግር መክንያት መቀጠል ባለመቻሉ ወደ ትምህርት ምንስትር ለስራ ጎራ አለ።እዛ ነው እንግዲህ የወቅቱን የለውጥ አራማጆች እነ ገርማሜ ንዋይ እና ሚልዮን ነቅንቅን ያገኘው።ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤልም ምንስትርና አለቃው ነበሩ ።
በዚሁ ወቅት ነበር ለብዙ አመት የለፋበትን ዩልዮስ ቄሳርን በተስፋ ገ/ስላሴ ማተምያቤትያሳተመው።
ብዙ ጭቅጭቅን አስከተለ የንጉሱን ፎቶ በመጀመርያ ገፁ ስላልያዘ የእንግሊዝ ትምህርቱም ተስፋ በዚሁ ስለጨለመ ወደ ጅማ በመምህርነት ተቀጥሮ ሄደ ።ከዛም ሲመለስ የስነፅሁፍ ስራውን የቀጠለ ሲሆን የመንግስቱ ለማ የቅርብ ጓደኛ ሲሆን ከገጣሚና ሰአሊው ገብረክርስቶስ ደስታ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ በደባልነት ለበርካታ ግዜ ኖረዋል።ሶሎሞን ደሬሳና ዳኛቸው ወርቁም ጓደኞቹ ነበሩ።ከጅማ መልስ ወደ ሩስያ በአማርኛ መምህርነት ተልኮ በሌኒን ግራንድ ለብዙ ወቅት ቆይቷል።የትዳር አጋሩን ወ/ሮ አልማዝ በቀለን ያገኘውም በዚህ ወቅት ነበር።
የኒኮላይ ጎጎልን "ዋናው ተቆጣጣሪ "ን በዚህ ወቅት ነበር መተርጎም የጀመረውከዛ መልስ በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ ገብቶ በስነ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን ወደ ኤዲንበርግ በመሄድ የማስተርስ ትምህርቱን ጀምሮ የነበረ ቢሆንም አልጨረሰም ሌኒንግራንድ ዩንቨርስቲም በፍልስፍና ማስተርሱን መማር ቢችልም አላገባደደውም ።
ወደትምህርት ምንስትር ተመልሶ የፋይን አርት ክፍሉ መሪ በመሆን ማገልገል ጀመረ።ቆይቶም በቋንቋዎች አካዳሚ በመዛወር ሃገሩን ያገለገል ሲሆን በወቅቱ ከተሰሩት ስራዎች መሃል የፊደላት በአንድመልክየማስቀመጥ(standardization)የጥንት የግእዝ ቅኔያት ግጥሞችን ስነቃሎችን የማሰባሰብ የሳይንቲፊክ መዝገበ ቃላት እና ሌሎችንም ማዘጋጀት ይገኙበታል።
በብርሃኑ ዘርይሁንና በአሉ ግርማ አርታኢነት ብዙ ፅሁፎችን ለአዲስ ዙመን ከመፃፉ ሌላ በዩልዮስ ቄሳር፣ዋናው ተቆጣጣሪ ፣የመስከረም ጮራ የግጥም ስብስብ በመሳሰሉት ስራዎች ይታወቃል ።
ሶስተኛው ደራሲ ይስማዕከ ሲሆን በደረሰበት አደጋ መክንያት መናገር እንደሚከበደው እና ሌሎችም ችግሮች እንዳጋጠሙት በቅርቡ ተናግሯል ።እባካችሁ ለዚህ ወጣት ባለብሩህ ተስፋ ደራሲና ገጣሚ እንድረስለት እንላለን! !

No comments:

Post a Comment

wanted officials